አባታችን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በጊዜው የነበረችው
ጨካኝ ንግሥት (ኤውዶክስያ) በክፋት ተነሣስታ በመንፈቀ ሌሊት አስጠርታ በፈረስ በሠረገላ አድርጋ ወደ ደሴተ አጥራክያ ስታግዘው
ለራሱ እንዲህ አለ፡- ንግሥቲቱ ከከተማ ስታስወጣኝ ምንም ዓይነት ንዴት አልተሰማኝም፤ ይልቁንም ለራሴ እንዲህ አልኩ እንጂ፡-
Sunday, September 30, 2012
Thursday, September 27, 2012
የዕርቅ ቀን
በእግረ ሕሊናችሁ ከአዲስ አበባ በሰሜን አቅጣጫ 1010 ኪ/ሜ ልውሰዳችሁ፡፡
የጠቀስኩላችሁን ያህል ርቀት ስትጓዙ ዓድዋ ከተማ ትደርሳላችሁ፡፡ ዓድዋ ማለት “ኦድዋ” ከሚል የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም
ከበብዋት ማለት ነው፡፡ ከተማዋ ይህን ስም ያገኘችው ዙርያዋ በተስዓቱ ቅዱሳን ገዳማት የተከበበች ስለሆነ እንደሆነ ይነገራል፡፡
አጠገብዋም ዓዲ አቡን - የአቡን ሀገር የምትባል ሌላ ከተማ
አለች፡፡ እዚያ አከባቢ ብቻ የሚበቅል ቲማቲም መሰል አትክልት አለ፡፡ ስሙም “ጸብሒ አቡን” ይባላል፡፡ የአቡን ወጥ እንደማለት
ነው፡፡
Wednesday, September 26, 2012
መስቀል ኃይላችን ነው
ከጌታችን ስቅለት በፊት መስቀል መቅጫ ነበር፡፡ ሰውን በመስቀል መስቀል የጀመሩት ፋርሳውያን ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች “ኦርሙዝድ” የሚባል የመሬት አምላክ ስለበራቸው እርሱን ላለማርከስ ብለው ወንጀለኛውን ሁሉ ከመሬት ከፍ አድርገው ሰቅለው ይቀጡት ነበር፡፡ በኋላም ይህ አድራጎት በሮማውያን ግዛት ሁሉ ሕግ ሆነ፡፡
በኦሪቱ ሥርዓትም በመስቀል የሚቀጡ ርጉማን ውጉዛን ነበሩ፡፡ ከጌታችን ስቅለት በኋላ ግን የነጻነታችን አርማ የድል ምልክታችን ሆነ፡፡ ክርስቶስ ይህን መስቀል ዙፋኑ አድርጎ ሰላምን እኩልነትን አድርጓልና፡፡ ስለዚህ ካሉን ነገሮች ሁሉ መስቀል የላቀ ክብር አለው፡፡
በኦሪቱ ሥርዓትም በመስቀል የሚቀጡ ርጉማን ውጉዛን ነበሩ፡፡ ከጌታችን ስቅለት በኋላ ግን የነጻነታችን አርማ የድል ምልክታችን ሆነ፡፡ ክርስቶስ ይህን መስቀል ዙፋኑ አድርጎ ሰላምን እኩልነትን አድርጓልና፡፡ ስለዚህ ካሉን ነገሮች ሁሉ መስቀል የላቀ ክብር አለው፡፡
Monday, September 24, 2012
MESKEL IN ETHIOPIA
In The Name of The Father, The Son;
& The Holy Spirit One God Amen!!
The word Meskel has two meanings.
One literal meaning is the Holy Cross. The other meaning is the Feast of the
Holy Cross; an event which is annually celebrated in Ethiopia in commemoration
of the finding of the Holy Cross. The Holy Cross is very significant in the
Ethiopian Orthodox Tewahdo Church (EOTC). The founding father of EOTC hymn, St.
Yared, says in his composition hymn book ‘MERAF’ that the Holy Cross is above
everything else in the Church. He says ‘It saves us from our enemy; the devil.
It is true that the Holy Cross has saved the entire world.’
