Monday, August 10, 2015
መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የማክሰኞ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ
መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የማክሰኞ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ: ገ/እግዚአብሔር ኪደ (መቅረዝ ዘተዋሕዶ ነሐሴ ፯ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም)፡- ለምስጋና ኹለተኛ፣ ለፍጥረት ሦስተኛ ቀን በሚኾን በዚህ ቀንም እመቤታችን ትመጣለች፤ የብርሃን ድባብ ይዘረጋል፤ የብርሃን ምንጻፍ ይነጸፋል፡፡ ከ...
Sunday, August 9, 2015
መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የሰኞ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ
መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የሰኞ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ: ገ/እግዚአብሔር ኪደ (መቅረዝ ዘተዋሕዶ ነሐሴ ፭ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም.)፡- ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም እመቤታችን ከባረከችው በኋላ ምስጋናውን የጀመረው “ፈቀደ እግዚእ…” ብሎ ነው፡፡ ፩. በ መቅድመ ወንጌል “ ወ አልቦቱ ...
Friday, August 7, 2015
“ኹል ጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ” ፊልጵ.4፡4
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ነሐሴ 1 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ
አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክታቱ ላይ ደጋግሞ ከሚናገራቸው ኃይለ ቃላት አንዱ ስለ ደስታ ነው፡፡
አራት ምዕራፍ ብቻ ባላት በፊልጵስዮስ መልእክት ብቻ እንኳን “ደስ ብሎኛል፤ ወደፊትም ደስ ይለኛል፤ ደስታዬን ፈጽሙልኝ፤ ደስ ይበላችሁ፤”
እያለ ዐሥራ አምስት ጊዜ ተናግሯል፡፡
ለመኾኑ
ምንድነው ይኼ ደስታ? አንድን ነገር (ለምሳሌ ልጅ፣ ሥራ፣…) ባገኘን ጊዜ ደስ እንደሚለን ያለ ደስታ ነውን? ወደ መዝናኛ ስፍራዎች
በሔድን ጊዜ አፀዱን፣ አዕዋፉን፣ ፏፏቴዉን ባየን ጊዜ፣ ምግቡን በበላን፣ ወይም መጠጡን በጠጣን ጊዜ ደስ እንደሚለን ያለ ደስታ
ነውን? አይደለም! እንዴት ነው ታዲያ?
በልብ
መታሰቡ፣ በቅዱሳት መጻሕፍት መዘገቡ፣ በቃል መነገሩ ከፍ ከፍ ይበልና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፡- “እኔ የምሰጣችሁ
ሰላም ዓለም እንደሚሰጣችሁ አይደለም” ብሎ እንደተናገረው /ዮሐ.14፡27/፥ ይህ ደስታም በዚህ ዓለም በምናገኛቸው ነገሮች ወይም
በምንደርስባቸው ስኬቶች የሚገኝ አይደለም፤ ከእግዚአብሔር ብቻ የምናገኘው ደስታ ነው እንጂ፡፡ ይህም ደስታ በግሪኩ “ቻራ” ይሉታል፡፡
ይህም ማለት ቋሚ ከኾነው ከእግዚአብሔር የሚገኝና፡- ብናገኝም ብናጣም፣ ብንጠግብም ብንራብም፣ በተሳካልንም ባልተሳካልንም ጊዜ፣
ጤና ስንኾንም ስንታመምም፥ በአጠቃላይ በዚህ ዓለም በዙርያችን በሚለዋወጡ ኹኔታዎች አብሮ የማይለዋወጥ ነው፡፡
Wednesday, August 5, 2015
መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የውዳሴ ማርያም ትርጓሜ- መግቢያ
መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የውዳሴ ማርያም ትርጓሜ- መግቢያ: ገ/እግዚአብሔር ኪደ (መቅረዝ ዘተዋሕዶ ነሐሴ ፩ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም.)፡- ውዳሴ፡...
Subscribe to:
Posts (Atom)