Pages

Tuesday, July 24, 2012

የቁልቢ ገብርኤል አመሠራረት- በዲ/ን ዳንኤል ክብረትና ቀሲስ ከፍያለው መራሒ!


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

 ከአዲስ አበባ በስተምሥራቅ 461 ኪ/ሜ. ርቀት ላይ በምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጋራ ሙለታ የሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ የዚህን ደብር አመሠራረት በተመለከተ በብዙ ሊቃውንት የሚተረከው የሚከተለው ነው፡፡

በዘጠነኛው መ/ክ/ዘ. ዮዲት ጉዲት ተነሥታ አብያተ ክርስቲያናትን ስትመዘብር፣ ክርስቲያኖችን ስትገድልና መጻሕፍትን ስትቆነጻጽል ንጉሥ አንበሣ ውድም በአኩስምና በአከባቢዋ የነበሩ ታቦታትንና ንዋያተ ቅዱሳትን በመያዝ ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ወደ ዝዋይ መጣ፡፡

ከ40 ዓመታት ስደት በኋላ አንበሣ ውድም ወደ አኵሱም ሲመለስና የንዋያተ ቅዱሳት ቆጠራ ሲደረግ ታቦተ ቅዱስ ገብርኤል በዝዋይ መቅረቱ ታወቀ፡፡ ከኤርትራ ደብረ ሲና ማርያም የመጡና አባ ሌዊ የተባሉ አባት ታቦቱን ለማምጣት ከንጉሡ አስፈቅደው ወደ ዝዋይ መጡ፡፡

አባ ሌዊ ከሰባት ቀን ሱባኤ በኋላ ታቦተ ቅዱስ ገብርኤልን ይዘው ወደ አኵሱም ሲጓዙ ቅዱስ ገብርኤል ተገልጦ “እኔ ወደማሳይህ ቦታ ታቦቱን ይዘህ ሂድ” አላቸው፡፡ አባ ሌዊም ታቦቱን ይዘው ተከተሉት፡፡ በመጨረሻም ቁልቢ ደረሱ፡፡ ለአባ ሌዊም የተፈቀደላቸው ቦታ ይሄ መሆኑን ታቦቱም በኋላ ዘመን ለሕዝቡ ድንቅ ሥራ እንደሚሠራ ቅዱስ ገብርኤል ነግሯቸው ተሠወረ፡፡ አባ ሌዊ በቦታው ለ130 ዓመታት ያህል አገልግለው በንጉሥ ግርማ ሥዩም ዘመነ መንግሥተ ታኅሳስ 14 ቀን ዐርፈዋል፡፡

ግራኝ አሕመድ ኢትዮጵያን ሲወርር ብዙ ካህናት ከሰሜን ኢትዮጵያ ታቦታትንና ንዋያተ ቅዱሳትን ይዘው ሲጓዙ ቁልቢ ደረሱ፡፡ መልአከ ገነት መብረቁ፣ መምህር የማነ አብ፣ አባ ተከስተ ሥሉስ የተባሉ ካህናት ከተነጠፈ ድንጋይ ላይ የተጻፈ ነገር ያገኛሉ፡፡ ጽሑፉም ታቦተ ቅዱስ ገብርኤል በሥዉር መቀመጡን፣ ልዩ ልዩ ተአምራት እንደሚፈጸምበት፣ ወደ ፊትም ታላቅ ቤተ መቅደስ እንደሚሠራበት፣ እንዴት አባ ሌዊ ታቦቱን ወደዚህ ቦታ እንዳመጡት የሚገልጽ ነበር፡፡ እነርሱም ይህን ታሪክ ይዘውት በነበረው መጽሐፈ ቀሌሜንጦስ ሕዳግ ላይ ጻፉት፡፡ ወደ ዝዋይ ደሴት ሲደርሱም መጽሐፉን በዚያ አኖሩት፡፡

