(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ረቡዕ 02 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡- “ሰማዕትነት
አያምልጣችሁ” እና “ነጽሮተ ሀገር” በሚል ርእስ የተዘጋጁ ኹለት መንፈሳውያን መጻሕፍት የካቲት 28 ቀን 2007 ዓ.ም. በገነተ
ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ስብከተ ወንጌል አዳራሽ ጥሪ የተደረገላቸው አበው ካህናት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ሰባክያነ
ወንጌል እና የመቅረዝ ዘተዋሕዶ ድረ ገጽ አንባብያን በአጠቃላይ ከ400 በላይ ታዳምያን በተገኙበት ደማቅ መርሐ ግብር ተመረቁ፡፡
“ሰማዕትነት አያምልጣችሁ” የሚል ርእስ የተሰጠው አንደኛው መጽሐፍ በመቅረዝ ዘተዋሕዶ ድረ ገጽ ዋና አዘጋጅ በገ/እግዚአብሔር ኪደ
የተተረጐመ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሥራ ሲኾን ኹለተኛው መጽሐፍ ደግሞ በመምህር ዘሪኹን መንግሥቱ የተዘጋጀ መጽሐፍ ነው፡፡ መርሐ
ግብሩ በአባ አሥራተ ማርያም ደስታ በጸሎት የተከፈተ ሲኾን ዘማሪት ጽጌ ወቅቱን የተመለከተ ያሬዳዊ መዝሙር አቀረበች፡፡
Tuesday, March 10, 2015
Wednesday, March 4, 2015
በመጽሐፍ ምረቃ ቀን እንዲገኙ ተጋብዘዋል
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ረቡዕ የካቲት
28 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ሰላመ እግዚአብሔር
ይብዛላችሁ ውድ የመቅረዝ አንባብያን፡፡ እንደምን ሰነበታችሁ? እግዚአብሔር ቢወድና ቢፈቅድ ቀጣይ ቅዳሜ ማለትም የካቲት 28 ቀን
2007 ዓ.ም. በገ/ጽ/ቅ/ጊ/ቤተ ክርስቲያን (ፒያሳ) ስብከተ
ወንጌል አዳራሽ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ዠምሮ
ኹለት መጻሕፍት አንድ ላይ ይመረቃሉ፡፡ አንደኛው መጽሐፍ በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመው የቅዱስ ዮሐንስ
አፈወርቅ መጽሐፍ ሲኾን ኹለተኛው መጽሐፍ ደግሞ የዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት የትምህርት ክፍል ሰብሳቢ በኾኑት በመምህር ዘሪኹን መንግሥቱ የተዘጋጀ ነው፡፡
Thursday, February 12, 2015
ቅዱሳት መጻሕፍት ስለማንበብ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሐሙስ የካቲት 5 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
እስኪ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ መጽሐፍ ቅዱስን ላለማንበብ ምክንያት ይደረድሩ ለነበሩ ሰዎች ይሰጣቸው የነበረውን ተግሣፅ ከዚኽም ከዚያም ያሰባሰብኩትን አንድ ላይ አድርጌ ላካፍላችኁና ራሳችንን እንመርምርበት፡-
·
መጽሐፍ ቅዱስ የለንም የሚሉ ነበሩ፡፡ ይኽም በጣም ውድ ስለኾነ ነው፡፡ በ4ኛው መ.ክ.ዘ. አንድን ሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ ለመግዛት የአንድ ዓመት ደመወዝ ነበርና፡፡ ሊቁ ግን “ይኽ ምክንያት አይኾንም፡፡ ብያንስ መጽሐፍ ቅዱስ ሙሉው ባይኖራችኁም ከወንጌል አንዱን ብቻ መግዛት ትችላላችኁ፤ ርሱንም ዘወትር ማንበብ ትችላላችኁ” ይላቸው ነበር፡፡ “ይኽን ማድረግ ባትችሉ እንኳን ዘወትር ወደዚኽ ጕባኤ በመምጣት በነጻ መማር ትችላላችኁ፡፡ ብያንስ ወደ ቅዳሴው ኑ፡፡ እዚያ የሚነበበውንና የሚተረጐመውን በሥርዓት አዳምጡ፡፡ ወዮ! እዚኽ ስትመጡ ትቁነጠነጣላችኁ፤ ሙቀቱ ብርዱ ትላላችኁ፡፡ ወደ ገበያ ቦታ፣ ወደ ተውኔት፣ ወደ ስታድዬም ስትሔዱ ግን ምንም አይመስላችኁም፡፡ ዶፍ ዝናብ ቢዘንብባችኁ፣ ሙቀቱ አናትን የሚበሳ ቢኾን፣ በውኃ ጥም ብትያዙ ትቋቋማላችኁ፡፡ ታድያ ምን ዓይነት ይቅርታ ይኾን የሚደረግላችኁ?” ይላቸው ነበር፡፡
Thursday, February 5, 2015
በእንተ አትሕቶ ርእስ
በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
(መቀረዝ ዘተዋሕዶ፣ ጥር 28 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
እግዚአብሔርን የምትወዱት አንድም እግዚአብሔር የሚወዳችኁ ልጆቼ! ትሕትናን ገንዘብ ማድረግ ምን ያኽል ጥቅም እንዳለው፥ በአንጻሩ ደግሞ ትዕቢትን ገንዘብ ማድረግ ምን ያኽል ጕዳት እንዳለው ታውቁ ዘንድ እወዳለኁ፡፡ ምንም ያኽል ምግባር ትሩፋት ቢኖረን፣ ብንጾም፣ አሥራት በኵራት ብናወጣ፣ ሌላም ብዙ የብዙ ብዙ ምግባራትን ብናደርግ ትሕትና ግን ከሌለን ከንቱ ነን ብዬ እነግራችኋለኁ፡፡ ምንም ያኽል ኃጥአን ሳለን ነገር ግን የተሰበረ ልቡና ካለን፥ በምግባር በትሩፋት አሸብርቀው ሳለ ትዕቢተኞች ከኾኑት ሰዎች ይልቅ በእግዚአብሔር ዘንድ ተወዳጆች ነን ብዬ እነግራችኋለኁ፡፡ ከቀራጩ በላይ ማን ኃጢአተኛ ነበር? /ሉቃ.18፡9-14/፡፡ ነገር ግን ይኽ ኃጢአተኛ ሰው ዓይኑን ወደ ሰማይ ቀና አድርጐ ሊያይ ባለመውደዱ፣ በምትመሰገንበት በቤተ መቅደስኅ መቆም የማይቻለኝ ኀጥእ ነኝ በማለቱ ከማይቀማው፣ ከማይበድለው፣ ከማያመነዝረው፣ በሳምንት ኹለት ጊዜ ከሚጾመው፣ ከገንዘቡ ኹሉ አሥራት ከሚያወጣው ፈሪሳዊው ይልቅ በእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነትን አገኘ፡፡ ይኽስ እንዴት ሊኾን ቻለ?
Subscribe to:
Posts (Atom)