Monday, December 15, 2014

የንስሐ ልጆቼን እንዴት ላገልግል? (3)

በዳዊት አብርሃም
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ማግሰኞ ታኅሳስ 7 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
የጽሑፉ ምንጭ፡- ሐመር መጽሔት፥ የግንቦት 2005 ዓ.ም. እትም ነው፡፡
ወጣቶችን ለንስሐ መጥራት
ለንስሐ አባትና ልጅ ግንኙነት እንደ አንድ ተግዳሮት እየኾነ ያለው ነገር የትውልድ ክፍተትና የባሕል ልዩነት ነው፡፡ በተለይ በከተሞች ውስጥ የሚኖሩ ወጣቶችን ዘመን አመጣሽ ችግሮች ተገንዝቦ መፍትሔ መስጠት በዕድሜ ከፍ ላሉትና ከገጠሩ አከባቢ ለመጡት ካህናት አስቸጋሪ ነው፡፡
 ቀሲስ ፋሲል ታደሰ ሌሎች ችግሮችንም ያወሳሉ፡- “የንስሐ ልጆች ከአባቶች ጋር ተገናኝተው ለመወያየት አመቺ ቦታም የሚጠፋበት ጊዜ አለ፡፡ ብዙ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን አፀድ ስር እየተገናኘን ለመነጋገር ብንሞክርም በጕባኤ ሰዓት ወይም በሌሎች የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ሰዓት መወያየት ከባድ ይኾናል፡፡”
 ለዚኽ ችግር እንደ መፍትሔ ቢኾን ብለው ቀሲስ ፋሲል አንዲት ቢሮ ከፍተዋል፡፡ አራዳ ጊዮርጊስ አከባቢ የምትገኘው ቢሯቸው (በአኹኑ ሰዓት 5 ኪሎ በማኅበረ ቅዱሳን ሕንፃ ውስጥ ነው) በመጠን አነስተኛ ብትኾንም በውስጧ በርካታ መጻሕፍትን የያዘች ናት፡፡ ቀሲስ ስለዚኽ ነገር ሲያስረዱ፡- “ተነሳሕያኑ ምክር ከተቀበሉ በኋላ ስለ ሃይማኖታቸውም ኾነ ስለ ግል መንፈሳዊ ሕይወታቸው ዕውቀታቸው እንዲዳብር የተመረጡ መጻሕፍትን አውሳቸዋለኹ፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን የንባብ ፍቅር ስለሚያድርባቸው ራሳቸው እየገዙ ማንበብ ይዠምራሉ፤ እንዲያውም ለእኛ ያመጡልናል” ይላሉ፡፡

Wednesday, December 10, 2014

የንስሐ ልጆቼን እንዴት ላገልግል? (2)

በዳዊት አብርሃም
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሐሙስ ታኅሳስ 2 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
የጽሑፉ ምንጭ፡- ሐመር መጽሔት፥ የግንቦት 2005 ዓ.ም. እትም ነው፡፡
የንስሐ ልጆች ጕባኤ
 አኹን አኹን የንስሐ ልጆቻቸውን መንፈሳዊ ፍላጐት ለማሟላት ጕዳይ እያሳሰባቸው የመጡ ካህናት የንስሐ ልጆቻቸውን የሚያሳትፍ ወርሐዊ ጕባኤ ያዘጋጃሉ፡፡ ቀሲስ አንተነህ ጌጡ ከእነዚኽ ካህናት አንዱ ናቸው፡፡ ቀሲስ አንተነህ በማኅበረ ቅዱሳን የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ፕሮግራም የትግበራ ቡድን አስተባባሪ ሲኾኑ በመደበኛ አገልግሎታቸው ተይዘው ዋነኛ የክህነት ተግባራቸውን ከፍጻሜ ሳያደርሱ እንዳይቀሩ በማለት 94 ለሚኾኑት የንስሐ ልጆቻቸው በማኅበረ ቅዱሳን ሕንፃ ላይ ወርኃዊ ጕባኤ ማዘጋጀት ከዠመሩ ሦስት ዓመት ሞላቸው፡፡ አዠማመሩን ሲገልጹ “የንስሐ ልጆቼ ጥቂት በነበሩ ጊዜ መገናኘት ቀላል ነበር፡፡ እየበዙ ሲሔዱ ግን አንድ በአንድ ዘወትር ማግኘት ይቸግራል፡፡ በዚኽ ጊዜ ደግሞ የንስሐ ልጆች መንፈሳዊ ሕይወት እንዳይጐዳ ለማድረግ በግለሰብ ደረጃ ያለውን ግንኙነት እንደ አስፈላጊነቱ በቀጠሮ እያደረጉ ኹሉን ደግሞ በቋሚ መርሐ ግብር በየወሩ በሚሠራ ጕባኤ ማከናወን ጥሩ አማራጭ ኾኖ ተሰማኝ፡፡”

Monday, December 8, 2014

የንስሐ ልጆቼን እንዴት ላገልግል? (1)

በዳዊት አብርሃም
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ማግሰኞ ኅዳር 30 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
የጽሑፉ ምንጭ፡- ሐመር መጽሔት፥ የግንቦት 2005 ዓ.ም. እትም ነው፡፡
 የንስሐ አባቶችን ሚና የሚያወሱና አገልግሎታቸውን የሚዘረዝሩ የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት በተለይ ካህናት ምእመናንን የመጠበቅ የእረኝነት ተግባራቸው ላይ ያተኩራሉ፡፡ ካህናት ምእመናንን ቃለ እግዚአብሔር መመገብ አለባቸው፤ ይኸውም በአደባባይ መስበክን የሚመለከት ሲኾን ከዚኹም ጋር በግል ለእያንዳንዱ የንስሐ ልጃቸው ምክር አዘል የኾነ ቃለ እግዚአብሔርን ማካፈልን ይጨምራል፡፡

Thursday, December 4, 2014

ወደ እግዚአብሔር ለመድረስ (ደረጃ ሁለት)



በዲ/ን ሳምሶን ወርቁ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሐሙስ ኅዳር 25 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ከዓለማዊ መሻት መለየት
 የተከበራችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንዴት ሰነበታችሁ? ወደ እግዚአብሔር ለመድረስ በሚለው ጽሁፍ ወደ እግዚአብሔር ለመድረስ  በያዕቆብ ምናባዊ መሰላል ደረጃ ለዓለም ጀርባ መስጠት የመጀመሪያ መሆኑን ተመልክተናል፡፡ በዚህ ያዕቆብ በራዕይ በተመለከተው ምናባዊ መሰላል ላይ እግራችን መውጣት ጀምሯል፡፡ አሁን ለዓለም ጀርባ ስለሰጠን አይኖቻቸን ወደ እግዚአብሔር የሚመለከቱ ጆሮዎቻችን ድምጹን ለመስማት የሚቀኑ መሆን ይጀምራሉ፡፡ ምንያቱም ለዓለም ጀርባ ስለሰጠን ኃጢአትን መጥላት፣ የእግዚአብሔርን ፍቅሩንና ቸርነቱን መረዳት ጀምረናል፡፡ አሁን በእውነት እኛ ወደ እግዚአብሔር በማደርገው ጉዞ እንደርስ ይሆን የሚል ስጋት አይገባንም ምክንያቱም እኛ እስከፈቀድን ድረስ ከድካማችን ሊያሳርፈን ከወደቅንበት የሚያነሳን አምላክ ሊረዳን እንደቀረበ አውቀን ተረድተናልና፡፡ አሁን ጥያቄው እንዴት በመንገዳችን ጸንተን እንጓዝ የሚል ነው?

FeedBurner FeedCount