ልዑል ራስ መኰነን ከዝዋይ ደሴት መጽሐፈ ቀሌሜንጦስን አስመጥተው ሲያነቡ የቁልቢ ገብርኤልን ታሪክ በማግኘታቸው የቅዱስ ገብርኤልን ቤተ ክርስቲያን ለማነጽ ተነሡ፡፡ ልዑል ራስ መኰንን በአከባቢው የአየር ንብረት ተማርከው በሥፍራው ቤት ሠርተው ነበር፡፡ ልዑል ራስ መኰንን ቁልቢ ገብርኤልን ከመትከላቸው በፊት ቦታው የአከባቢው ጎሳዎች የግጭት መነሃርያ ነበር፡፡ ሰላምን በአከባቢው ከመሠረትህ በቦታው በስምህ ቤተ ክርስቲያን እሠራልሃልሁ ብለው እንደተሳሉም ይነገራል፡፡

የተሳሉት በመፈጸሙ የቅዱስ ገብርኤል ታቦት የት እንዳለ ሲያፈላልጉ ቡልጋ ውስጥ ከአዠጉጉ ካህናተ ሰማይ ጋር አባ ዱባለ የተባሉ ካህን ያስቀመጡት ታቦተ ቅዱስ ገብርኤል መኖሩ ተነገራቸው፡፡ ልዑል ራስ መኰንን ለአባ ዱባለ መልእክት ስለላኩባቸው ከሐረር በተላኩ ካህናት አማካኝነት የቅዱስ ገብርኤልን ታቦት ላኩ፡፡ ልዑል ራስ መኰንንም ከነሠራዊቶቻቸው ሸንኮራ ድረስ ሄደው ታቦቱን በመቀበል የካቲት 21 ቀን 1884 ዓ.ም ታቦቱ ቁልቢ ገባ፡፡

የመቃኞው ሥራ በ1883 ዓ.ም ተጀምሮ ፍጻሜ አግኝቶ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረው ሐምሌ 19 ቀን 1884 ዓ.ም ነው፡፡ በዚሁ ዕለት የዋናው ቤተ ክርስቲያን ሕንጻ ሥራ የመሠረቱ ድንጋይ ተጥሎ ታኅሳስ 19 ቀን 1888 ዓ.ም የቤተ ክርስቲያኑ ሥራ ተፈጽሞ በአቡነ ማትያስ ተባረከ፡፡ ቦታውን ከባለ አባቶች የገዙት በአርባ የቁም ከብት ነው፡፡ ራስ መኰንን መጋቢት ዘጠኝ ቀን 1889 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ ሲሄዱ እዚህ ቦታ ላይ በድንገት ስለታመሙ በዕለቱ ሥጋወደሙ ተቀብለውበታል፡፡ በመጀመርያ ሲተከል በገጠር ቤተ ክርስቲያን ሥሪት ሲሆን በኋላ ግን በስእለት ሰማኢነቱ በመላ ኢትዮጵያ እየታወቀ ስለ መጣ ደብር ሆኗል፡፡

የቅዱስ ገብርኤል ምልጃና በረከት አይለየን!!

(ምንጭ፡ የቤተ ክርሰቲያን መረጃዎች- በዲ/ን ዳንኤል ክብረት፤ Saints and Monastries in Ethiopia, by Kesis Kefyalew Merahi)    

11 comments:

  1. 1.yezih blog tshufochEN bemtshaF MELEK BETAWETOACHEW,2.ABA SELAMA YETEHADSO BLOG ENKUA 670,OOO GEDEMA SEWOCH EYETEGOBEGH YEHEN YEMESELE TEWAHDOAWI YEWENGEL AZMERA 30.000 SEWOCH BICHA MEGOBEGHETU ASAZENOGHALENA BE NE DANIEL KIBRET BLOG LAY BETASTEWAWEKEW 3.BETERFE MANENETEH MENEM BAYAREGELENEM SEMHEN BETASAWUKEN GOD BLESS YOU I HOPE I WILL GET YOU AGAIN IN BOOK

