Wednesday, July 9, 2014

ለመቅረዝ ዘተዋሕዶ ድረ ገጽ ወዳጆች

(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሐምሌ ፪ ቀን፣ ፳፻፮ ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!



መቅረዝ ዘተዋሕዶ መንፈሳዊት ድረ ገጽ አድራሻ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህሕዶን እምነት ሥርዓት ትውፊትና ታሪክ መሠረት ያደረጉ ትምህርታዊ የኾኑ ጽሑፎች በአራት በተለያዩ ቋንቋዎች ላለፉት ዓመታት ወጥተዋል፡፡ እነዚኽ ትምህርቶች በሀገር ውስጥም ኾነ ከሀገር ውጪ የኢንተርኔት አቅርቦት ላላቸው ምዕመናን በተቻለ መጠን ለማድረስ ተሞክሯል፡፡ ነገር ግን እነዚኽን መንፈሳውያን ጽሑፎች በዓቅም ማነስ ምክንያት ቴክኖሎጂውን መጠቀም ላልቻሉ  ምዕመናን ሊዳረሱ አልቻሉም፡፡

Friday, June 20, 2014

“መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል” 1 ጢሞ. 6፣16



በቀሲስ ጥላሁን ታደሰ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሰኔ 13 ቀን፣ 2006 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለመንፈስ ልጁ ጢሞቴዎስ በላከለት የመጀመሪያው መልእክት ማጠቃለያ ላይ የምናገኘው ኃይለ ቃል ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስይህንን መልእክት ከአቴና በደቀ መዝሙሩ በቲቶ በኩል ልኮለታል፡፡ ይሄንን የመጀመሪያ መልእክት ቅዱስ ጳውሎስ ወደ መቄዶንያ በሔደጊዜ፤ ደቀ መዝሙሩ ጢሞቴዎስን በሃገረ ኤፌሶን ትቶት ሔዶ ነበር፡፡ በዚያ ቆይታው ስለ መንፈሳዊ አገልግሎቱና /እርሱም/ በመንፈሳዊሕይወቱ ሊፈጽማቸው ስለሚገቡ ጉዳዮች ሊያስረዳው ጽፎለታል፡፡

Monday, June 9, 2014

ጾምን ቀድሱ

(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሰኔ ፪ ቀን፥ ፳፻፮ ዓ.ም.)፡-  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
 የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ. ምእመን ኾኖ ስለ ጾም ምንነትና አስፈላጊነት የማያውቅ አለ ማለት አይቻልም፡፡ ከ፯ ዓመታችን አንሥተን አብዛኞቻችን ከጾም ጋር ተዋውቀናልና፡፡ ጾም የሥጋን ምኞት እንደምታጠፋ፣ የነፍስን ቁስል እንደምትፈውስ፣ ጽሙናንና ርጋታን እንደምታስተምር፣ ከእንስሳዊ ግብር እንደምትጠብቅ፣ ሰውን መልአክ ዘበምድር አድርጋ መንፈሳዊ ኃይልን እንደምታስታጥቅ አብዛኞቻችን ተምረነዋል፤ በቃላችንም እናውቀዋለን፡፡ ነገር ግን በተግባር እግዚአብሔር እንደወደደው የሚጾሙት እጅግ ጥቂቶች መኾናቸው በጣም አሳዛኝ ነው፡፡ ብዙዎቻችን የሥጋ ፈቃዳችንን ሳንተው “ስለምንጾም” በሕይወታችን ለውጥ አይታይብንም፡፡

Saturday, June 7, 2014

በዓለ ጰራቅሊጦስ



(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፥ ግንቦት ፴ ቀን፥ ፳፻፮ ዓ.ም)፡ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
  “ጰራቅሊጦስ” ማለት በጽርዕ ልሳን “አጽናኝ” ማለት ነው፡፡ ምንም እንኳን በ፩ኛ ዮሐ.፪፡፩ ላይ ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ተጠቅሶ ብናገኘውም፥ አብዛኛውን ጊዜ ግን ከሦስቱ አካላተ ሥላሴ አንዱ ለሚኾን ለመንፈስ ቅዱስ የሚሰጥ ስያሜ ነው /ዮሐ.፲፬፡፲፮/፡፡ ይኸውም የመንፈስ ቅዱስን ግብር የሚገልጥ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ በበዓለ ኃምሳ ቤተ ክርስቲያንን በአሚነ ሥላሴ አጽንቶ ዓለምንም ኹሉ ወደ እውነት እንዲመራት መውረዱን የሚያመለክት ነው፡፡

FeedBurner FeedCount