Wednesday, February 26, 2014

ዘወረደ ዘሠሉስ



በዲ/ን ስመኘው ጌትዬ

(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ የካቲት 17 ቀን፣ 2006 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ
ጸልዩ እምቅድመ ንባበ ዝንቱ ክርታስ
 አባታችን በትናንት ሰኞ ዘወረደ ድርሰቱ አንዳየነው ከላይ በወረደው በጌታ ስም ጀምሮ በዓለም ታንቀንበት የነበረውን ያለፈውን የኃጢአት ገመድ አላቆ የጾምን ክብር በተለይም የዚህን ጾም ክብር ገልጦልናል።በመጨረሻም ተመለሱ ወደ እርሱም ቅረቡ እርሱም አለም ከሚሰጣችሁ ደስታ የተለየ ደስታ ይሰጣችኋል ብሎን ነበረ። ዛሬ ደግሞ በዛው ነፍሳችን በምትሰማው ሠማያዊ ዜማ የሚለን ነገር አለ።

ዘወረደ ዘሰኑይ



በዲ/ን ስመኘው ጌትዬ



(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ የካቲት 16 ቀን፣ 2006 ዓ.ም.)፡-  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ ጸልዩ እምቅድመ ንባበ ዝንቱ ክርታስ

የብሉይ እና የሐዲስ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ከጸዋትወ ዜማ መጽሐፍቱ አንዱ በሆነው የድጓ ክፍል ጾመ ድጓ (በጾም ስለሚደረስ ጾመ ድጓ ተብሏል) ስለ ጾም ብዙ ጽፏል። ዛሬ ታዲያ እኔ የምፈቅደው እዚህ ያንን ሰማያዊ ዜማ ስለ ጾም በጾም ለጾመኞች እየተዜመ ብንሰማው ነበረ።ነገር ግን አሁን እሱን ማድረግ አንችልም። ነገር ግን ምንም እንኳን አባታችን በዜማ ያስተላለፈውን መልእክት በጽሁፍ መግለጤ ሰማያዊውን መልእክት ዋጋ እንዳያሳጣው ቢያስፈራኝም በጌታ ባለን ድፍረት እያነበብነው ለፍሳችን በነባቢት ባህሪይዋ ዜማውን እንድትሰማው እርሱ እንዲፈቅድ እየጸለይን ዛሬ ከሰኞ ዘወረደ ድርሰቱ በጥቂቱ የተመረጡ የጾም ቃላትን እያነበብን እንማማራለን። ግእዙን ብጽፈው የሀይለ ቃሉን ኀይል በተረዳነው ነበረ። ነገር ግን ይገባን ዘንድ በአማረኛ እስከገለጠልን ድረስ እናየዋለን

Thursday, January 9, 2014

ለመላው ኦርቶዶክሳውያን ፦ ታላላቅ የአንድነት የስብከትና የዝማሬ ጉባኤያትን ስለማዘጋጀት - ጥቆማ



በታምራት ፍሰሓ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ጥር ፪ ቀን፣ ፳፻፮ ዓ.ም.)፡- ኦርቶዶክሳዊት እምነታችን በብዙ መስክ (በቅዳሴ በማህሌት በሰአታት በሰርክ ጉባኤያት በበዓላት ዝግጅቶች) በልዩ ስርአት ወጥነት ሐዋርያዊ መሰረተ እምነቷን ለምእመናን ስታስተላልፍ ቆይታለች አሁንም በማስተላለፍ ላይ ትገኛለች፤ በቅዳሴው ለተካፈለ በማህሌቱም ለተሳተፈ በሰአታቱም ለተገኘ በሰርክ ጉባኤውም ላልቀረ ይህ እሙን ነው፡፡ ነገር ግን ስንቶቻችን በነዚህ ተገኘን? ካልተገኘንስ እንደምን እምነታችንን ልናውቅ በእምነታችንስ ልንፀና ይቻለናል?

ብዙወቻችን ደግሞ የቤተክርስቲያን ታላላቅ በዓላትን (ደመራ ጥምቀት) መሰረት በማድረግ ተገኝተን እናከብራለን ይህም በጣም ብዙ ኦርቶዶክሳዊ በአንድነት የሚገናኙባቸው ክስተቶች ቢሆኑም ነገር ግን እኒህ ልዩ በዓላት እንደመሆናቸው የራሳቸው የሆነ የአከባበር ስርአትና ይዘት ያላቸው በመሆኑ በዚህ ጊዜ ለሚገኙ ምእመናን የሚገባውን ያህል ትምህርት ሰጥተው የሚያልፉ አይደለም ይልቅስ በነዚህ በዓላት ጥቂት ከመዘመርና በዓሉን የመታዘብ ያክል ከተመለከትን በኅላ ወደቤታችንም ሆነ ወደሌሎች ጉዳዮች የምንመለስ ብዙወች ነን፡፡ ስለዚህም ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ በአንድነት ተሰባስበን የቤተክርስቲያናችንን ስብከቷን ዝማሬዋንም ሆነ ልዩ ልዩ ሃሳቦቿን የምንረዳባቸው የምንሳተፍባቸውና የምንወያይባቸው መድረኮች የሉንም፡፡

FeedBurner FeedCount