(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ቅዳሜ ታኅሳስ 18
ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ
አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ትርጕም
ጥሬ ቃሉን ስንመለከተው መልአክ የሚለው የግእዝ ቃል ኹለት ትርጉሞች አሉት፡፡
አንደኛው አለቃ፣ ሹም ማለት ነው፡፡ በዮሐንስ ራዕይ ላይ የምናገኛው ሰባቱ የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎች መላእክት ተብለው መጠራታቸውም
ከዚኽ አንጻር ነው /ራዕ. 2 እና 3/፡፡ ኹለተኛውና ከተነሣንበት ርእስ አንጻር ስናየው ደግሞ መልክእተኛ፣ የተሰደደ፣ የተላከ
የሚል ትርጕም አለው /ዕብ.1፡14/፡፡ ይኸውም የመላእክት ተግባር ምን እንደኾነ የሚያስረዳ ቃል ነው፡፡ መላእክት ከእግዚአብሔር
ወደ ሰው፥ ከሰውም ወደ እግዚአብሔር የሚላላኩ መናፍስት ናቸውና፡፡ መላእክት በሌላ ስማቸው የሰማይ ሠራዊት ተብለው ይጠራሉ፡፡