Pages
ቀዳሚ ገጽ
ቢመለከቷቸው ይጠቅማሉ
Labels
ልዩ ልዩ
ስብከት ወተግሳጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
በእንተ ቅዱሳን
ጥያቄና መልስ
ትምህርተ ሃይማኖት
ወቅታዊ
የጥበብ ትሩፋት
ክርስቲያናዊ ሕይወት
ነገረ ማርያም
ለሕፃናት
Friday, December 20, 2013
ነቢዩ ሚክያስ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ታኅሳስ ፲፪ ቀን፣ ፳፻፮ ዓ.ም.)፡-
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
“ሚክያስ” ማለት “መኑ ከመ እግዚአብሔር - እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው?” ማለት ነው፡፡ ይኸውም ተልእኮውን የሚያስረዳ ነው፡፡ ምክንያቱም መጽሐፉን ስናነብ የሚከተሉትን እንገነዘባለንና፡-
Read more »
Tuesday, December 17, 2013
ነቢዩ አሞጽ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ታኅሳስ ፱ ቀን፣ ፳፻፮ ዓ.ም.)፡-
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
“አሞጽ” ማለት “ሽክም፣ ጭነት” ማለት ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ በዚኽ ስም የሚጠሩ ሦስት ሰዎች ያሉ ሲኾን እነርሱም የነቢዩ ኢሳይያስ አባት /ኢሳ.፩፡፩/፣ የምናሴ ልጅ ንጉሥ አሞጽ /፪ኛ ነገ.፳፩፡፲፰/ እንዲኹም ለዛሬ የምናየውና ከደቂቀ ነቢያት አንዱ የኾነው ነቢዩ አሞጽ ናቸው፡፡
የቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት እንደሚያስረዳው የነቢዩ አሞጽ አባት ቴና ሲባል እናቱ ደግሞ ሜስታ ትባላለች፡፡ ነገዱም ከነገደ ስምዖን ወገን ነው፡፡
Read more »
Sunday, December 15, 2013
ነቢዩ ሆሴዕ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ታኅሳስ ፮ ቀን፣ ፳፻፮ ዓ.ም.)፡-
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
“ሆሴዕ” ማለት ከ፲፪ቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ ሲኾን የስሙም ትርጓሜ “መድኃኒት” ማለት ነው፡፡ መድኃኒት መባሉም እንደ ኢያሱ ወልደ ነዌ ባጭር ታጥቆ፥ ጋሻ ነጥቆ፥ ዘገር ነቅንቆ አማሌቃውያንን አጥፍቶ እስራኤልን አድኖ፥ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋዉን ቆርሶ፥ ደሙን አፍስሶ፥ ፲፫ቱን ሕማማተ መስቀል ታግሦ፥ አጋንንትን ድል ነስቶ ነፍሳትን አድኖ አይደለም፤ አባት እናቱ በትንቢቱ በትምህርቱ እንዲያድን አውቀው “ሆሴዕ - መድኃኒት” ብለዉታል እንጂ፡፡ ስለዚኽ የስሙ ትርጓሜ ተልእኮውን የሚያስረዳ ነው ማለት ነው፡፡
Read more »
Friday, December 13, 2013
ነቢዩ ዳንኤል
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ታኅሳስ ፬ ቀን፣ ፳፻፮ ዓ.ም.)፡-
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
“ዳንኤል” ከአራቱ ዐበይት ነቢያት አንዱ ሲኾን የስሙም ትርጓሜ “እግዚአብሔር ፈራጅ ነው” ማለት ነው፡፡ ይኸውም ተልእኮውን የሚገልጥ ነው፡፡ አፍአዊ በኾነ ትርጓሜ (Literally) ስንመለከተው እግዚአብሔር በነቢዩ ዳንኤል አድሮ በአሕዛብ ላይ እንደሚፈርድ፤ በአሕዛብ ላይ ብቻ ሳይኾን የዋሐንን በሚከስሱ ሰዎች ላይ እንደሚፈርድ፤ አንድም እግዚአብሔር ጨቋኙን ንጉሥ አጥፍቶ ወደ ምርኮ የኼዱት ኹለቱም ወገኖች ማለትም እስራኤልንና ይሁዳን ነፃ እንደሚያወጣቸው የሚያስረዳ ሲኾን፤ በምስጢራዊው መልኩ ግን የክብር ባለቤት ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዲያብሎስ ምርኮ የኼዱት ኹለቱም ወገኖች ማለትም ሕዝብም አሕዛብም ከኃጢአት ባርነት ነፃ አውጥቶ የክብርን ሸማ እንደሚያለብሳቸው/ሰን የሚያመለከት ነው፡፡
Read more »
Newer Posts
Older Posts
Home
Subscribe to:
Posts (Atom)
FeedBurner FeedCount