    ReplyDelete
  2. Beewnet betam amesegnalehu! 1. Ene yegna bemibalut blogoch endiastewawkulgn teykeachew neber. Honom gn ke ANDADRIGEN beker fekadegnoch alhonum. Engdih ene yeakmen madregen eketlalehu. Blogun yemiwedu miemenanm yedrshachew biwetu melkam new. Malete share byadergut bzu sewoch ytekemubetal. 2. Bemetshaf melku mazegajet ychalal. Yemasatem akmu gn yelegnm. Yhn madreg yemifelg kalem be 0912074575 bidewllgn destaye weder yelewm. 3. Kene sim ylk yekalu balebet Egziabher enditawek lemalet new smen yalawetahut. Kasfelege gn edit adergewalehu. G/Egziabher Kide ebalalehu. GBU again!

    ReplyDelete
  3. yihe ye'Tehadisowoch lisan new yemibal neger semichalew.
    1,ye'tehadiso kalihone sile'Emebetachin milja bitasitemiru
    2,kirstos temalaj enji amalaj enidalihone ena feraj mehonun bedenib bitasitemiru.
    Ye'Tehadiso mehonun ena alemehonun maregaget yemichalew Ye'orthodox tewahdo eminet yehonewun negeroch hulu sitasitemiru new.
    Ene facebook lay ye Orthodox tewahdo page alegn bizu abalatoch alugn yihen blog enidiyanebu share adrigew neber abizagnochu gin ye'tehadiso lisan yehone blog endet share taderigaleh bilew betam new yazenut.ene bebekule ye'tehadiso yemibalu timritoch alagegnhubetim gin ahunem bihon bizu mesirat yalebih yimesilegnal.
    Orthodox Tewahdo'n keleloch yemileyiwutan timritoch bedenib masitemar alebih.maletim ye'emebetachinen amalajinet,ye'melaektin ena ye'kidusanen amalajinet,ye sigdet ayinetoch,ye'kirstos ferajinet....
    Bemecheresha maninetih bitawek simeh bigelets tiru new.

    ReplyDelete
  4. ehete weyim wendeme betamkonjo(betamsexy) yehe blog yetehadso blog alemehonun aregagtlshalehu 1.seleemebetachin mastemar yemigeba bihonem sele getachinem bihon eyastemare tekeklegh behone malet beorthodoxawi menged kastemare tehadso ayasbelewum endewum protestantoch yemiweksun selemebetachin yimtsebkut lekerstos kemetawulut yesebket gize yibeltal teblo aydelemen degmos yehinen anbebeshewal ... ወደ አንዲት ድንግል … ልዩ ድንግል በመሆን አንድ ናትና “አንዲት!” ብሎ ገለጻት። ሌሎች በሥጋ ድንግል ይሆኑ ይሆናል። እርሷ ግን በሥጋም በኀሊናም ድንግል ናት “ርግቤ መደምደሚያዬ አንዲት ናት፣ ለወለደቻትም የተመረጠች ናት” (መኀመኀ.6÷9)። ጠቢቡ በትንቢት መንፈስ ሆኖ፡-ርግቤ አላት የየዋሕነቷን
    መደምደሚያዬ አላት የሞትን ታሪክ የሚደመድመውን ትውልዳለችና ለወለደቻትም የተመረጠች ናት፡- የተወለደ ሁሉ ምርጥ አይደለም። ድንግል ማርያም ግን እንኳን ለወለደቻት ለወለደችውም የተመረጠች ናት።

    ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፡- ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከ የሚናገረው እውነት ነውና ::

    የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ፡- ማርያም ማለት ጸጋወሀብት ማለት ነው። ለጊዜው ለእናት ለአባቷ ልጅ ሆና ተሰጥታለች በፍጻሜው ግን የጸጋ እናት ሆና ለልጆቿ ሁሉ ተሰጥታለችና። መልአኩም ወደ እርሷ ገብቶ ደስ ይበልሽ፣ ጸጋን የሞላብሽ ሆይ፣ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፣