Wednesday, September 19, 2012
ምክረ አበው -ቁጥር ሦስት
1. ከዕለታት በአንድ ቀን አባ ፓምቦ
አባ እንጦንስን “ማድረግ ያለብኝ ነገር ምንድነው?” ብሎ ይጠይቋል፡፡ አባ እንጦንስም እንዲህ ሲል መለሰለት “በራስህ ጽድቅ
አትታመን፤ ላለፈው አትጨነቅ፤ ይልቁኑ አንደበትህንና ሆድህን ግዛ፡፡”
2. አባ እንጦንስ በአንድ ወቅት
እንዲህ አለ፡- “በዚህች ምድር ላይ ስንኖር ሕይወታችንንም ሆነ ሞታችን ከባልንጀራችን ጋር ነው፡፡ ወንድማችንን ገንዘብ ካደረግነው
እግዚአብሔርን ገንዘብ እናደርጓለን፤ ወንድማችንን ካስቀየምነው ግን በክርስቶስ ላይ ኃጢአትን እንሠራለን፡፡”
Sunday, September 16, 2012
እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ
የዮሐንስ ወንጌል የ37ኛ ሳምንት ጥናት (ዮሐ.8፡12-20)
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
በምንዝር በያዝዋት ሴት ላይ ለመፍረድ ተሰብስበው የነበሩት አይሁድ ፈሪሳውያን ጌታችን “ጸሐፍት ፈሪሳውያን ሆይ! ኃጢአታችሁ ከዚህች ሴት ኃጢአት የባሰ እንደሆነ ተመልከቱ፡፡ ታውቁት ትረዱት ዘንድም አሁን ሕሊናችሁን መርምሩ፡፡ ስለዚህ እናንተው ራሳችሁ ወንጀለኞች ሳላችሁ በዚህች ሴት ላይ የምትፈርዱ አትሁኑ፡፡ ይልቁንም እርሷን ከመውቀሳችሁና ከመክሰሳችሁ በፊት ራሳችሁን የምትወቅሱ ሁኑ፡፡ እርሷ ተወግራ እንድትገደል የምትፈርዱ ከሆነ ግን እናንተም ከዚያ ነጻ አይደላችሁም” ብሏቸው እነርሱም ይህን ዘለፋ
በሰሙ ጊዜ ሕሊናቸው ወቅሷቸው በፊት ከገቡት ጀምሮ በኋላ እስከ ገቡት ድረስ አንድ አንድ እያሉ እየወጡ ሄደው ነበር /ቁ.9/፡፡(በዚህ ርእስ ላይ ይህን ይመልከቱ እኔም
አልፈርድብሽም-
የዮሐንስ
ወንጌል
የ36ኛ
ሳምንት
ጥናት(8፡1-11)
ሆኖም ግን ተመልሰው መጡ፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ቂመኛ አይደለምና ዳግመኛ አስተማራቸው፡፡ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት
ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም” ብሎ ተናገራቸው /ቁ.12/፡፡ እንዴት ያለ ፍቅር ነው? እንደምን ያለ መውደድ ነው?
ፍቁራን ሆይ! የጌታን ንግግር ታስተውሉታላችሁን? እንዲህ ማለቱ ነበር፡-“ፈሪሳውያን
ሆይ! እናንተ በመጻሕፍተ ኦሪት የዘለዓለም ሕይወት እንዳለችሁ ይመስላችኋል፤ እነርሱንም ትመረምራላችሁ፡፡ እነርሱ ግን ስለ እኔ
የሚመሰክሩ ናቸው /ዮሐ.5፡39/፡፡ እንግዲያውስ ወደ እኔ ኑ እንጂ በዚያ የምትቀሩ አትሁኑ! ዳዊት ‘የሕይወት ምንጭ ከአንተ
ዘንድ ነውና በብርሃንህ ብርሃንን እናያለን’ እንዳለ /መዝ.36፡6/ የሕይወት ምንጭ እኔ ነኝና ወደ እኔ ቅረቡ እንጂ በጨለማ
የምትቆዩ አትሁኑ፡፡ እውነተኛው ብርሃን እኔ ነኝና ወደ ብርሃን (ወደ እኔ) ኑ! በጨለማ ላለ ሰው ብርሃን ያስፈልጓል፡፡
የተጠማ ሰውም የሚያረካ መጠጥ ያስፈልጓል፡፡ እንግዲያውስ የእነዚህ ምንጫቸው እኔ ነኝና ታገኝዋቸው ዘንድ ወደ እኔ ቅረቡ
(በእኔ እመኑ)፡፡ ከእናንተ መካከል አንዱ በሌሊት ውኃ ቢጠማው ተነሥቶ ኩራዝን የማያበራ ማን ነው? ኩራዙንም ተጠቅሞ ውኃ
