Thursday, February 27, 2014

ዘወረደ ዘቀዳሚት ሰንበት



በዲ/ን ስመኘው ጌትዬ

(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ የካቲት 21 ቀን 2006 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ
ጸልዩ እምቅድመ ንባበ ዝንቱ ክርታስ

 እግዚአብሔር ሙላቱ ሁሉ በእርሱ እንዲኖር በእርሱም በኩል በመስቀሉ ደም ሰላምን አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዷልና፡፡ቆላ 1÷19-20 ይህ የመስቀሉ ደም ለደማውያኑም ለመንፈሣውያንም ፍጥረት ፍጹምና ዘለዓለማዊ ሰላምን ሰጥቷል፡፡ ታዲያ እኔም በማትከፈል ሦስትነት በአንድ ሕልውና በምትሆን በእግዚአብሔር ሰላምታ ዘለዓለማዊው ሰላም ይደረግልን ብዬ የአባቴን የቅዱስ ያሬድን የቀዳሚት ሰንበት ዘወረደ ጾመ ድጓ በጥቂቱ የተመረጡ ቃላት እነሆ፡፡

ዘወረደ ዘዐርብ



በዲ/ን ስመኘው ጌትዬ
 
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ የካቲት 21 ቀን፣ 2006 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ
ጸልዩ እምቅድመ ንባበ ዝንቱ ክርታስ 

 የጽዮን አምሳያ ለሆነችው ቤተክርስቲያን እንዲህ ይላል ቅዱስ አባት ዜመኛው ኢትዮጵያዊጎሕ ጎሐ ወኮነ ጽባሐ ንሳለማ ለጽዮን ምክሐ እምነ በሀ - ሌሊቱ ነጋ ጠዋትም ሆነ መመኪያችን እናታችን ጽዮን እንሳለማት፡፡” እኔም በቤተክርስቲያን ጡቶች ያደግሁ ከእርሷ በሚሆን ወተት ላደጉና ለኖሩ ምዕመናን እናታችን ለምትሆን ለቤተክርስቲያን ዜመኛው በሰጣት ሰላምታ የጽዮን ልጆች ሆይ ሰላም ለእናንተ ይሁን ሰላማችሁ ይብዛ፡፡ ትናንት በቅኔ ማሕሌት እንደተኛው ከበሮ (ከበሮ አገልግሎት በዚህ ወቅት አይሠጥም) ሳይሆን የድካም የሆነ ወዝ (ላብ) ከማይታይበት ከላይ ታች፣ ከግራ ቀኝ፣ ወደፊት ወደኋላ በሚለው መቋሚያ እየታገዝን ዜማውን በቤተክርስቲያን ስለቤተክርስቲያን ሠምተናል፡፡ ዛሬም እንዲሁ ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን (ጽዮን) እና ቅዱስ መስቀል በመሃልም መልካም ቃለ እግዚአብሔር እንሠማለን፣ የአባታችን አምላክ ከመላእክቱ ጋር ያሰልፈን፡፡

Wednesday, February 26, 2014

ዘወረደ ዘሐሙስ



በዲ/ን ስመኘው ጌትዬ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ የካቲት 19 ቀን 2006 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ ጸልዩ እምቅድመ ንባበ ዝንቱ ክርታስ

ወገኖቼ ዛሬ በሐሙስ ዜማችን በእኔ ሳይሆን .ያሬድ ዛሬ ብዙውን ስለሚወራላት ቤተ ክርስቲያ በሰጣት የጅማሬ ሰላምታ በሀክሙ እላችኋለሁ። ሰላመ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር የሆነ ደስ ያላችሁ ሆይ ደስ ይበላችሁ እላለሁ።

ትናንት በረቡዕ ድርሰቱ ራስን መመርመር፣ ጾምን፣ መገዛትን፣ ምስጋናን፣ መውደድን ፣ የተራበን ማጥገብን፣ ለድሃውም መፍረድን መልካም እንደሆን ነግሮን እነዚህን ሁሉ ደግሞ በጾም ወቅት ማድረጉ የበለጠ ተገቢ ነውና ጾማችንን አብረን ቀድሰን እንድንፈጽም በሰላም መንገድ እንድንጓዝ ብሎን ለዛሬ አቀብሎን ነበረ።

ዘወረደ ዘረቡዕ




በዲ/ን ስመኘው ጌትዬ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ የካቲት 18፣ 2006 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ ጸልዩ እምቅድመ ንባበ ዝንቱ ክርታስ

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን ። በክርስቶስ ወገኖቼ የሆናችሁ ተወዳጆች በትናንት የማክሰኞ ድርሰቱ አባታችን ቅዱስ ያሬድ በፍቅርና በትህትና እንጹም ብሎ ጀምሮ በጾም ከአለም ልቀን ከፍ ከፍ እንድንል መክሮ ሳይተወን ከፍ ከፍ ማለታችን ደግሞ ምድራዊ ሕዋሳቶቻችንን ሁሉ በማጾም እንደሰማያዊ እንድንሆን ነው ካለን በኋላ በመጨረሻም በክርስቶስ መርቆን ተለያየን። ዛሬ በዕለተ ረቡዕ የሚያዜመውን ከዝማሜው ጋር እንደወትሮው ነፍሳችን ትሰማው ዘንድ እየጸለይን እንቀጥላለን።

FeedBurner FeedCount