    ደስ ይበልሽ…ይህንቃል የተናገራት ቅዱስ ገብርኤል ቢሆንም መልአክቱ የመጣው ግን ከሰማይ ነው። ጌታ ደስ ይበልሽ አላት። ደስ ይበልሽ ያላት በመጀመርያ ድኅነተ ዓለም ስለደረሠ ሲሆን ቀጥሎ ደግም እርሱን ለመውለድ ክብር በመመረጧ ነው። አንዳንዶች ግን ጌታን ደስ ያሰኙት እየመሰላቸው “ደስ ይበልሽ” ያላት እናቱን “ይሰድቡለታል”!

    ጸጋን የሞላብሽ ሆይ

    ከቅዱስ ሕዝብ ወገን ጸጋ ያለው እንጂ ጸጋ የሞላበት የለም። አንድ ሁለት ጸጋ ይሞላበት ይሆናል፣ ጸጋ ሁሉ ግን አይሞላበትም። የጸጋ ስጦታ ልዮ ልዩ ነውና (1ቆሮ. 12÷4)። ድንግል ማርያም ግን “ ምልዕተ ጸጋ” የሚለው ማዕርጓ ጸጋ ሁሉ እንደሞላባት የሚያሳየን ነው። እንዴት በሉ?

    1ኛ- ጌታ ከነ ጸጋ ስጦታው ሁሉ ጋር በማኀፀኗ በማደሩ ነው። ታዲያ አባቶች ” የጸጋ ግምጃ ቤት” ቢሏት ተሳስተው ይሆን?
    2ኛ- ፍጹሙ ጸጋ እርሱን ጌታን መውለድ ነውና።
    ጌታ ከአንቺ ጋር ነው

    አንዳንዶች ጌታ በዮሐንስ ወንጌል ላይ..” አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? “ ብሏታል። ስለዚህ ማርያም ማርያም አትበሉ ሲሉ ብዙ ጊዜ ሰምተናል (ዮሐ. 2÷4)። አንድን ጹሑፍ ላልተጻፈበት ዓላማ ማዋል አለመታደል ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ዘይቤ “ከአንቺ ጋር ምን አለኝ” ማለት “ከአንቺ ጋር ምን ጠብ አለኝ?” ማለት እንደሆነ ግልጽ ቢሆንም መልአኩ ግን በቀጥተኛ መልዕክት “ጌታ ከአንቺ ጋር ነው”ይላታል። “ጌታ ከአንቺ ጋር ነው” የሚለው የእግዚአብሔር መልእክተኛ ከሆነ “ጌታ ከእርሷ ጋር ምን አለው?” የሚለውስ የማን መልእክተኛ ነው ትላላችሁ? ተወዳጆች ሆይ፡- ጌታ ከእርሷ ጋር ባይሆን ዛሬ እኛ ከእርሱ ጋር አንሆንም ነበር፣ የእርቃችን ሰነድ፣ የአብሮነታችን ምስጢር፣ የመገናኛ ድንኳናችን ናት። አማኑኤል ትርጓሜውም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር” የተባለው ከእርሷ ሰው ሆኖ አይደለምን? (ማቴ.1÷23)። ፍቅርን እየወደደ የፍቅርን ሀገር የሚጠላ ማነው? ፍቅር ጌታን እየወደደ ሀገረ ፍቅር ድንግል ማርያምንስ የሚጠላ ማነው? እርሱ ይመለካል፣ እርሷን ብጽዕት እንላለን! እርሱ ታላቅ ገናና ነው፣ እርሷ ታላቅ ሥራ ተደርጎባታል (ሉቃ.1÷49)። እርሱ አምላክ ነው፣ እርሷ እናቱ ናት። የልባችን መሻት እንዲሞላ እርሱ ከእርሷ ጋር እንደሆነ እርሷም ከእርሱ ጋር ናት።

