Thursday, August 16, 2012

የቅዱሳን ሕይወት- ክፍል ሁለት!


    በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
 በቅዱሳን  ሕይወት ውስጥ የምንመለከተው እኛን ለማዳን ሲል ሰው የሆነውን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ነው። የተቀደሰና ዘላለማዊ ሕይወትን ማግኘት የሚቻለው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ መልበስ፣ ሞትና ትንሣኤ ነውና። እርሱ የኛን ባሕርይ ባሕርይ አድርጎ ሞት ውላጤ የሚስማማው የነበረ ባሕርያችንን የማይሞት የማይጠፋ አደረገው። በገዛ ጥፋታችን ያመጣነውን የማይገፋ የነበረ ጠላታችን ሞትን በሥጋ ቀምሶ በልዩ ትንሣኤው አሸነፈልን። መድኃኒት የሆነ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን በኃጢአት በቆሰለ ሰውነታችን ላይ በመጨመር ከኃጢአታችን እንድንፈወስ፣ ከእርሱ ጋር አንድ እንድንሆን አደረገ። ይህን ሁሉ የማዳን ሥራ ከፈጸመ በኋላ ከዚህ በኋላ እኛ ደግሞ እርሱን እንድንመስል ምሳሌ ትቶልን እርሱ በሚሰጠን ይልና ጸጋ ሞትን (ሐጢአትን፣ ዓለምን) እንድናሸንፍ አዝዞን በክብር ወደ ሰማይ ረገ።ለዚህ ተጠርታችኋልና፤ ክርስቶስም እኮ ፍለጋውን ትከተሉ ዘንድ ምሳሌውን ሊተውላችሁ ስለእናንተ መከራን ተቀብሏል።” (፪ጴጥ.*፳፩)ከእኔም ተማሩ፤ እኔ የዋህ ነኝና፤ ልቤም ትሑት ነውናእንዲል (ማቴ.፲፩*፳፱)

 ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በዐይናቸው ዐይተው በጆሯቸው ሰምተው ይህን ያዩትንና የሰሙትን ለዓለም መሰከሩ።የእናንተ ግን ዐይኖቻችሁ ያያሉና፣ ጆሯችሁም ይሰማሉና ብፁዓት ናቸው። እውነት እውነት እላችኋለሁ ብዙዎች ነብያትና ጻድቃን እናንተ የምታዩትን ሊያዩ ተመኝተው አላዩም፣ እናንተ የምትሰሙትንም ሊሰሙ ተመኝተው አልሰሙምእንዲል (ማቴ.፲፫*፲፮ -፲፯ ) በብሉይ ኪዳን የነበሩ ነብያትና ቅዱሳን የክርስቶስን መምጣት ከሩቅ ሆነው በትንቢታቸው በእምነት ተመለከቱ እንጂ በዐይነ ሥጋ አላዩም፤ ዐረፍተ ዘመን ገትቶአቸዋልና። ቅዱሳን ሐዋርያት በእርሱ ቸርነት ለዚህ ክብር ተመረጡ። ይህንንም ያዩትንና የሰሙትን ለዓለም ሕዝብ በብቃት መሰከሩ፤ አስተላለፉ። ቅዱሳን ሐዋርያት ምስክርነታቸው በቃል በማስተማርና በተግባር ደግሞ በሥራ በማሳየት ነበር። ስለሆነም እንደዚህ ብለውደፍረውእስከመናገር ደረሱ፡-እኔ ክርስቶስን እንደምመስለው እኔን ምሰሉ” (፩ቆሮ.፲፩*) ቅዱሳን ደግሞ ይህንን የሐዋርያትን ሕይወት በመከተል ሐዋርያትን መስለውና አህለው ተነሥተዋል፤ ገናም እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ ይነሣሉ።

