Friday, July 19, 2013

ፈቃደ እግዚአብሔር- (ክፍል ሁለት)

በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ በድጋሜ የተለጠፈ)፡- ባለፈው ዕትም ፈቃደ እግዚአብሔርን ለመቀበል እንዳንችል ከሚያደርጉን ምክንያቶች አንደኛውንና ‹‹ ክፉው ከእግዚአብሔር አይደለም›› የምንለውን የተሳሳተ ሀሳባችንን ከቅዱሳት መጻሕፍት አንጻር ተመልክተን ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ ሁለተኛውን ብቻ እንመለከታለን፡፡

ፈቃደ እግዚአብሔር (ክፍልአንድ)

በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ

(መቅረዝ ዘተዋሕዶ- በድጋሜ የቀረበ ጽሑፍ)፡- በአሁኑ ጊዜ በምንኖረው ሕይወት ከፍተኛ ግራ መጋባት ከሚፈጥሩብን ነገሮች ውስጥ ፈቃደ እግዚአብሔርን የተመለከተው ቀዳሚ ሥፍራ የሚወስድብን ይመስለኛል፡፡የምናዝንባቸው፣ የምንበሳጭባቸው፣ መደረጋቸውን መቀበል እስከሚያቅተን ድረስ የምንረበሽባቸው ድርጊቶች በተፈጸሙ ጊዜ መፈተናችን ይጨምራል፡፡ ነገሮቹ በቤተ ክርስቲያን አካባቢ ሲሆኑ ደግሞ የበለጠ እንፈተናለን፡፡ እንዲያውም አንዳንድ ጊዜ ወይ እምነታችን የተሳሳተ ካለበለዚያም እግዚአብሔር የእኛን ጸሎት መስማት ያቆመ ይመስለናል፡፡ እንደዚህ ዓይነት ስሜቶች ደግሞ መቋሚያቸው ይህ ብቻ አይደለም፤ ከፍተኛ ጥራጣሬ ላይ ጥለውን ብቻ ሳይሆን ደስታችንንም ሰርቀውብን አጎረምራሚና ወቃሽ አድረገውን፤ በቤተ ክርስቲያናችንና በአንዳንድ የቤተ ክርስቲያን አካላትም ላይ እንድናኮርፍ አድርገውን በአጠቃላይ  መንፈሳዊ ሕይወታችንም ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥረውብን ያልፋሉ ወይም እኛን ወደ ሌላ ሕይወት ያሳልፉናል፡፡ በተለይ በእነዚህ ጊዜያት ‹‹ የእግዚአብሔር ፈቃድ›› ነው ተቀበሉ የሚል ሰው ከገጠመን ልናደምጠው እንቸገራለን፤አንዳንዴማ ልባችንን ዘልቆ ከገባው ሐዘን የተነሣ የሚናገርን ሰው ሞኝነቱ ብቻ ሳይሆን በእኛ ኅሊና የተሳለው አላዋቂነቱም እየታየን ብስጭታችን ሊጨምር ይችላል፡፡ ለመሆኑ ክፉ ሰዎች ግፍ ሲፈጽሙ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ማታለልና ተንኮል ሲፈጸም ይህን ሁሉ ፈቃደእግዚአብሔር ነው ብሎ መቀበል ይቻላልን? የፈቃደ እግዚአብሔር ድንበሩስ ምንድን ነው? ክፉ ሰዎች ሲሾሙ፣በሀገርና በሕዝብ ላይ አስከፊ ነገር ሲፈጸም አደጋና ጥፋት ሲደርስስ ፈቃደ እግዚአብሔር ነው ማለት ይቻላል? የምንፈልገው መልካም ነገር የማይፈጸመውስ ለምንድን ነው? እግዚአብሔር በጎው እንዲፈጸም አይወድምን? ወይስ ፈቃዱ የሚሆነው መቼ ነው?እነዚህ ሁሉ ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ጥያቄዎች ሆነው የሚያስቸግሩበት አጋጣሚ ብዙ ነው፡፡ ጉዳዮቹን በቀጥታ ከማየታችን በፊት ፈቃደ እግዚአብሔርን ለመቀበል የሚፈትኑን ነገሮች እናስቀድም፡፡

Thursday, July 18, 2013

ፈቃደ እግዚአብሔር (ክፍል ሦስት)



በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ ሐምሌ ፲፪ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም)፡- ባለፉት ጊዜያት ፈቃደ እግዚአብሔርን እንዳንረዳ ያደረጉንን ሁለት ምክንያቶች ተመልክተን ነበር፡፡ በዚህ ክፍል ደግሞ ከችግሮቹ ውስጥ ሦስቱን አቀርባለሁ፡፡ በሚቀጥለውና በመጨረሻው ክፍል ግን ፈቃደ እግዚአብሔርን እንዴት እንደምንረዳ አይተን ጽሑፉ ይጠናቀቃል፡፡ መልካም ንባብ!