    ሴትየዋ በዕድሜ የገፉ ናቸው፣ አንዱ በመንገድ አስቁሞ “ቃል ላካፍልዎት” ይላቸዋል። እርሳቸውም “ተወኝ ባክህ ልጄ ልደትዬን ተሣልሜ እየተመለስሁ እንደመሆኔ ደክሞኛል” ይሉታል፣ እርሱም “ ማናት ደግሞ ልደትዬ” ? ይላቸዋል፣ “ድንግል ማርያም ናት“ይሉታል። እርሱም “ጌታ እኮ ከአንቺ ጋር ምን አለኝ!“ ብሏታል ሲል ደንግጠው “ እናቱን?” አሉ “አዎ”! አላቸው። እርሳቸውም “ለእናቱ ያልሆነ ለእኔ ይሆናል ብለህ ነው” ብለው እንደቆመ ጥለውት ሄዱ። እባካችሁ ለእናቱ የማይሆን ኢየሱስ እኛ ቤት የለም!kemekrez blog bentekidusan kemilew amed yetewosede new
    .......yiketlal

    ReplyDelete
  5. 2.ehete weyim wendeme betamkonjo(betamsexy)menfesawi wendeme getachi getachin ahun bekiber eyale endemayamaled astemroal... menalbat yaleshachew sewoch tehadso yihone belew menfesawi wendemen yeterterut bebetkerstian likawnet zend getachin selegbabat kidste kidusan hulet aynet hassab selemintsbarek new እንግዲያውስ ተወዳጆች ሆይ! “ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራል” የሚል ጥሬ ምንባቡን ብቻ በመያዝ እንዳይሳሳቱ ይጠንቀቁ፡፡ ይህ ማለት አስቀድመን እንደነገርንዎት የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ የዕለተ ዐርብ የማስታረቅ አገልግሎት ከአዳም መፈጠር ጀምሮ እስከ ዕለተ ዐርብ ላሉት ሁሉ ብቻ ሳይሆን እስከ ዕለተ ምጽአት የሚፈጠረው ፍጥረት ሁሉ በዚሁ የዕለተ ዐርቡ የማስታረቅ አገልግሎት እያመነ እንደሚድን ደሙም የማስታረቅ ችሎታ እንዳለው የሚገልጽ ነውና /ዮሐ.17፡20-21/፡፡ ሊቀ ካህናችን ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ጊዜ የሠዋው መሥዋዕት እንደ ብሉይ ኪዳን ሊቃነ ካህናት መሥዋዕት ተረፈ ኃጢአት (ያልተደመሰሰ ኃጢአት) አስቀርቶበት አሁን ያንን ለማስተስረይ የሚወድቅ የሚነሣ አይደለምና፡፡ ጸሎቱና መሥዋዕቱ ምልአተ ኃጢአትን (ኃጢአትን ሁሉ) ለመደምሰስ አንድ ጊዜ ተፈጽሟልና /ዮሐ.19፡30/፡፡ ስለዚህ ይማልድልናል ስንል “የዕለተ ዐርቡ ቤዛነት፣ ካሣ፣ ሞት፣ ደም መፍሰስ አዲስና በየዕለቱ ንስሐ የሚገቡትን የሚያቀርብ የሚያድን ነው” ማለት መሆኑን ልንረዳ ያስፈልጋል፡፡ (yehaymanotachin like kahnat part3) ....menalbat yaleshachew sewoch tehadso yihone belew menfesawi wendemen yeterterut... malede yemilen kal bemtekemu kehone mesthaf kidusm eko malede... biloal neger gen wendemem hone metshafkidus ahun getachin komo yimaldal alalum ...bebetkerstian likawnet zend getachin selegbabat kidste kidusan hulet aynet hassab selemintsbarek new ሁል ጊዜ ይለምናል ብሎ የሚያስብስ ከቶ እንደምን ይኖራል?ቁሞ የሚያገለግል እንዳያስመስሉት በማሰብ በመትጋት መሥዋዕት አንድ ጊዜ እንደሠዋ አስረዳ፡፡ አንድ ጊዜ ሰው እንደ ሆነ አንድ ጊዜ ተሾመ፤ አንድ ጊዜ እንደ ተሾመ አንድ ጊዜ አገለገለ፡፡ ሰው በሆነ ጊዜ የሰውነትን ሥራ በመሥራት ጸንቶ እንዳልኖረ ሁሉ ባገለገለ ጊዜም በማገልገል ጸንቶ አልኖረም፡፡ አሁን ቢያገለግል ኖሮ ሐዋርያው ቆመ እንጂ ተቀመጠ ባላለ ነበር(yehaymanotachin like kahnat part3)ና፡፡ayesh ahun komo ayagelgelem bemider lay yadergachewn negeroch and gize fetsmo ahun bekiber new yalew mekemet mefredn engi milgan ayasymena ...yiketlal

