Friday, September 19, 2014
Monday, September 15, 2014
የትምህርተ ሃይማኖት መግቢያ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ መስከረም 5 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡-
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
“ሃይማኖት” ማለት አምነ፣ አመነ ከሚል የግእዝ ግሥ የወጣ ሲኾን መዝገበ ቃላታዊ ትርጓሜውም “ማመን፣ መታመን” ማለት ነው፡፡ በምሥጢራዊው ትርጕሙ ግን “ሃይማኖት” ማለት ፍጥረትን ኹሉ ካለ መኖር ወደ መኖር ያመጣ አንድ እግዚአብሔር እንዳለ፣ ለሚታየውም ለማይታየውም ፍጥረት ሠራዒውና መጋቢው ርሱ ብቻ እንደኾነ፣ ልዩ ሦስትነት እንዳለው፣ በዚኽ አለ በዚኽ የለም የማይባል ምሉዕ በኵለሄ እንደኾነ፣ … ማመን መታመን ማለት ነው፡፡
Tuesday, September 9, 2014
ዘመኔን አድሰው
በወርቅነሽ ቱፋ
ይኸው…
ሩቅ ያልኩት ቀረበ፥ ነገ ዛሬ ሊኾን፥ መጣ እየበረረ፤
በለስ ሕይወቴም ሲፈተሸ፥ ምንም አላፈራ፥ አላዘረዘረ፡፡
Sunday, September 7, 2014
አዲሱ ዓመት - ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው (የመጨረሻው ክፍል - ክፍል ፬)
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ጳጉሜ ፪ ቀን፣
፳፻፮ ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
የቀጠለ…
እግዚአብሔር
የሚወዳችኁ እናንተም የሚምትወዱት ልጆቼ! ይኽን ኹሉ በዝርዝር የምነግራችኁ ለምን ይመስላችኋል? ይኽን ኹሉ በዝርዝር መናገሬ
በዘዴ ኹላችንም የምናደርገውን ማናቸውም እንቅስቃሴያችን ለእግዚአብሔር ክብር እናደርገው ዘንድ ስለምሻ ነው፡፡ በባሕር የሚነግዱ
ነጋዴዎች ንብረታቸውን ወደ ከተማ ዳር መልሕቅ ካመጡ በኋላ መዠመሪያ የሚያደርጉት ነገር ቢኖር በቀጥታ ወደ ገበያ ሥፍራ መሔድ
አይደለም፡፡ ወደ ገበያ ሥፍራ ከመሔዳቸው በፊት ስለ ትርፋቸው ያስባሉ እንጂ፡፡ እኛም በምናደርገው ኹሉ ከእግዚአብሔር ዘንድ የምናገኘውን
ጥቅም ማሰብ አለብን፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)