ቀድቶ የሚጠጣ አይደለምን? እንግዲያውስ እናንተም በብርሃኔ ብርሃን የሆንኩትን እኔን ያዙና ዳግመኛ ጽምዓ ነፍሰን የማያስጠማ
የሕይወትን ውኃ ጠጡ፡፡ ልጆቼ ሆይ! በጨለማ (በድንቁርና) መኖርን ስለምን ትመርጣላችሁ? እናንተን እንዲሁ አፍቅሬ አማናዊው
ብርሃን የምሆን እኔ ወደ እናንተ ስመጣ ስለምን ዐይነ ልቡናችሁን በመዝጋት እኔን ከማየት ትከለከላላችሁ? አባቶቻችሁ ከምድረ
ግብጽ ለመውጣት ፊት ለፊት የሚመራቸውን ዓምደ ብርሃንን ተከትለው ከባርነት የወጡ አይደሉምን? /ዘጸ.13፡21/ እንግዲያውስ
እናንተም ወደ እውነተኛው ሀገራችሁ (ወደ ገነት መንግሥተ ሰማያት) ለመግባት ብርሃን እኔን ተከተሉ፡፡ እኔ የፍልስጥኤም ወይም
የገሊላ ወይም ደግሞ የይሁዳ ብቻ ሳልሆን የዓለም ሁሉ ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ(የሚያምንብኝ) ቢኖር የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል፡፡
ክብርን፣ ዕውቀትን፣ መንግሥተ ሰማያትን ያገኛል እንጂ በሐሳር፣ በጨለማ ፣ በገሃነም አይመላለስም፡፡ የሚከተለኝ ቢኖር
በሴሰኛይቱ ሴት እንዳደረጋችሁት ሳይሆን በራሱ ኃጢአት ላይ ስለሚፈርድ በእኔ አምኖ ይኖራል፡፡ ወደ ክሕደት፣ ወደ ገሃነም፣
በሌሎች ላይ ወደ መፍረድ፣ ወደ ክፉ ነገር አይሄድም፡፡ የሕይወትን ውኃ ክብረ መንግሥተ ሰማያትን ታገኛል፡፡ ስለዚህ በእኔ
እመኑና ከስሕተት ከክሕደት ውጡ” /St. Cyril of Alexandria on the Gospel of John, 5:2/፡፡
ፈሪሳውያን ግን ይህን ፍቅር ከመረዳት ራቁ፡፡ መድኅን የሆነው ስሙ ከፍ ከፍ ይበልና አፍቃሪያቸውን
እንደ “ዕሩቅ ብእሲ” አይተዉት “የሌለውን አምላክነት” ለራሱ የወሰደ መሰላቸው፡፡ ስለዚህ፡- “አንተ ስለ ራስህ ትመሰክራለህን?”
ራስህን የምታመሰግን፣ ራስህንም የምታደንቅ ከሆነማ… አሉት፡፡ ሐሰት የባሕርይው ያይደለ አምላክ “ምስክርነትህ (የምትናገረው ሁሉ)
እውነት አይደለም” አሉት /ቁ.13/። የሚደንቀው ግን
Wednesday, September 12, 2012
ዜና ሐዋርያት
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
መንደርደርያ ይሆነን ዘንድ እስከ አሁን ባቀረብናቸው ሁለት ክፍሎች (እነዚያን ለማንበብ ይህን ይጫኑ http://mekrez.blogspot.com/2012/08/blog-post_7538.html) ክርስቲያኖች ለባሴ ክርስቶስ (ክርስቶስን የለበሱ)፣ ዘላለማዊ ሕይወትን የያዙ ማለት እንደሆኑና ቅዱሳን ደግሞ ዘላለማዊ በሆነ በክርስቶስ ከፍተኛ የቅድስና ደረጃ ላይ የደረሱ፣ ሞት የማይሠለጥንባቸው ፍጹማን ክርስቲያኖች፣ ሁለንተናዊ ሕይወታቸው በክርስቶስ የሆነ እንደሆኑ ተመልክተናል። ከዚህ በተጨማሪ እኛም እንደ እነርሱ እውነተኞች የተግባር ክርስቲያኖች ለመሆንና በክርስቶስ በሕይወት ለመኖር የቅዱሳንን ሕይወትና ታሪክ ማጥናትና እነርሱን ለመምሰል መጣጣር መተኪያ የሌለው ጉዳይ እንደሆነ ተመልክተናል። እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በሚቀጥሉት ጊዜያት ከቅዱሳን ሐዋርያት ጀምሮ በየዘመናቱ የተነሡ ቅዱሳንን ታሪክ እናቀርባለን። ለዛሬ የቅዱሳን ሐዋርያትን ታሪክ መግቢያ እነሆ!
