Friday, July 25, 2014

††† መቅረዝ ዘተዋሕዶ - የውዳሴ ማብራርያ መጽሐፍ በቅርብ ቀን በገበያ ላይ ትውላለች †††


መቅረዝ ዘተዋሕዶ ከዚኽ በፊት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ባዘጋጁት የትርጓሜ መጽሐፍ ተተንተርሳ የተዘጋጀች መጽሐፍ ስትኾን የምትለየውም በሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች ነው፡-
፩ኛ) የጥንቱን ለዛ ሳይለቅ ቀለል ባለ አቀራረብና ይዘት በእያንዳንዱ ምዕመን እጅ እንዲደርስ በማሰብ መዘጋጀቷ፤
፪ኛ) “እንዲል፣ እንዳለ፣ እንዲሉ” የሚለውን ጥንታዊ አቀማመጥ ጸሐፊውንና ደራሲውን መለየቷ፤
፫ኛ) አንዳንድ ተጨማሪ ማብራሪያ የሚያስፈልጋቸውን ምንባባት ከተለያዩ ድርሳናት ተጨማሪ ማብራሪያ መያዟ፤
፬ኛ) የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ በሚያስፈልጋቸው ቦታዎች ላይ ጥቅሱን በማስቀመጥ ምዕመናን እንዲያመሳክሩት መንገድ መክፈቷ፡

Friday, July 11, 2014

ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ



(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሐምሌ ፭ ቀን፣ ፳፻፮ ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
 በዛሬው ዕለት የምናከብረው በዓል ኹለቱም ታላላቅ ሐዋርያት በሰማዕትነት ያረፉበትን በዓል ነው፡፡ ይኽ ዕለት በየዓመቱ አይለዋወጥም፡፡ የሐዋርያትን ጦም ከጨረስን በኋላ የምናከብረው ነው፡፡ በዚኽ ዕለት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በቅዳሴዋም በትምህርቷም ኹሉ እነዚኽን ታላላቅ ሐዋርያት ታነሣለች፤ ታወድሳለች፤ ሰማዕትነታቸውንም ለልጆቿ ታስተምራለች፡፡ ምንም እንኳን በእነዚኽ ሐዋርያት ስም የተሰየመ ቤተ ክርስቲያን በብዛት ባይገኝም በአዲስ አበባ ግን “ብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ” የሚባል ቤተ ክርስቲያን አለ፡፡
 ወደ ሰሜኑ የአገራችን ክፍል ስንሔድ ይኽ ዕለት “ሓወርያ” ተብሎ ይጠራል፡፡ ስያሜውም የእነዚኽን ሐዋርያት ሰማዕትነት ለመግለጥና ለማሰብ የተሠጠ ነው፡፡ እረኞች ጅራፋቸውን ገምደው በቡድን በቡድን እየኾኑ ያስጨኹታል፡፡ የጅራፉ ጩኸት የእነዚኽ ሰማዕታት መገረፍ፣ መቁሰል፣ መሰየፍ፣ መሰቃየት፣ መሰቀል የሚያስታውስ ነው፡፡ አባቶቻችን ክርስትናውን ማንበብና መጻፍ ወደማይችለው ማኅበረ ሰብእ ምን ያኽል እንዳሰረጹትም ከዚኽ እንገነዘባለን፡፡ እኛ ግን እንኳንስ ለተማረው ማስተማር ይቅርና አባቶቻችን የሠሩትን እንኳን መጠበቅ አቅቶናል፡፡

Wednesday, July 9, 2014

ለመቅረዝ ዘተዋሕዶ ድረ ገጽ ወዳጆች

(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሐምሌ ፪ ቀን፣ ፳፻፮ ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!



መቅረዝ ዘተዋሕዶ መንፈሳዊት ድረ ገጽ አድራሻ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህሕዶን እምነት ሥርዓት ትውፊትና ታሪክ መሠረት ያደረጉ ትምህርታዊ የኾኑ ጽሑፎች በአራት በተለያዩ ቋንቋዎች ላለፉት ዓመታት ወጥተዋል፡፡ እነዚኽ ትምህርቶች በሀገር ውስጥም ኾነ ከሀገር ውጪ የኢንተርኔት አቅርቦት ላላቸው ምዕመናን በተቻለ መጠን ለማድረስ ተሞክሯል፡፡ ነገር ግን እነዚኽን መንፈሳውያን ጽሑፎች በዓቅም ማነስ ምክንያት ቴክኖሎጂውን መጠቀም ላልቻሉ  ምዕመናን ሊዳረሱ አልቻሉም፡፡

FeedBurner FeedCount