Sunday, October 4, 2015

የዘመናችን አጥማቂ ነን ባዮች፡- የሐሳዊው መሲሕ መንገድ ጠራጊዎች



በዲ/ን ዳንኤል ክብረት
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ መስከረም 23 ቀን 2008 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ክፍል አንድ
በዚህ ዘመን በተደጋጋሚ ከሚነሡ መንፈሳውያን ጥቄዎች መካከል አንዱ የጥምቀትና አጥማቂዎች ጉዳይ ነው፡፡ ጥምቀት(የክርስትና ጥምቀትን አይመለከትም) በብሉይና በሐዲስ ኪዳን ምእመናን ፈውሰ ሥጋ ፈውሰ ነፍስ እንዲያገኙባቸው ከእግዚአብሔር ከተሰጡ ጸጋዎች አንዱ ነው፡፡(2 ነገሥት 5 ዮሐ. 5፣ዮሐ. 9)፡፡ በቤተ ክርስቲያን ታሪክም ውስጥ በልዩ ልዩ ገድላተ ቅዱሳን ላይ እንደምናነበው በጠበል ሕዝቡን ሲፈውስ ኖሯል፡፡ ሕዝብ ፈውስ የሚያገኝባቸው እንደ ሰሊሆምና እንደ ቤተ ሳይዳ የታወቁ የቃል ኪዳን ቦታዎችም ነበሩ፡፡
አሁን በያዝነው ዘመን አያሌአጥማቂ> የሚባሉ ሰዎች ተነሥተዋል፡፡ ክብራቸውን የሚገልጥ ማስታወቂያ ያስነግራሉ፣ መቁጠሪያ ይሸጣሉ፣ ቅባት ይቀባሉ፣ አዳራሽ ከፍተው ወይም ሕዝብ በሜዳ ሰብስበው እንፈውሳለን ይላሉ፤ ሰይጣን ተናገረ የሚባለውን በካሴት ቀድተው ይሸጣሉ፡፡ ከዚህ ቀጥዬ በማቀርባቸው አሥር ምክንያቶች እነዚህን ሐሳውያን መቀበል የለብንም ብዬ አምናለሁ፡፡

Friday, October 2, 2015

ቅዱስ ቀሌምንጦስ ዘሮም



በሥርጉተ ሥላሴ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ መስከረም 21 ቀን 2008 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
በጥንታዊቱ ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያትን አህለው ሐዋርያትን መስለው ከተነሡ እጅግ ከሚታወቁት ሐዋርያነ አበው መካከል፥ የቅዱስ ጴጥሮስና የቅዱስ ጳውሎስ ደቀ መዝሙር የነበረው ቅዱስ ቀሌምንጦስ ዘሮም አንዱ ነው፡፡ ስለዚሁ ቅዱስ ሰው ብዙ ዓይነት አመለካከት ያለ ሲኾን፥ አውሳብዮስ ዘቂሳርያ፣ አባ ጀሮም እና ሌሎች አርጌንስን ተከትለው የቅዱስ ጳውሎስ ደቀ መዝሙር እንደ ነበረ ያስተምራሉ /ፊልጵ.4፥3/፡፡ “የንጉሥ ድምጥያኖስ የአጎት ልጅ ነው” የሚሉም ያሉ ሲኾን፣ ሌሎች ደግሞ “እጅግ ጥበበኛና የተማረ ሰው የነበረና በኋላም ዕውቀትን ፍለጋ ወደ ፍልስጥኤም ሲሔድ ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር ተገናኝቶ ክርስቲያን ኾኗል” ይላሉ /አባ ቴዎድሮስ ያ.ማላቲ፣ ሐዋርያነ አበው፣ ገጽ 64/
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ. ሊቃውንት የሚታመነውና ሕዳር 29 የሚነበበው ስንክሳር እንደሚነግረን ደግሞ፥ ቀሌምንጦስ ዘሮም ትውልዱ ከንጉሣውያን ቤተ ሰቦች ነው:: አባቱ “ቀውስጦስ” የሮማው ንጉሥ የጦር አለቃ የነበረ ሲን፥ በቅዱስ ጴጥሮስ ስብከት አምኗል:: በአንድ ወቅት “ቀውስጦስ” ወደ ሮማው ንጉሥ ዶ ለብዙ ቀናት ቢዘገይ ወንድሙ ሚስቱን ለማግባት ፈለገ:: የቀሌምንጦስ እናት ይህንን ማ ቀሌምንጦስንና ታናሽ ወንድሙን ይዛ አባታቸው እስኪመለስ ድረስ ፍልስፍና ይማሩ ብላ ወደ አቴንስ ከተማ ለመድ ተነሣች:: በመርከብ ተሳፍረው ሲዱ ሳሉ ግን ኃይለኛ ማዕበል ተነሥቶ መርከቧን ሰባበራት ንም በታተናቸው:: ቀሌምንጦስንም ከቤተ ሰቦቹ ለይቶ እስክንድርያ አደረሰው:: ቅዱስ ጴጥሮስ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ እስክንድርያ ከተማ ገብቶ ሲያስተምር ከቀሌምንጦስ በቀር አማኝ አላገኘም:: ቀሌምንጦስ የቅዱስ ጴጥሮስን ስብከት ሲሰማ በጌታችን አምኖ የክርስትና ጥምቀት ተጠመቀ፤ ከዚችም ሰዓት ጀምሮ የቅዱስ ጴጥሮስ ደቀ መዝሙር ፡፡
ቅዱስ ሄሮኔዎስ እንደሚነግረን፥ በኋላ ላይ የሮማ ከተማ አራተኛው ሊቀ ጳጳስ ኗል /በእንተ መናፍቃን፣ ሣልሳይ መጽሐፍ 3:3/፡አውሳብዮስ ዘቂሳርያም ከዚህ ተነሥቶ “ጊዜው ከ92 እስከ 101 ዓ.ም. ነው” ይላል፡፡

