Monday, February 22, 2016

ትንቢተ ዮናስ - ክፍል ኹለት



(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ የካቲት 14 ቀን 2008 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!


ምዕራፍ ኹለት


ዮናስ ወደ ባሕሩ ተጣለ፡፡ ኾኖም ይሞት ዘንድ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነውና ይሞት ዘንድ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር የነነዌን ሰዎች እንዲያድናቸው ወዷልና ዮናስ የተጣለው እንዲሞት አይደለም፡፡ በሰዎች እይታ ዮናስ ለዚህ የተገባ አይደለም ሊባል ይችላል፡፡ በእግዚአብሔር እይታ ግን የተገባ ነው፡፡ አሁንም እግዚአብሔር ይወዷል፤ ልጄ ይሏል፤ የእኔ ነቢይ ብሎ ይጠራዋል፡፡ ምንም እንኳን ለወገኖቹ ለእስራኤል አዝኖ አልታዘዝ ቢልም፣ አለመታዘዙ ወደ ሌላ ኃጢአት እንዲገባ ቢያደርገውም አሁንም እግዚአብሔር ዮናስን ይፈልገዋል፡፡ ነነዌን ያድናታል፡፡ እግዚአብሔር ትዕግሥተኛ ነው፡፡ እንደ እኛ ለፍርድ አይቸኩልም፡፡ ለመቅጣት አይቸኩልም፡፡ በወደቁ ልጆቹ ፈጥኖ አይፈርድም፡፡ ለፍርድ የምንቸኩለው እኛ ነን፡፡ ከወደቁ ሰዎች ጋር ያለን ግንኝነት ፈጥነን የምናቋርጥ እኛ ነን፡፡ እርሱ እግዚአብሔር ግን እንዲህ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ጠባቂ ነው፡፡ በጣም ብዙ ጊዜ ይጠብቃል፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ በትዕግሥት የሚጠብቀን ባይኾን እስከ አሁን ማን ይቆይ ነበር? ማን ቀና ብሎ ይሄዳል? የቆየነው እንጀራ ብቻ በልተን አይደለም፤ መድኃኒት ውጠንም አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ስለጠበቀን እንጂ፡፡ ስንበድል ዕድሜ ለንስሐ ሰጥቶን እንጂ፡፡ ስንቶቻችን መርዝ በጥብጠናል? ስንቶቻችን ገመድ አንጠልጥለናል? ስንቶቻችን ስለት ስለናል? እግዚአብሔር ግን ከዚያ ጠበቀን፡፡ አሁንምልጄ! እወድሃለሁ፤ ልጄ! እወድሻለሁይለናል፡፡

Sunday, February 21, 2016

ትንቢተ ዮናስ - ክፍል አንድ



(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ የካቲት 13 ቀን 2008 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
መግቢያ፡
ትንቢተ ዮናስ 46 የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት አንዱ ነው፡፡ የመጽሐፉ ጸሐፊም ነቢዩ ዮናስ ይባላል፡፡ ዮናስ ማለት ርግብ፣ የዋኅ ማለት ሲኾን የነበረበትም ዘመን በዳግማዊ ኢዮርብአም ዘመነ መንግሥት /825-784 .../ ነው፡፡ በትውፊት እንደሚነገረው ዮናስ ነቢዩ ኤልያስ ከሞት ያስነሣው የሠራፕታዋ መበለት ልጅ ነው /1ነገ.1810-24/፡፡ ነቢዩ ዮናስ ምንም እንኳን የእስራኤል ነቢይ ቢኾንም ያስተማረው ከምድረ እስራኤል ውጪ ማለትም በነነዌ ስለኾነ፣ ነቢየ አሕዛብ ይባላል፡፡ ሊቃውንት እንደሚናገሩት ይህቺ ነነዌ በጤግሮስ ወንዝ ምሥራቃዊ ቆሬ፣ ከዛሬዋ የሞሱል ከተማ በተቃራኒ ከባግዳድ ሰሜን ምዕራብ 350 .. ርቀት ላይ ነበረች፡፡ የትንቢተ ዮናስ መጽሐፍ ዋና መልእክት እግዚአብሔር የእስራኤል ብቻ ሳይሆን የአሕዛብም አምላክ እንደሆነና በንስሐ ወደ እርሱ የተመለሱትን ሁሉ በምሕረት እንደሚጐበኝ ማሳየት ነው፡፡ በመሆኑም በአራት ተከታታይ ክፍል የእያንዳንዱን ምዕራፍ ትርጓሜ በተለይ ደግሞ ከሕይወታችን ጋር እያገናዘብን እንመለከተዋለን፡፡ ቅዱሳን አባቶቻችን ይህን የነነዌን ጾም ከዓቢይ ጾም ኹለት ሳምንት አስቀድመን እንድንጾመው ማድረጋቸው ያለ ምክንያት አይደለምና፡፡ በዚህ መጽሐፍ በሁዳዴ ጾም ልናከናውነውና ሊኖረን የሚገባ የንስሐና የጾም ዓይነት ምን ሊመስል እንደሚባ፣ የእግዚአብሔር ፍቅርና ጥበብ እንደምን የበዛ እንደኾነ፣ ነቢያት እንኳ ድካም እንደነበረባቸውና እንደምን እንደተነሡ እንመለከታለን፡፡ እግዚአብሔር ማስተዋሉን ያድለን፡፡

Friday, February 19, 2016

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የሃይማኖታችን ሊቀ ካህናት- የመጨረሻው ክፍል (ክፍል አምስት)!

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የሃይማኖታችን ሊቀ ካህናት- የመጨረሻው ክፍል (ክፍል አምስት)!:        በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!   ተወዳጆች ሆይ! እንደ እግዚአብሔር ሐሳብ ለመማማር የጀመርነው ርእስ የሚያልቅ ስላልሆነ እናንተ በይበልጥ ከሊቃውንት ከመጻሕፍት እንድታዳብሩት እ...

Wednesday, February 17, 2016

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የሃይማኖታችን ሊቀ ካህናት- ክፍል አራት!

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የሃይማኖታችን ሊቀ ካህናት- ክፍል አራት!:        በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ውድ ክርስቲያኖች! የእግዚአብሔር ፍጹም ሰላም ይብዛላችሁ! አሜን! በክፍል ሦስት ትምህርታችን ወደ ስድስት የሚሆኑ ነጥቦችን አይተን ነበር፡፡ ለ...

FeedBurner FeedCount