Pages

Thursday, August 9, 2012

ከሕዝቡ ግን ብዙዎች አመኑበት- የዮሐንስ ወንጌል የ34ኛ ሳምንት ጥናት


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

  ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ካላቸው እይታ አንጻር የሥነ መለኰት ምሁራን አይሁድን በሦስት ምድብ ይመብዋቸዋል፡፡ አንደኛው ምድብ የአለቆች፣ የካህናትና የፈሪሳውያን ምድብ ሲሆኑ እነርሱም ለክርስቶስ ፍጹም ጥላቻ የነበራቸው ናቸው፡፡ ሁለተኛው ምድብ ደግሞ በኢየሩሳሌም ውስጥ የሚኖሩና በአንደኛው ምድብ ባየናቸው ቡድኖች ጥላቻ ግራ የተጋቡ ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች የአለቆቻቸውን ጥላቻ ቢያውቁም ጌታ በሚያደርጋቸው ገቢረ ተአምራት ፍጹም የሚማረኩ ናቸው፡፡ ጌታን ለአለቆቻቸው አሳልፈው እንዳይሰጡት በሚያስተምራቸው ትምህርት፣ በሚያሳያቸው ፍቅር፣ በሚያደርግላቸው ምልክት ልባቸው የተወሰዱ ናቸው፡፡ ሦስተኛው ምድብ ደግሞ ከኢየሩሳሌም ውጪ የሚኖሩ ናቸው፡፡ እነዚህ ከኢየሩሳሌም ውጪ የሚኖሩ አይሁዳውያን ለገቢረ በዓል ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጡ በክርስቶስ እጅግ የተማረኩና በምድብ አንድ ያየናቸውን አለቆች ስሜት የማያውቁ ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች አለቆች ክርስቶስን ሊገድሉት እንደሚፈልጉ ሲሰሙ በእጅጉ የተደናገጡና በአለቆቹ ክፉ ሥራ ግርምት ውስጥ የገቡ ናቸው /Fr.Tadros Malaty,Commentary on the Gospel of John,pp359/፡፡

  አሁን ወንጌላዊው እየነገረን ያለው የሁለተኛው ምድብ የሆኑ ሰዎች ስሜት ነው፡፡ “እንግዲህ ከኢየሩሳሌም ሰዎች አንዳንዶቹ እንዲህ አሉ፡- ሊገድሉት የሚፈልጉት ይህ አይደለምን? እነሆም፥ በግልጥ ይናገራል አንዳችም አይሉትም። አለቆቹ ይህ ሰው በእውነት ክርስቶስ እንደ ሆነ በእውነት አወቁን? ነገር ግን ይህን ከወዴት እንደ ሆነ አውቀናል፤ ክርስቶስ ሲመጣ ግን ከወዴት እንደ ሆነ ማንም አያውቅም” እንዲል /ቁ.25-27/። እንዲህ ማለታቸው ነበር፡-“አለቆቻችን እንገድለዋለን ብለው የሚዝቱበት ይህ አሁን በድብቅ ያይደለ በይፋ በስውር ያይደለ በግልጥ የሚያስተምራቸው አይደለምን? እነሆ፡- ከእናንተ ሕግን የሚያደርግ አንድ ስንኳ የለም ብሎ በግልጥ ይናገራል /ቁ.19/፤ ሆኖም ግን አንዳች ስንኳ አይሉትም፡፡ ወይስ ይህ ሰው በእውነት ክርስቶስ እንደሆነ አውቀዋል ማለት ነው? ይህ አሁን የሚናገረው ሰውዬ (ሎቱ ስብሐትና) ከቤተ ልሔም እንደተወለደ የቀራጩ የዮሴፍም ልጅ እንደሆነ እናውቃለን /ማቴ.2፡4/፡፡ ክርስቶስ ሲመጣ ግን ኢሳይያስ፡- ትውልዱን ማን ይናገራል ብሎ እንደተናገረ ማንም አያውቅም” /ኢሳ.53፡8፣ Saint Cyril the Great/፡፡

 የእነዚህ ሰዎች ችግር ነቢዩ ኢሳይያስ የተናገረው ቃል ለቀዳማዊ ልደቱ ከማድረግ ይልቅ ለደኃራዊ ልደቱ አድርገው መረዳታቸው ነው፡፡ ነቢያቱ ግን እንዲህ የቀዳማዊ ልደቱ አይመረመሬነት እንደተናገሩ ሁሉ /ኢሳ.53፡8/ ሰው ሆኖ ከድንግል እንደሚወለድም በግልጽ ቦታውን ሳይቀር ጨምረው ተናግረዋል /ኢሳ.7፡14፣ ሚክ.5፡2/፡፡