ነቢያትን ትንቢት ያናገረ አምላክ፣ ወልደ አብ ወልደ ማርያም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ሰው ሆኖ ከኃጢአት በስተቀር የሰውን ሥራ በመሥራት አደገ፡፡ በሠላሳ ዓመቱም በባርያው በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ፡፡ በገዳመ ቆሮንቶስ ፵ መዓልትና ፵ ሌሊት ጾመ፤ ተራበ፤ ተጠማ፤ በዲያብሎስ ተፈተነ፡፡ ከዚህም በኋላ ወንጌለ መንግሥቱን ማስተማር ጀመረ፡፡ በሚያስተምርበት ወቅትም ለተለያዩ ዓላማዎች ብዙ ሕዝብ (፭ ገበያ ያህል) ይከተሉት ነበር። ግማሹ “ይሤኒ ላህዩ እምውሉደ ዕጓለ እመሕያው- መልኩ ከሰው ልጆች ሁሉ ያምራል” እንዲል /መዝ.45፡2/ መልኩን ለማየት፤ ግማሹ በአምስት እንጀራና በሁለት ዓሣ አምስት ሺህ ሕዝብ ሲመግብ አይተው /ማቴ. 14፡16/ ሕብስት አበርክቶ ይመግበናል ብለው፤ ግማሹ ልዩ ልዩ ደዌ ያደረባቸውን ሰዎች በተአምራት ይፈውስ ነበርና ከበሽታቸው ለመፈወስ ይከተሉት ነበር /ማቴ.4፡23/። ጌታችንም ከዚህ ሁሉ ሕዝብ መካከል መቶ ሃያ ቤተሰቦችን መረጠ። ምክንያቱ ደግሞ እነርሱ ከዋለበት እየዋሉ ካደረበት እያደሩ ትምህርቱን ሰምተው ተአምራቱን አይተው በሚገባ የሚከታተሉ “ቀለም” ተማሪዎች ስለነበሩ ነው። ከእነዚህም ውስጥ አስቀድመው የተመረጡት ቅዱሳን ሐዋርያት ሲሆኑ (እርሱም ጸጋን ሰጠ፤ ከቤተሰቦቹም ሐዋርያትን፣ ከእነርሱም ነብያትንና የወንጌል ሰባኪዎችን ጠባቂዎችንና መምህራንን ሾመ። ኤፌ. ፬፣፲፬) በኋላ ፸፪ቱ አርድእት (ከዚህም በኋላ ሌሎች ሰባ ሰዎችን መረጠ ሉቃ. ፲፣፩) ቀጥሎ ደግሞ ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት ተመርጠዋል። ፲፪ + ፸፪ + ፴፮ = ፻፳ ፤ መቶ ሃያ ቤተሰብ የሚባሉ እነዚህ ናቸው።
ሐዋርያ የሚለው ቃል “ሖረ” ከሚለው የግዕዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም “ለማስተማር የተላከ” ማለት ነው፡፡ የአሥራ ሁለቱም ሐዋርያት ስም፡- ጴጥሮስ፣ እንድርያስ፣ ያዕቆብ፣ ዮሐንስ፣ ፊሊጶስ፣ በርተለሜዎስ፣ ቶማስ፣ ማቴዎስ፣ ያዕቆብ ወልድ እልፍዮስ፣ ታዴዎስ የተባለ ልብድዮስ፣ ስምዖን ቀኖናዊ እንዲሁም የአስቆሮቱ ይሁዳ ናቸው /ማቴ.10፡1-4/፡፡ አባቶቻችን ቅዱሳን ሐዋርያት ምንም እንኳን ትውልዳቸው ከ፲፪ቱ ነገደ እስራኤል ቢሆንም የተመረጡት ግን በጌትነት ከሚኖሩ ከመሳፍንትና ከመኳንንት ወይም ከባለጸጎች ወገን ሳይሆን ከድሆች (ብዙዎች ሐዋርያት ዓሣ አጥማጆች ነበሩ)፣ ካልተማሩትና በአጠቃላይ በኅብረተሰቡ ዘንድ ዝቅተኛ ስፍራ ከሚሰጣቸው ወገኖች ነበሩ። የዚህም ምክንያት ሐዋርያው “ወንድሞቻችን! እንግዲህ እንዴት እንደተጠራችሁ እዩ፤ በሥጋ እጅግ ብዙዎች ዐዋቂዎች አይደላችሁምና፤ ብዙዎች ኃያላንም አይደላችሁምና፤ በዘመድም ብዙዎች ደጋጎች አይደላችሁምና። ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን ሊያሳፍር የዚህን ዓለም ሰነፎች መረጠ፤ ኃይለኞችንም ያሳፍር ዘንድ እግዚአብሔር የዚህን ዓለም ደካሞች መረጠ። አለን የሚሉትንም ያሳፍር ዘንድ ዘመድ የሌላቸውን የተናቁትን፤ ከቁጥርም ያልገቡትን እግዚአብሔር መረጠ” ብሎ እንደተናገረው ሰው በጥበቡና በኃይሉ በትውልዱም በእግዚአብሔር ፊት መመካት እንደማይገባው በተግባር ለማስገንዘብ ነው (፩ቆሮ. ፩፣፳፮- ፍጻሜ)።
ጌታችን እነዚህን መርጦ ሐዋርያት ብሎ ከሰየማቸው በኋላ (ከዕርገት በኋላ እርሱን ተክተው ሐዋርያት መደበኞች ሆነው አርድእት ደግሞ ሐዋርያትን እየረዱ የሚያስተምሩ ናቸውና!) ለጊዜው በምድረ እስራኤል ብቻ እንዲያስተምሩ ላካቸው፡፡ የዚህ ዓለም ወታደር ወደ ጦር ሜዳ ሲሄድ በቂ ስንቅና ትጥቅ እንደሚሰጠው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለቅዱሳን ሐዋርያት “በአሕዛብ መንገድ አትሂዱ ወደ ሳምራውያን ከተማም አትግቡ። ነገር ግን ከእስራኤል ወገን ወደ ጠፉት በጎች ሂዱ። ሄዳችሁም መንግሥተ ሰማያት ቀርባለች እያላችሁ አስተምሩ። ድውያንን ፈውሱ፤ ሙታንንም አንሡ፤ ለምጻሞችንም አንጹ፤ አጋንንትንም አውጡ፤ ያለዋጋ የተቀበላችሁትን ያለዋጋ ስጡ” ብሎ ድውይ የሚፈውሱበት፣ ሙት የሚያስነሡበት፣ ጋኔን የሚያወጡበት፣ ለምጽ የሚያነጹበት ሙሉ ትጥቅ ሰጣቸው፤ “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለች” እያሉ እንዲያስተምሩም ላካቸው /ማቴ. ፲፣፭ - ፰/። በተመሳሳይ ሁኔታ አርድእቱንም እንደላካቸው በሌላ ቦታ ተጽፎ እናገኛለን (ሉቃ. ፲)።
ከዚህም በተጨማሪ “እነሆ እንደበጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ እንግዲህ እንደእባብ ብልሆች እንድርግብም የዋሆች ሁኑ። ከክፉዎች ሰዎች ተጠበቁ፤ ወደ አደባባዮች አሳልፈው ይሰጧችኋልና፤ በምኩራቦቻቸውም ይገርፏችኋልና” እያለ ወደፊት በስሙ ሲያስተምሩ ዓለም እንደሚጠላቸውና መከራ እንደሚያመጣባቸው፤ ይህንንም መከራ እንዴት እንደሚያሸንፉት ከነመፍትሔው ነገራቸው /ማቴ. ፲፣፲፯ ፣ ዮሐ. ፲፭፣፲፰- ፳፭/።
ከዚህ በኋላ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፅንስ የጀመረውን የማዳን ሥራ በሞቱ በቀራንዮ ፈጸመው፡፡ ዓለምን አድኖም ፫ መዓልትና ፫ ሌሊት በከርሠ መቃብር አድሮ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ተነሣ። ከትንሣኤው በኋላ ለሐዋርያት በጉባኤም በተናጠልም (ለአንዱ ለሁለቱ) እየተገለጸ ፵ ቀን አስተማራቸው። በ፵ኛው ቀን ኃይል፣ ጽንዕ የሚሆናቸው መንፈስ ቅዱስን እንደሚልክላቸው ተስፋ ሰጥቷቸው እስካሁን ያዩትንና የሰሙትን እውነት ለዓለም እንዲመሰክሩ አዝዟቸው ዐረገ። ባረገ በ፲ኛው ቀንም የተናገረውን የማያስቀር ጌታ “ሁሉም መንፈስ ቅዱስን ተሞሉ፤ ይናገሩ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እንዳደላቸው መጠንም እየራሳቸው በሀገሩ ሁሉ ቋንቋ ይናገሩ ጀመሩ” እንዲል ጰራቅሊጦስን (መንፈስ ቅዱስን) ሰደደላቸው /ሐዋ. ፪ ፣ ፬/። ጰራቅሊጦስ ማለት በፅርእ ቋንቋ የሚያጽናና የሚያስደስት ማለት ነው፡፡