Wednesday, July 17, 2013

ውሉደ ብርሃን ትሆኑ ዘንድ በብርሃን እመኑ - የዮሐንስ ወንጌል የ፵፯ኛ ሳምንት ጥናት (ዮሐ.፲፪፡፴፬-፶)

በገ/እግዚአብሔር ኪደ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ ሐምሌ ፲ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም)፡- ውሸት በእልፍ የሚያማምሩ ሕብረ ቀለማት ብትቀባም ውሸትነቷ ከመታወቅ አታመልጥም፡፡ ያረጀና ያፈጀ ግድግዳም ምንም ያህል በሚያምር ቀለም ቢቀባም አዲስ መሆን አይችልም፡፡ የሚዋሽ ሰውም እንደዚሁ ነው፡፡ ምንም ያህል ውሸቱን እውነት በሚመስሉ ውብ ቃላት ቢያሽሞነሙነውም ውሸታም መሆኑ በቀላሉ ይታወቃል፡፡ በአይሁድ ሕዝብ ዘንድ የምናስተውለውም ይኸንኑ ነው፡፡ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ከምድር ከፍ ከፍ ያልሁ እንደሆነ ሁሉን (በአሚን) ወደ እኔ እስባለሁ” ሲላቸው /ቁ.፴፪/ እነርሱ ግን መልሰው፡-እኛስክርስቶስ (በመሲሑ) ሞት እንደሌለበት፣ ለዘለዓለምም እንደሚኖር በኦሪት ሰምተናል /መዝ.፻፱፡፬፣ ኢሳ.፬፡፮፣ ሕዝ.፴፯፡፳፮፣ ዳን.፯፡፲፫-፲፬/፤ አንተስ የሰው ልጅ ክርስቶስ ይሰቀል ዘንድ አለው እንደምን ትላላህ? ይህ የሰው ልጅ ክርስቶስስ ማን ነው?” ይሉታልና /ቁ.፴፬/። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ይህን አንቀጽ በተረጐመበት ድርሳኑ እንዲህ ይላል፡- “ምንም እንኳን እነዚህ ሰዎች መሲሑ (ክርስቶስ) ለመዘኑ ኅልፈት ለመንግሥቱም ሽረት የሌለበት ዘለዓለማዊ መሆኑን ከተለያዩ መጻሕፍተ ብሉያት ቢያነቡም፣ እዚያው ዘለዓለማዊነቱን ባነበቡበት ቦታ ላይም ለሰው ልጆች ሲል ስለሚደርስበት መከራ መስቀልና ስለ ትንሣኤው ጨምረው አንብበዋል፡፡ ‘ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም’ /ኢሳ.፶፫፡፯/፤ ‘ይሁዳ የአንበሳ ደቦል ነው፤ ልጄ ሆይ፥ ከመሰማርያህ ወጣህ፤ እንደ አንበሳ ተኛህ እንደ ሴት አንበሳም አንቀላፋህ እንደ አንበሳ ደቦልም የሚቀሰቅስህ የለም’ /ዘፍ.፵፱፡፱/ እና የመሳሰሉት ቃላት ደጋግመው አንብበዋቸዋል፡፡ ነገር ግን ጌታችን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ (መሲሑ) አይደለም ለማለት ስለፈለጉ ብቻ ‘እኛስ በመሲሑ ሞት እንደሌለበት፣ ለዘለዓለምም እንደሚኖር በኦሪት ሰምተናል’ ይላሉ፡፡ የመሲሑ ሞት ዘለዓለማዊነቱን የሚጻረር አስመስለው ለማቅረብ ይሞክራሉ፡፡ አንዱን ጫፍ ብቻ በመያዝም ወደ ስሕተት ይነጉዳሉ፡፡ ‘ከፍ ከፍ ያልሁ እንደሆነ’ ሲላቸው ‘እሞታለሁ እሰቀላለሁ’ ማለቱ እንደሆነ ስለገባቸው ‘አቤቱ ሆይ! ስለመሲሑ የምናውቀው አሁን እንደነገርንህ ነው፡፡ ስለዚህ አሁን ይሞታል ይሰቀላል የምትለው መሲሕ ፈጽመን አናውቀውም (አንተን አናውቅህም) ይሉታል” ይላል /St. John Chrysostom, Homily LXVIII/፡፡ ዓምደ ሃይማኖት የተባለው ቅዱስ ቄርሎስም “ከመጻሕፍት ጥቅስ በመጥቀስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚያስተምረው ትምህርት ሐሰት ነው ለማለት ይጥሩ ነበር” ይላል /St. Cyril of Alexandria, Commentary on The Gospel of John, Book 8/፡፡

FeedBurner FeedCount