   ከዚህ በኋላ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመቅደስ ሲያስተምር፡-እኔንም ታውቁኛላችሁ ከወዴትም እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ፤ እኔም በራሴ አልመጣሁም ነገር ግን እናንተ የማታውቁት የላከኝ እውነተኛ ነው፤ እኔ ግን ከእርሱ ዘንድ ነኝ እርሱም ልኮኛልና አውቀዋለሁ” ብሎ ጮኸ /ቁ.28-29/። እንዲህ ማለቱ ነበር፡- “ጀሮ ያለው መስማትን ይስማ፤ ነቢያት አብዝተው እንደነገሯችሁ ከወዴት እንደሆንኩ (ናዝሬት ገሊላ እንዳደግኩ)፣ ከወዴት እንደተወለድኩ (ከቤተልሔም እንደተወለድኩ)፣ ከማን ወገን እንደተወለድኩ (ከዳዊት ወገን እንደተወለድኩ) ታውቃላችሁ፡፡ ሆኖም ግን ከአብ ባሕርይ ዘእምባሕርይ አካል ዘእምአካል የተወለድኩትን ቀዳማዊ ልደቴን ጨምረው የነገርዋችሁን አታውቁም ብዬ በእውነት እነግራችኋለሁ፤ ይህን ከማመን ይህን ከመቀበል በፍቃዳችሁ ተከልክላችኋል ብዬ በእውነት ያለ ሐሰት እነግራችኋለሁ/St. John Chrysostom, Hom 50./፡፡ በእኔ ፈቃድ ብቻ ያይደለ በበአባቴም ፈቃድ ሰው ሆኛለሁና እርሱን ብታምኑበት እኔም ከእውነት የተወለድኩ እውነት እንደሆንኩ ባወቃችሁ ባመናችሁ ነበር፡፡ ደጋግሜ እንደነገርኳችሁ እኔ በህልውና ያየሁትን ነገርኳችሁ እንጂ አብን በባሕርይው ያየው አንድ ስንኳ የለም /ዮሐ.1፡18/፡፡ እኔ ልገልጽለት ያልፈቀደ፣ በእኔ ያላመነ ሁሉ አብን ሊያየው ሊያውቀው የሚችል እንደሌለ በእውነት እነግራችኋለሁ፤ ወልድን ያየ ግን አብን አይቷል ብዬ በእውነት ያለ ሐሰት እነግራችኋለሁ” /ዮሐ.14፡9፣ Augustine, On the Gospel of St. John, tractate 31/፡፡  

  ፈሪሳውያን ግን እንዲህ ስለተናገረ ሊይዙት ይፈልጉ ነበር፤ ከማር በሚጣፍጠው መለኰታዊ ቃሉ የሕዝቡን ልብ እንደወሰደ ወደ እውነትም እንደመለሰ ሲያውቁ ሊገድሉት ይፈልጉ ነበር፡፡ ነገር ግን ጊዜው ገና ስላልደረሰ የሚሰቀልበት ሰዓት ስላልደረሰ በመለኰታዊ ሥልጣኑ ይህን እንዳያደርጉ ከለከላቸው፤ ስለዚህ ማንም እጁን አልጫነበትም /ቁ.30/።

