Wednesday, March 12, 2014

ምኩራብ ዘሐሙስ



በዲ/ን ስመኘው ጌትዬ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ መጋቢት 3 ቀን፣ 2006 ዓ.ም.)፡- በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ

 ጸልዩ እምቅድመ ንባበ ዝንቱ ክርታስ

 ከልዑላን ይልቅ ከፍ ከፍ በሚል፣ በቅዱሳን ዘንድ በሚቀደስ፣ በትጉሃንም በሚመሰገን፣ ከሀዲዎችን በዘለዐለማዊ ቀኝ ክንድ በሚገለባብጥ፣ አምኖ ስሙን ለሚጠራው የመትጋትን ኃይል በሚያደርግለት፣ አፍ ሁሉ አንደበትም ሁሉ በሚያመሰግነው፣ ጉልበትም ሁሉ በጊዜ እና በዘመናት ሁሉ በሚሰግድለት በእግዚአብሔር ስም ለዘለዓለሙ ሰላም ለእናንተ ይሁን (መጽሐፈ ምስጢር)፡፡

Tuesday, March 11, 2014

ምኩራብ ዘረቡዕ



በዲ/ን ስመኘው ጌትዬ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ መጋቢት 2 ቀን፣ 2006 ዓ.ም.)፡- በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ
 ጸልዩ እምቅድመ ንባበ ዝንቱ ክርታስ

 የሕልውናው መሠረት በማይገኝ፣ በቁጥርም በማይቆጠር፣ የፀሐይን ክበብ በነፋሳት ሠረገላ በሚከምር፣ የመብረቶች ብልጭታ ሲያበራ የነጎድጓድም ድምጽ ሲጮህ የዝናብ ጠብታዎችን ከደመናዎች ማህፀን የሚቀዳ፣ በሥሉስ ቅዱስ ስም በአንዲት ምክርና ንግግር አንድ በሆነ ሥላሴ ሰላም ለሁላችን ይሁን፡፡ ዛሬ አባታችን ቅዱሥ ያሬድ እንደ ትናንትና ባለ አዲስ ምሥጋና ነገም በሚያመሰግንበት በጎ ቃል ቤተክርስቲያንን እያወደሰ እኛን ያስተምረናል፡፡ ከሀያ አራቱ ካህናተ ሰማያት ጋር ያሰልፈን፡፡

Monday, March 10, 2014

ምኩራብ ዘሠሉስ



በዲ/ን ስመኘው ጌትዬ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ መጋቢት 1 ቀን፣ 2006 ዓ.ም.)፡- በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ

 ጸልዩ እምቅድመ ንባበ ዝንቱ ክርታስ

 ለመወለዱ ጥንት በሌለው፣ አስቀድሞ አለም ሳይፈጠር በመለኮቱ ከአብ በተወለደ፣ ዳግመኛም እኛን ለማዳን በዘመኑ እኩሌታ ከቅድስት ድንግል ማርያም በተወለደ በአንዱ የእግዚአብሔር ልጅ ስም እንደ ሐዋርያት ባለ ሰላምታ ሰላም ለእናንተ ይሁን፡፡ ዛሬም እንደሌሎች የፆም ቀን ለቤቱ ምስጋናን በከሚያቀርበው ኢትዮጵያዊ ሊቅ ጋር ጥቂት ቃላትን መርጠን በነፍስ ዜማ እንቆያለን፡፡

Sunday, March 9, 2014

ምኩራብ ዘሰኑይ



በዲ/ን ስመኘው ጌትዬ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ የካቲት 30 ቀን፣ 2006 ዓ.ም.)፡- በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ
ጸልዩ እምቅድመ ንባበ ዝንቱ ክርታስ
የከይሲን ምክር አጥፍተህ፣ መርዙንም ነቅለህ፣ አስቀድሞ አጥተነው የነበረውን ልጅነታችንን እና መኖሪያችንን በደምህ ንጽሕት ባደረካት ቤተክርስቲያን ተክተህ የሰጠኸን፣ የምኩራብን መስዋእት ሽረህ አማናዊው መስዋእት የሆንከን፣ የድኅነታችን ወደብ በሆንከው በአንተ ሠላማችን ይብዛ፡፡ ሰላም ለሁላችሁ ይሁን!!!
በዚህች የሳምንቱ መጀመሪያ የሥራ ቀን ከእረፍታችን ስንፍና በጠዋት ተነስተን ከቅዱስ ያሬድ ጋር ምስጋናችንን በተመረጡ ጥቂት ቃላት እንጀምራለን፡፡

FeedBurner FeedCount