 ታዲያ የእነዚህን ቅዱሳን ሕይወት ማንበብና ማወቅ ለእኛ መንፈሳዊ ሕይወት ምን ዐይነት ፋይዳ አለውበቅዱሳን ሕይወትስ እንዴት መጠቀም እንችላለንከላይ እንደተመለከትነው የቅዱሳን ሕይወት ክርስቶስን የመልበስና በሁለንተናዊ ኑሮአቸው እርሱን የመምሰል ሕይወት ነው። ታዲያ እኛስ የምንፈልገው ይህንኑም አይደልበዚህ ረገድ ቅዱሳን በመከራ ተፈትነው ፈተናውን በሚገባ ያለፉና በድል ያሸነፉ በመሆናቸው በሕይወት ማደግ ለምንፈልግ ለኛ የተግባር ምህርት ቤቶች ናቸው። እነርሱ ፍጹማን ክርስቲያኖች ስለሆኑና ክርስቶስን ስለሚመስሉ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ (ወንጌልን) በመፈጸም መንፈሳዊ ፍሬ ያፈሩና እውነተኛ የወንጌል ገበሬዎቸ ናቸው። እነርሱ ወንጌልን በተግባር ኑረው ባያሳዩን ኖሮ በሰው የማትቻል ምናባዊ (ideal) ሕግ ሆና ትቀር ነበር። ስለዚህ ሕይወተ ቅዱሳን የወንጌል ተግባረ ዕድ (‘applied or practical’ ወንጌል) /ቤት ነው። ይህንንም የተለያዩ የቅዱሳን ገድላትን፣ ድርሳናትንና እንዲሁም ስንክሳርን ስናነብ የምንገነዘበው ነው። ይህንን ሐሳብ የሚያጠናክር አንድ አባት ሲያስተምሩ የሰማሁትን ላካፍላችሁ።
  • በሚሰድቧችሁና በሚያሳድዷችሁ ጊዜ፣ ስለእኔም እየዋሹ ክፉውን ሁሉ በሚናገሩባችሁ ጊዜ ብፁዓን ናችሁ። ደስ ይበላችሁ ሐሴትንም አድርጉ…” (ማቴ*፻፩-፻፪) ለዝርዝሩየሐዋርያት ሥራ :- “ሐዋርያትንም ጠርተው ገረፉአቸው እንግዲህ ወዲህም በኢየሱስ ስም እንዳያስተምሩ ገሥጸው ተዉአቸው። እነርሱም ከሸንጎው ፊት ደስ እያላቸው ወጡ”(*-፵፩)
  • ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ ለሚጠሏችሁም መልካም አድርጉ። የሚረግሟችሁንም መርቁአቸው፤ ለሚበድሏችሁም ጸልዩላቸው” (ሉቃ*፳፯-፳፰) ለዝርዝሩ የሐዋርያት ሥራ :-“ከከተማም ወደ ውጭ ጎትተው አውጥተው ወገሩት … በጉልበቱም ተንበርክኮ አቤቱ ይህን ኃጢኣት አትቁጠርባቸው ብሎ ጮኸ።” (ሐዋ.*)
  • አምላክህ እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ይልህ ውደደው” (ማቴ፳፪*፴፯) ለዝርዝሩ ወደ ሮሜ ሰዎች :- “ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ ነውንኀዘን ነውንስደት ነውንራብ ነውንመራቆት ነውንጭንቀት ነውንሾተል ነውን? ... ከክርስቶስ ፍቅር ሊለየን የሚችል የለም (ሮሜ. *፴፭)
  • እውነት እውነት እላችኋለሁ በእኔ የሚያምን እኔ የምሠራውን ሥራ እርሱም ይሠራል፤ ከዚያም የሚበልጥ ይሠራል።” (ዮሐ፲፬*፲፪) ለዝርዝሩ ገድለ ጊዮርጊስ፡፡
  • ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢገዛ ነፍሱንም ቢያጣ ለሰው ምን ይረባዋል?” (ማቴ፲፮*፳፯) ለዝርዝሩ የአባ ጳውሊ ታሪክን ይመልከቱ፡፡
  • . . .
 እኛም  እንደእነርሱ ተግባራዊ የወንጌል ሕይወትን ለመኖር ከሕይወታችው ለመጠቀም የሚከተሉትን ነጥቦች ተግባራዊ እናድርግ :-
. ቅዱሳንን  የሕይወታችን ምሳሌ ማድረግ :- ቅዱሳን በሙሉ በሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ቃል እንዲህ ይሉናል፡-እኔ ክርስቶስን እንደምመስለው እኔን ምሰሉ” (፩ቆሮ.፲፩*) እውነተኛና ተግባራዊ ሕይወትን እንዴት መኖር እንዳለብን ከሕይወታቸው መማርና ዘወትር እነርሱን ለመምሰል መታገል አለብን።
. ቅዱሳንን የቅርብ ወዳጆቻችን ማድረግና በጸሎታችን እርዳታቸውን መጠየቅ :- እኛ የምናምነው እምነት ቅዱሳን ያመኑትን ነው፤ ልንደርስበት የምንፈልገውም የቅድስና ሕይወት እነርሱ የኖሩትን ነው። ስለዚህ ቅዱሳን በእምነት ወንድሞቻችን እህቶቻችን ስለሆኑና ምንም እንኳ በሥጋ ቢለዩም በነፍስ ሕያዋን ስለሆኑ ብንጠራቸው ይሰሙናል፣ ይረዱናል። በቦታና በጊዜ ከማይወሰነው ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ስለሆኑ እነርሱም የጸጋ ምልአት (ያለመወሰን) ተሰጥቷቸዋል። ስለሆነም በየትኛውም ጊዜና ቦታ ሆነን ብንጠራቸው በረድኤታቸው ያግዙናል።
. ዜና ገድላቸውን ዘወትር ማንበብ:- ቅዱሳን ስለ ክርስቶስ ፍቅር ሰይጣንንና ዓለምን ከነኮተቱ አሸንፈው እንዴት ለክብር እንደበቁ ለማወቅና ከእነርሱ ልምድ ለመቅሰም ሁሌም ታሪካቸውን ገድላቸውን ማንበብ አለብን።
. ቅዱሳን ልክ እንደኛ ሰዎች እንደሆኑ ማሰብ:- ቅዱሳን ስለ ክርስቶስ ፍቅር ሕይወታቸውን የሠዉት፣ ዓለም በቃኝ ብለው በየበረሃው የዞሩት የተለዩ ፍጡሮች ስለሆኑ አይደለም። እነርሱም እንደኛው ሥጋን የለበሱ ፍጡራን ናቸው። እኛን የሚያምረን የሚያምራቸው፣ ለኛ የሚያጋ*ጥሙን መከራዎች በሙሉ ያጋጠሙአቸው (እንዲያውም በበለጠ) ናቸው። ነገር ግን በእምነታቸውና ለክርስቶስ ባላቸው ፅኑ ፍቅር ሁሉን ተፈትነው በመጨረሻ በድል አድራጊነት የቋጩ ስለሆነ ዘወትር ሕያው ምስክር ይሆኑናል።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ይቀጥላል!


ክፍል አንድን ለማበብ ይህን ይጫኑ
http://mekrez.blogspot.com/2012/08/blog-post.html

FeedBurner FeedCount