Saturday, August 30, 2014

አዲሱ ዓመት - ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው (ክፍል ፩)



(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ነሐሴ ፳፬ ቀን፣ ፳፻፮ ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
 የምወዳችኁ ልጆቼ! አዲሱ ዓመት የደስታ የሰላምና የጤና እንዲኾንላችኁ ትሻላችሁን? እንኪያስ ገና ከዥመሩ በስካር፣ በዘፈን፣ በገቢረ ኀጢአት ለማሳለፍ አታቅዱ፡፡ የአዲሱ ዓመት የመዠመሪያውን ዕለት ብቻ ሳይኾን እያንዳንዱን ቀን በገቢረ ኀጢአት አትዠምሩት፡፡ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ፣ ምግባር ትሩፋት በመሥራት አሐዱ በሉ እንጂ፡፡ ዕለታት ክፉዎች ወይም ጥሩዎች የሚኾኑት በተፈጥሮአቸው እንደዚያ ኾነው አይደለም፡፡ ዕለቱን ክፉ ወይም ደግ እንዲኾን የምናደርገው እኛው ነን፡፡ የአምናው ማግሰኞ ከዘንድሮ ማግሰኞ የተለየ አይደለም፡፡ የተለየ የሚያደርገው የእኛ ብርታት ወይም ስንፍና ብቻ ነው፡፡

Tuesday, August 12, 2014

ማርያም ፊደል

(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ነሐሴ ፯ ቀን፣ ፳፻፮ ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
 እንኳን ለዓለም ኹሉ ደስታን ወዳመጣችው ዕለት አደረሳችኁ፤ አደረሰን፡፡ ነሐሴ ሰባት ቀን የባሕርያችን መመኪያ የምትኾን ንጽሕተ ንጹሐን፥ ቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተፀነሰችበት ዕለት ነው፡፡ ይኽቺን ዕለት ያልናፈቀ ትውልድ የለም፡፡ ጽድቃቸው እንደ መርገም ጨርቅ ለኾነባቸው ቅዱሳን አበው ወእማት ተስፋቸው የሚፈጸመው በዛሬው ዕለት በተጸነሰችው በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ነውና፡፡ ቅድስትና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያናችንም ከእግዚአብሔር ቀጥሎ እንደ እመቤታችን ከፍ ከፍ የምታደርገው ፍጥረት የሌለው ስለዚኹ ነው፡፡ ሊቃውንቱ፡- “ሐና አንቺን የጸነሰችበት የደስታ ቀን ምን ያኽል የተባረከች የተቀደሰች ቀን ናት፤ ሟች ኢያቄምም ለሕይወት አንቺን  ያፈራባት ቀን ምን ያኽል የተባረከች የተቀደሰች ቀን ናት፤” ብለው የሚዘምሩላትም ይኽን ምሥጢር በልቡናቸው ቋጥረው ነው /አባ ጽጌ ድንግል፤ ማኅሌተ ጽጌ ቁ.፵፬/፡፡

Monday, August 4, 2014

መቅረዝ ዘተዋሕዶ - የውዳሴ ማብራርያ መጽሐፍ በገበያ ላይ ዋለች



መቅረዝ ዘተዋሕዶ ከዚኽ በፊት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ባዘጋጁት የትርጓሜ መጽሐፍ ተተንተርሳ የተዘጋጀች መጽሐፍ ስትኾን የምትለየውም፡-
፩ኛ) የጥንቱን ለዛ ሳትለቅ ቀለል ባለ አቀራረብና ይዘት በእያንዳንዱ ምዕመን እጅ እንድትደርስ በማሰብመዘጋጀቷ፤
፪ኛ) “እንዲል፣ እንዳለ፣ እንዲሉየሚለውን ጥንታዊ አቀማመጥ ጸሐፊውንና ደራሲውንመለየቷ፤
፫ኛ) አንዳንድ ተጨማሪ ማብራርያ የሚያስፈልጋቸውን ምንባባት ከተለያዩ ድርሳናት ተጨማሪ ማብራሪያመያዟ፤
፬ኛ) የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ በሚያስፈልጋቸው ቦታዎች ላይ ጥቅሱን በማስቀመጥ ምዕመናን እንዲያመሳክሩት መንገድመክፈቷ ነው፡፡

Sunday, August 3, 2014

ፍልሰታ


(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሐምሌ ፳፯ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ተዋዳጆች ሆይ!  ዛሬ የምንማማረው በእንተ ፍልሰታ ለማርያም አይደለም፡፡ ስለ ራሳችን ፍልሰታ እንጂ፡፡ ኹላችንም ስለ እመቤታችን ፍልሰታ የመናገር ችግር የለብንም፡፡ ዛሬ እንድንማማርና እንድንወቃቀስ የፈለግኹት በሕይወታችን ከግብርናተ ዲያብሎስ ወደ ክርስቶስ ሳንፈልስ (ሳንሻገር) የእመቤታችንን ፍልሰታ ብቻ ለምናከብር ለየኔ ቢጤዎች ነው፡፡

FeedBurner FeedCount