    ReplyDelete
  6. 3.ehete weyim wendeme betamkonjo(betamsexy)menfesawi wendeme1menalbat yaleshachew sewoch tehadso yihone belew menfesawi wendemen yeterterut bebetkerstian likawnet zend getachin selegbabat kidste kidusan bizu andmeta endalew balemeredatachew new gen kideste kidusan emebetachin nat beblu kidan debtera dinkuan yegeziabher meglech neberch endihu degmo beamanawi huneta yetegeletbat sigan yenesabat kideste kidusan emebetachin nat
    1 መጸሐፈ ነገሥት 8፡ 10-12

    ሉቃስ 1፡ 35ልአኩም እንዲህ ሲል መለሰ፤ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፤ የልዑል እግዚአብሔርም ኀይል በአንቺ ላይ ይሆናል፤ ስለዚህ ከአንቺ የሚወለደው ሕፃን ቅዱስ ነው፤ የእግዚአብሔርም ልጅ ይባላል፡፡››

    ‹‹ካህናቱ ከቤተ መቅደሱ እንደወጡ ቤተ መቅደሱ ድንገት በደመና ተሞላ፤ በደመናውም ውስጥ የእግዚአብሔር የክብር መገለጥ ብርሃን ያንጸባርቅ ስለነበር ካህናቱ ተመልሰው ለመግባትና አገልግሎታቸውን ለማከናወን አልቻሉም፡፡ በዚህ ጊዜ ሰሎሞን እንዲህ ሲል ጸለየ፤ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ አንተ በደማናና በጨለማ ውስጥ መሰወርን ወድደሃል፡፡››