አባቶቻችን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ፸፪ ቋንቋ ተገልጦላቸው በዕውቀት ጐለመሱ፤ ከብልየት ታደሱ፤ ፈሪዎች የነበሩ መከራ ሥጋን የማይፈሩ ጥቡዐን ሆኑ። መዲናቸው ኢየሩሳሌምን በኅብረት ካስተማሩ በኋላ “ሑሩ ወመሀሩ- ሂዱና አስተምሩ” ያላቸውን ቃል በመጠበቅ ዓለምን በዕጣ ተከፋፍለው አርድእት ደግሞ ሐዋርያትን ተከትለው “አምላክ ከሰማያት ወረደ፤ በድንግልና ተፀንሶ በድንግልና ተወለደ፤ የምሥራችን አስተማረ፤ በአይሁድ እጅ ተገፈፈ ተገረፈ፤ በመስቀል ተሰቀለ፤ ሞተ፤ ተቀበረ፤ መቃብር ክፈቱልኝ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል በኃይሉና በሥልጣኑ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፤ በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ዳግመኛም ለፍርድ ይመጣል” ብለው ወንጌልን ለዓለም ሁሉ ሰበኩ፤ ለቤተ ክርስቲያን ሕግ አወጡ፤ ሥርዓት ደነገጉ፡፡ ነቢዩ ዳዊት “ውስተ ኵሉ ምድር ወጽአ ነገሮሙ ወእስከ አጽናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ” ትርጉሙም “ድምፃቸው ወደ ምድር ሁሉ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ” ብሎ የተናገረው ትንቢት ደረሰ፤ ተፈጸመ (መዝ. ፲፰ ፣ ፬)።
ጌታችን በተራራው ስብከቱ ላይ ሲያስተምራቸው “እናንተ የምድር ጨው፣ የዓለም ብርሃንና የተራራ ላይ መንደር ናችሁ” ብሏቸው ነበርና በትምህርታቸው በትሩፋታቸው አልጫውን ዓለም በሃይማኖትና በአምልኮተ እግዚአብሔር አጣፈጡት። በኃጢአት ጨለማ ውስጥ የነበረውን የሰው ልጅ በንጽሕናና በቅድስና ወንጌል ብርሃን አበሩት። በድንቁርና ዋሻ ተሰውሮ የነበረውን የአሕዛብን ልብ በዕውቀት ተራራ ላይ አውጥተው ለዓለም ሁሉ እንዲገለጥና እንዲታይ አደረጉት። ይህን ሁሉ ሲያደርጉ የሐዋርያዊ አገልግሎታቸው ዋነኛ መሣሪያዎች ጌታቸውና መምህራቸው እንዳዘዛቸው ጥበብ፣ ትዕግሥት፣ ፍቅርና የዋህነት ነበሩ። በዚህ ሁኔታ የተመረጡለትን ታላቅ አምላካዊ ዓላማ አሳኩ፡፡ በኋላም የጌታቸውን አርአያ ተከትለው ያላመኑ አይሁድና አሕዛብ እኩሉን በገመድ እያነቁ፣ እኩሉንም በደንጊያ እየወገሩ፣ እኩሉንም በሰይፍ እየመቱ በልዩ ልዩ ዓይነት ስቃይ እያሰቃዩ ገደልዋቸው፡፡ ሐዋርያትም ቁልቁል ተሰቅለው፣ በሰይፍ ተከልለው፣ እንደ በግ ተገፈው፣ በእሳት ተጠብሰው በድንጋይ ተወግረው ሰማዕትነትን ተቀብለው የመከራ ወንዝ የሆነ ይህን ዓለም ተሻገሩ፡፡ ሰውን ከሰው አላገናኝ ያለውን የቋንቋ፣ የጐሣ፣ የቅንዓትና የምቀኝነት ወንዝ ተሻግሮ እምነት፣ ተስፋ፣ ፍቅር ከሚገኝበት ከተማ የሚያደርሰውን ድልድይ ሠርተው ተልእኮአቸውን ጨረሱ፡፡ “የምሄድበት ጊዜዬ (ለሞት ዕድሜዬ) ደርሷል፡፡ መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ፤ ሩጫውን ጨርሻለሁ፤ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤ ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፤ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፤ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም” በማለት መስክረው አለፉ /፪ጢሞ.፬፡፮-፰/፡፡
ሐዋርያት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በአካል በዓይናቸው ያዩ፣ ቃሉን ከእግሩ ሥር ቁጭ ብለው የተማሩና በጆሮዎቻቸው የሰሙ፣ በእጃቸውም የዳሰሱት በአጠቃላይ ፫ ዓመት ከ፫ወር ሲያስተምር ከዋለበት እየዋሉ ካደረበት እያደሩ አብረውት የነበሩ፣ በኋላም ክርስቶስ በደሙ የመሠረታትን ቤተ ክርስቲያን አጥንታቸውን ከስክሰው፣ ደማቸውን አፍሰው፣ ሥጋቸውን ቆርሰው ስለገነቧት ቅድስት ቤተክርስቲያን ከፍተኛና ለየት ያለ ቦታ ትሰጣቸዋለች። ለመታሰቢያቸውም የቤተ ክርስቲያን ጣራ ፲፪ ዐምድ (ምሰሶ) እንዲኖረው ሊቃውንት ወስነዋል፡፡ ስለዚህ ሐዋርያት ከጌታችን ያዩትንና የሰሙትን ወንጌል ያስተላለፉ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ስለሆኑ የቤተክርስቲያን መሠረቶች ናቸው። ከእነርሱ አስተምህሮና ትውፊት የወጣች ቤተክርስቲያን ቤተክርስቲያን ልትባል አትችልም። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም “እናንተ ግን የእኛን ፍለጋ ተከተሉ፤ እናንተስ እኛም ብንሆን ወይም መልአክ ከሰማይ ወርዶ እኛ ካስተማርናችሁ ወንጌል ሌላ ቢሰብክላችሁ ውጉዝ ይሁን። አስቀድሜ እንዳልሁ አሁንም ደግሜ እላለሁ ካስተማርናችሁ ሌላ ትምህርት ያስተማራችሁ ቢኖር ውጉዝ ይሁን” በማለት ከሐዋርያት ትምህርት የሚወጣውን አስቀድሞ አውግዟል (ገላ. ፩፣ ፰ -፱)፡፡
እግዚአብሔር ቢፈቅድና ብንኖር በቀጣይ ጊዜ የእያንዳንዱን ሐዋርያ ታሪክና ሐዋርያዊ ጉዞ በተከታታይ ለማቅረብ እንሞክራለን። ለዚህም የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመ ብርሃን አማላጅነት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት በረከታቸውና ረድኤታቸው አይለየን አሜን!!
Subscribe to:
Posts (Atom)