Wednesday, September 30, 2015

በዶክተር ዓለማየሁ ዋሴ መጽሐፍ "እመጓ"ላይ የቀረበ አጭር ሥነ ጽሑፋዊ ዳሰሳ



ከዲ/ን ብርሃኑ አድማስ ምጽሐፈ ገጽ የተወሰደ

(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ መስከረም 19 ቀን 2008 ዓ.ም.)፤- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
የመጽሐፉ ርእስ - እመጓ
ደራሲ፡- ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ (/)
የገጽ ብዛት፡- 204
የኅትመት ዘመን፡- ነሐሴ 2007 ..(ሁለተኛ ዕትም)
ዋጋ - 65 ብር
መጽሐፉ ምንድን ነው?
ሲጀመር መጽሐፉ እውነተኛ ታሪክ ነው? ልቦለድ ነው? የጉዞ ማስታወሻ ነው? ወይስ ምን ልንለው እንችላለን? የሚሉትን ጥያቄዎች መልሰን ካልጀመርን መጽሐፉን የምንዳስስበትን መርህ ለመምረጥ ስለማያስችለን በትንሹም ቢሆን ማንሳቱ የግድ አስፈላጊ ነው፡፡ የታሪኩን መጽሐፍ እንደ ልቦለድ፣ ሌላውንም በሌላ መንገድ ልንመረምረው አንችልምና፡፡

Saturday, September 26, 2015

መስቀል ኃይል

በልዑል ገብረ እግዚአብሔር
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ መስከረም 15 ቀን 2008 ዓ.ም.)፦ በስመ አብ ወወልድ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

የአዳም ነገር……
በቀራኒዮ መሐል ቀጠሮ ተይዞለታል
የገመጣት ፍሬ መዘዝ ወልዳ
ከሰገነት……...ቁልቁል ሰድዳ
ብርሃን ልብሱ ተገፎበት
ልበ ምቱ……..ቀንሶበት
ክብሩን ሊመልስለት
…….የማይሻረው ቃልን ሰጥቶታል!

የእሳት አጥር ጉድጓድ ጨለማ ቤት ሰፍፎ
ለዚህ አልነበረም…….ተፈጥሮው
በሲኦል ከተማ መጋኛ ሊመታው
ያ የሰው በኩር የፊጥኝ ታስሮ
በዲያቢሎስ ቀንበር ተቀንብሮ
እሳቱን ሲያሳርሰው በጅራፍ ጀርፎ
ባርነትን ተፈራርመው
………………..ፀጋ ልብሱን ገፍፎ ገፍፎ!

ዋይ! ዋይ! ዋይ!
የሲቃ ድምፀት ምህረት የለሹ እኩይ ግዛት
አዳም እንጂ የተጎዳ…
እበላለው ብሎ የተበላ
…………..እወጣለው ብሎ የወረደ
በፍቃዱ …….
ከግዛቱ ወደ ግዞት ተሰደደ ተዋረደ

FeedBurner FeedCount