    ReplyDelete
  7. 3.3.ehete weyim wendeme betamkonjo(betamsexy)menfesawi wendeme1menalbat yaleshachew sewoch tehadso yihone belew menfesawi wendemen yeterterut bebetkerstian likawnet zend getachin selegbabat kidste kidusan bizu andmeta endalew balemeredatachew new1 kelay endayenew ki deste kidusan emebetachin nat2.getachin yegbabet kideste kidusan meskel new የኦሪት ሊቃነ ካህናት ወደ ለእግዚአብሔር መስዋት በመስዋት ሐጢያትን ያስተሰርዩ ነበር። በተለይም በአመት አንድ ጊዜ ካህኑ ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ ደም ይዞ በመግባት ስለህዝቡና ስለራሱ በእግዚአብሄር ፊት ይታይ ነበር ይሁንና ሰለ ራሱና ስለ ሕዝቡ ስሕተት የሚያቀርበውን ደም ሳይዝ አይገባም፤ ዕብ ፱፡፯ like kahnu. hulegeth wede denkuanu sigeba ደም ይዞ መሆን አለበት ጌታችን degmo ደሙን ያፈሰሰዉ በመስቀል ላይ engi በሰማይ አይደለም ዕብ ፯፤፪፯ እርሱም እንደነዚያ ሊቃነ ካህናት አስቀድሞ ስለ ራሱ ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ሊያቀርብ አያስፈልገውም፤ ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎአልና። ዕብ ፩፤፫፫ እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤ ብ ፱፤፪፮፡፪፯ጌታችን ሊቀ ካህናት ሊባል የተገባው ፍፁም ሰው መሆኑን ለማጠየቅ በእውነተኛይቱ ሰው በማይገባባት ቅድስተ ቅዱሳን (መስቀል) አንድ ጊዜ ብቻ ስለገባ ፡ በእርሷም እውነተኛውን መስዋእቱን (ራሱን) ስላቀረበና ሃጢአተ አለምን ስላራቀ ነው፡፡ የቀደመው ክህነት ግን ፍፁም አይደለም፡፡በመሆኑም እለት እለት ወደ ቤተ መቅደስ እየገቡ የሚሞት መሥዋእት ማቅረብ ግድ ሆነባቸው፡፡ ዕብ 9፡6-7 ጌታችን ግን ክህነቱ ”ፍፁም” መሥዋእቱም “ህያው” ስለሆነ እለት እለት መስዋእት ማቅረብ አላስፈለገውም፡፡ ዕብ.7:27 “እርሱም እንደነዚያ ሊቃነ ካህናት አስቀድሞ ስለ ራሱ ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ሊያቀርብ አያስፈልገውም፤ ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎአልና።” እንዳለ አንድ ጊዜ ባቀረበው መስዋእት ለዘላለም አንፅቶን ሊኖር ይቻለዋልና ሊቀ ካህናትም በየዓመቱ የሌላውን ደም ይዞ ወደ ቅድስት እንደሚገባ፥ ራሱን ብዙ ጊዜ ሊያቀርብ አልገባም፤ እንዲህ ቢሆንስ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ብዙ ጊዜ መከራ ሊቀበል ባስፈለገው ነበር፤ አሁን ግን በዓለም ፍጻሜ ራሱን በመሠዋት ኃጢአትን ሊሽር አንድ ጊዜ ተገልጦአል። ለበለጠ ማስረጃ የአይሁድ ሊቃነ ካህናት ስርዐተ መሠዋት እንመልከት ።as there was a high priest every year who celebrated the Old Covenant *** Jesus Christ is The High Priest of the New Covenant for Eternity
    ***The priests chose two perfect adult male goats Jesus Christ and Barabbas were chosen by Pontius Pilate
    ***The two goats were presented by the priests outside the Temple *** Jesus Christ and Barabbas were presented to the crowds outside the Praetorium***