  የፈሪሳውያን ቁጣ እየበዛ በሄደ ቁጥር ሕዝቡም እውነቱን እየተረዳ እያወቀ መጣ፡፡ ነገር ሁሉ ግልጽ እየሆነለት መጣ፡፡ ስለዚህ ከሕዝቡ ብዙዎች አመኑበት፡፡ ያመኑትም ሕዝብ እንዲህ ብለው ተነጋገሩ፡-አይሆንም አይደረግም እንጂ አለቆቻችን ይመጣል ብለው የሚነግሩን ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ይህ አሁን ያመንንበት ክርስቶስ ካደረጋቸው ምልክቶች በላይ ተአምራትን ያደርጋልን?” /ቁ.31/፡፡ የሚደንቅ ነው! ሕሙማነ ሥጋ በተአምራት ሕሙማነ ነፍስም በትምህርት ሲፈውሳቸው በዙርያ የነበሩ ድሆች አመንዝሮችና ቀራጮች አመኑበት፡፡ እናውቃለን ከሚሉት እረኞች ይልቅ የተበደሉት ሰዎች ዳኑበት፡፡ ቁስላቸውን ፈወሱበት፡፡ ስብራታቸውን ጠገኑበት፡፡ ተስፋቸውን ቀጠሉበት፡፡ ከውድቀታቸው ተነሡበት፡፡ አለቆች ነን ባዮቹ ግን አንዳችም ሳይጠቀሙ ከነደዌአቸው ቀሩ፤ ወደ ሐኪማቸው ከመቅረብ ተከለከሉ፤ ይባስ ብለውም ሊገድሉት ፈለጉ፡፡
  ሕዝቡ ሰለ ክርስቶስ እንደዚህ ሲነጋገሩ ሲሰሙም ሎሌዎቻቸውን ላኩ /ቁ.32/። ሰው ወዳጁ ጌታ … ሰው አፍቃሪው ንጉሥ ግን እንዲህ አላቸው፡-“ፈሪሳውያን ሆይ! በዚህ ዓለም ከእናንተ ጋር ብዙ እንደምቆይ ስለምን ትቆጣላችሁ? ሸክም እንደሆንኩባችሁ አውቃለሁ፡፡ ክፋታችሁን በእውነት ስለምናገርባችሁ አውቃለሁ፡፡ ሰላም እንደነሣኋችሁ አውቃለሁ፡፡ ሆኖም ግን እኔ ሳልፈቅድላችሁ ማድረግ አትችሉምና ጊዜዬ ሳይደርስ እኔን ለመግደል በከንቱ የምትደክሙ አትሁኑ፡፡ በቅናትና በቁጣ ተነሳሥታችሁ እኔን ለመግደል የምትቻኮሉ አትሁኑ፡፡ ድኅነተ ዓለም የምፈጽምባትን የእኔን ሰዓት፣ በእኔ ዘላለማዊ ዕቅድ ውስጥ ያለችውና መከራ መስቀልን የምቀበልባት ያቺ ሰዓት ስትደርስ በፈቃዴ፣ ወድጄ ራሴን እሰጣችኋለሁ፡፡ ከዚያን ጊዜ በኋላ ግን ሥራችሁ ክፉ ነውና ፈጽሞ አታገኙኝም፤ በጨለማ መኖርን የምትወዱ ናችሁና ወደ ብርሃን መውጣት የማትፈልጉ ናችሁና ስለዚሁ በእናንተ ዘንድ የማድር የምዋሐድ አይደለሁምና አታገኙኝም፡፡ አንድም ጥጦስ መከራ ሲያደርስባችሁ ትሹኛችሁ፤ አታገኙኝም፡፡ አንድም ጻድቃንን ልፈርድላቸው ኃጥአንን ልፈርድባቸው በመጣሁ ጊዜ አምነንበት ቢሆን ብላችሁ ትፈልግኛላቹ፤ አታገኙኝም፡፡ መንገዱም እውነቱም እኔ ነኝና በእኔ ሳታምኑ ተድላ ደስታ ወዳለባት መንግሥተ ሰማያት መምጣት አይቻላችሁምና አታገኙኝም፡፡ ፈሪሳውያን ሆይ! ጥቅም በሌለው ምክር ራሳችሁን የምታጎሳቁሉ አትሁኑ፡፡ አለቆች ሆይ! መከራ ነፍስ የሚያመጣባችሁ ነውና ቁጣችሁን ወደ ሰገባው መልሱት፡፡ በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ በመዳንም ቀን ረዳሁህ ይላልና እነሆ የተወደደ ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ የመዳን ቀን አሁን ነው /2ቆሮ.6:2/፡፡ አትሳቱ! ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና የዘለዓለምን ሕይወት ታጭዱ ዘንድ በመንፈስ የምትዘሩ ሁኑ /ገላ.6፡7-8/፤ በእኔ እመኑ በአባቴም እመኑ፡፡ እኔስ ሞታችሁን እገድል ዘንድ እናውቀዋለን ከምትሉት ሆኖም ግን ከማታውቁት ከአባቴ ዘንድ መጥቻለሁና፣ ሕይወት ይሆንላቸው ዘንድ ለወደዱ ሕይወትን እሰጣቸው ዘንድ ሰው ሆኛለሁና ሞት በእኔ ላይ ሥልጣን የለውም፡፡ ሰዓቱ ሲደርስ ግን የሲዖል የምሥጢር በሮችን እሰባብራለሁ፡፡ ምርኮን እማርካለሁ፡፡ ስለዚህ እናንተ እንደምታስቡት ፈጥነንም እናስወግደው እንደምትሉት በመቃብር በስብሼ የምቀር አይደለሁም፡፡ ከሙታን ተለይቼ እነሣለሁ እንጂ፡፡ መነሣትም ብቻ ሳይሆን ደቀመዛሙርቴ እያዩኝ በይባቤ መላዕክት በቅዳሴ በብርሃን በሥልጣን ዐርጋለሁ /መዝ.46፡5/፡፡ ያኔ ሰዎች ዕርገቴን አይተው ያደንቃሉ፤ መላእክትም፡-“ይህ በእጅህ መካከል ያለ ቁስል ምንድነው?” ይሉኛል፤ እኔም “በወዳጆቼ ቤት የቆሰልኩት ቁስል ነው” እላቸዋለሁ /ቁ.33-34፣ ዘካ.13፡6፣ St. Augustine: On the Gospel of St. John, tractate 31:9/፡፡

  ከዚህ በኋላ አይሁድ፡-እኛ እንዳናገኘው ይህ ወዴት ይሄድ ዘንድ አለው? በግሪክ ሰዎች መካከል ተበትነው ወደሚኖሩት ሊሄድና የግሪክን ሰዎች ሊያስተምር አለውን? እርሱ። ትፈልጉኛላችሁ አታገኙኝምም እኔም ወዳለሁበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም የሚለው ይህ ቃል ምንድር ነው?” ብለው እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ /ቁ.35-36/።

  ቸርነትህ የበዛ አፍቃሪያችን ሆይ! በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበን፡፡ ቀን ሳለልን በብርሃን እንድንመላለስ እርዳን፡፡ ዓለምን ለማሳለፍ በመጣህ ጊዜ ያ የቀመስነውና የለመድነው የፍቅር ፊትህ በምግባራችን ክፋት እንዳይለወጥብን ዛሬ ላይ በምግባር በትሩፋት እንድንመላለስ እርዳን፡፡ ሙሽራችን ሆይ! ዘይታችን አልቆ ከውጭ ከሚቀሩ ቆነጃጅት እንዳንሆን ደግፈን፡፡ የአባቴ ብሩካን ከምትላቸው ወዳጆችህ ጋር ደምረን፡፡ አሜን በእውነት አሜን!!!!!!!

5 comments:

  1. kale hiwot yassemalgh .........................kalbegebahut.....meseret..Sacrificial System of the OT....It is important to understand a couple things about the sacrificial system of the Old Testament. The first thing to note is that all the sacrifices were pointing to a future reality. Their value lay in the concept of "icon" as understood in Orthodoxy. They were essentially windows that allowed those prior to Christ to participate in His sacrifice by faith through these icons.Heb 9:9-14 temple and its sacrifices were "copies" or shadows of the heavenly one. They point to the reality. The only power of those animal sacrifices to accomplish anything in the people that preformed them was in Christ making it effective through His sacrifice. Therefore, it is important to keep in mind that the blood itself of the sacrifices could do nothing to help those who offered it.God did not desire sacrifices at times because instead of pointing to Christ, the people did them as if the act itself had power to forgiven and heal. Psa 51:16-17,Hos 6:6,Mat9:13,Psa 40:6The required blood to forgive sins is not the animal's but Christ's blood. They did not need the icon of the sacrifice if it did not point to the reality. This is important to remember because some theologies would have these sacrifices actually accomplishing forgiveness of sins because of the blood of the animal rather than the blood of Christ.So, what is it about the blood?To understand where blood fits into the sacrificial system, we must first go back even before that was instituted to see what "blood" represented. ኦሪት ዘሌዋውያን 17; 10፤ ከእስራኤልም ልጆች ወይም በመካከላቸው ከሚኖሩ እንግዶች ማናቸውም ሰው ደም ቢበላ፥ ደም በሚበላው በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከብድበታለሁ፥ ያንንም ሰው ከሕዝቡ ለይቼ አጠፋዋለሁ።notice the restriction God places from the very beginning on drinking the blood of any life.This is important in understanding the roll of blood in our salvation.The other important piece of information is that the blood contains the life of the animal.ኦሪት ዘሌዋውያን 17;14 የሥጋ ሁሉ ሕይወትና ደሙ አንድ ነውና God tells them in many of the sacrifices to eat the flesh but not to drink the blood. The sacrifice, which defines all sacrifices in the Old Testament, is the Passover sacrifice.Exo 12:7-8, 12-13 And the blood shall be to you for a token upon the houses where ye are: and when I see the blood, I will pass over you, and there shall no plague be upon you to destroy you, when I smite the land of Egypt.The life of the blood was to give life to those under it. The life of the blood was to counter death....