    ReplyDelete
  8. continued...The scapegoat was chosen by lots*** Barabbas was chosen by the crowds***
    The scapegoat later received the Rite of Atonement, and was set free *** Barabbas was set free, which is a picture of the Gospel***
    The sacrificial goat was then sacrificed, and the High Priest then entered the Holy Place with the blood of the sacrificial lamb *** Jesus Christ was the High Priest, and the Crucifixion Site became the Holy Place of the New Covenant. Jesus Christ was sacrificed by God on the Cross, as the Lamb of God.***
    The High Priest was completely alone in the Tabernacle Jesus Himself was the only High Priest of the New Covenant once and for all in Eternity***
    The High priest spread blood on the horns of the altar in the Holy Place *** The Blood of Jesus Christ was smeared all over the Cross
    The High Priest prayed to God to forgive the sins of the people *** Jesus Christ prayed for God to forgive the sins of the people
    There was a confession of sin by the high priest over the scapegoat *** Jesus Christ, the High Priest of the New Covenant, did NOT confess sin, because He was without sin. Instead, Jesus Christ became the Blood Sacrifice to take away sin.
    The scapegoat bore all the sins of the people to an uninhabited land *** In the New Covenant, "The blood of Jesus Christ His Son cleanses us from all sin," I John 1, 7
    The blood of the sacrificial goat was sprinkled onto the Mercy Seat of the Ark of the Covenant, in the Holy of Holies The high priest then removed his ceremonial linen garments*** When Jesus Christ was crucified all four of his priestly garments were removed
    The Temple Sacrifice happened every year on the Day of Atonement ** Jesus Christ was crucified on Passover, AD 33, on one occasion only***
    On the Day of Atonement the high priest made atonement for the Jewish people *** On the Day of Crucifixion, Jesus Christ died for the sins of the whole world***
    By Rabbinic tradition, the high priest spent 3 hours in the Holy of Holies, in the pitch darkness*** Jesus Christ spent 3 hours in total darkness on the Cross, and the darkness was world wide***
    During this 3 hour period, God appeared in Shekinah Glory between the Cherubim, over the Mercy Seat*** During this 3 hour period, Jesus Christ was rejected by God the Father, and atoned for the sins of the world***
    By Rabbinic tradition, at the end of this period of 3 hours, the high priest stood up and said, "It is finished" ***At 3 pm, after 3 hours of darkness all over the world, Jesus Christ stood up on the Cross to announce His 7th announcement from the Cross. He said, "It is finished".ሊቀ ካህናት ሊባል የተገባው ፍፁም ሰው መሆኑን ለማጠየቅ በእውነተኛይቱ ሰው በማይገባባት ቅድስተ ቅዱሳን (መስቀል) አንድ ጊዜ ብቻ ስለገባ ፡ በእርሷም እውነተኛውን መስዋእቱን (ራሱን) ስላቀረበና ሃጢአተ አለምን ስላራቀ ነው

    ReplyDelete
  9. honom andmeta tirguamew ena andand yitent abatoch geta yegebabat debteradinkuan meskel endehone neger gin geta leabatu yetayebet kideste kidusan getse ab endhone adrgo tergumotal wendeme yetsfew yihen yandmeta tirguame hasab teketlo enji yeneaba selama aynet tehadsowochin hassab teketlo aydelem

    ReplyDelete
  10. beterfe yanchin asteyayet teketlo sile kidusan milja...etc bithu endemiyasnebeben tesfa adrgalehu

    ReplyDelete
  11. betam tiru milash new yesetehegn.Egziabher yistilegn!ante enidalikew kehone le'eminetachin ande ye'jeriba atint yemihon'na hulachinem yeminimaribet blog yihonal biye aminalew.
    Ene facebook lay wede 4000 memeber alew group alegn.engdih blogun eyeteketateliku tewahdo hayimanotachenen yemiyatenakir neger sagegn share aderigalew.
    Ahunem bihon gin mezenigat yelelebachew negeroch
    1,ye tewahdo hizbun eyadenegageru yalu negerochin tegebi yemibalewun milash be'blogih mesitet yeteketatay kutirihen enidemiyasadigut new.
    2.ahun betam achekachaki yehonutin negeroch
    -ye'melaekit ena ye'kidusan milja
    -ye melaekit ena ye'kidusan milja be'atsede siga'na be'atsede nefis
    -ye'emebetachin milja be'atsede siga ena nefis
    -tabot be'bluy kidan ena be'addis kidan
    -tsom-ye'awaj tsom'na ye'gil tsom
    -kirstos manew(ende orthodox tewahdo abatoch timiret meseret)
    -kirstos Amalaj new yemilut ye metsihaf kidus tiksoch ewunetegna tirgumachew
    -ye kidus paulos andimta beteley Ebrawiyan Meliekit lay
    Enezihen enz leloch wektawi'na afatagn milash yemishu gudayoch'n memeles yemichil blog kehone Egziabher miskire new abiren tebabiren enasadigewalen.
    EGZIABHER BE'WENDIMACHIN LAY ADIRO EWUNETUN YASITEMIREN KE'GNA GAR ABIRO YIHUN!
    Wesibhat le'egziabher
    Weweladitu dingel!

    ReplyDelete