    ReplyDelete
  2. .....Sin is what causes death to our souls, both our own sins and the sin of Adam, which has passed down this death from the beginning. The life defeats death, but the only life that is able to do this is God's life. Therefore, these animal sacrifices point to the one life that can give our souls new life and defeat death.Jesus' crucifixion happening at the same time the Passover lambs are slaughtered. St. Paul also has this very much in mind:1ኛ ቆሮንቶስ5;7 ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና፤Indeed, from the beginning of the Church, the celebration of the Resurrection of Christ was called "Passover" by using the Greek transliteration of the Hebrew term for Passover, "Pascha".Notice The people were to eat the sacrifice at their home, not in the temple even. As we have noted, however, they did not drink the blood, but put it upon the doorpost of the dwelling. notice a key change when we come to what Christ says:ዮሐ6;53 ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም።

    54 ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።

    55 ሥጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና። ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ።Here Christ tells us not just to eat His flesh, but also to drink His blood in order to have life. This is the only time in the whole Bible God tells us to drink blood. Why? Because only Christ's blood contains the life that can actually give us life and defeat death. How are we to drink this blood and eat this flesh? By sacrificing his body so that the blood may flow. By becoming one of us, with divine life, He is able to defeat death and gives us a means to unite to His life......www.orthodoxconvert.

    ReplyDelete
  3. .... By becoming one of us, with divine life, He is able to defeat death and gives us a means to unite to His life once again. ዕብራውያን 2:14እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ።the sacrifices were pointing to the life of His blood by which we can unite to His life. By this life, death is defeated, but to unite with Christ, first He had to be broken so that we could partake of Him.1ኛቆሮ10:15-18የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን?

    17 አንድ እንጀራ ስለ ሆነ፥ እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን፤ ሁላችን ያን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና።

    18 በሥጋ የሆነውን እስራኤል ተመልከቱ፤ መሥዋዕቱን የሚበሉ የመሠዊያው ማኅበረተኞች አይደሉምን?The fact that the Israelites ate from the altar and by doing so participated in the sacrifice, so partaking of Christ in the Eucharist is a participation in the life of Christ. This union to Christ by grace is what saves us.God's forgiveness of our sins becomes a complete when God needs to free us from the bondage of death.Until we have that life in us, God's forgiveness is only an unrealized potential. Accepting His forgiveness freely offered is to unite to Him and live in Him. We do that through the partaking of the blood of Christ and having death pass over us. since We are not justified to the Law; rather, the Law shows us our sin and indicates to us the gravity of our situation. The Law cannot give us the solution to our problem; it can only show us the problem.That is why the Orthodoxy understanding of salvation is the union with Christ who is our life; having faith in Him as the source of salvation. Not simply that He accomplishes it for us, but that He Himself is our salvation and not the fulfilling of the Law.We see this when Christ was asked what is the most important commandment. He told us that love of God and each other, relationship to Him, is the key. Fulfill that and you fulfill all the Law and the Prophets. Ironically, by uniting to Christ, we fulfill the Law as well for it is that union to which the Law points.it is clear that the reason many Protestants see Orthodoxy as not focusing on forgiveness ,but in orthodoxy understanding of salvation This forgiveness not only involves a reconciliation of the relationship to God, but the freeing of our souls from the bondage of death. God saves us by uniting us to the person of Jesus Christ and not by Him(protestants veiw) or us(JEWsveiw) meeting the demands of the Law.He fulfills the Law, yes, but righteousness comes through faith in Christ, not through faith in the fulfilling of the Law. It is the establishing of a right relationship with Christ and God that makes us righteous, not the fulfilling of the Law itself.ሮሜ4:13-16 የዓለምም ወራሽ እንዲሆን ለአብርሃምና ለዘሩ የተሰጠው የተስፋ ቃል በእምነት ጽድቅ ነው እንጂ በሕግ አይደለም።

    14 ከሕግ የሆኑትስ ወራሾች ከሆኑ እምነት ከንቱ ሆኖአል የተስፋውም ቃል ተሽሮአል፤

    15 ሕጉ መቅሠፍትን ያደርጋልና፤ ነገር ግን ሕግ በሌለበት መተላለፍ የለም።

    16-17 ስለዚህ ከሕግ ብቻ ሳይሆን ከአብርሃም እምነት ደግሞ ለሆነ ለዘሩ ሁሉ የተስፋው ቃል እንዲጸና እንደ ጸጋ ይሆን ዘንድ በእምነት ነው protestants understanding is meaningless as if the judge said to someone he just declared "not guilty," "Take him back to his prison cell." What good does such forgiveness do if one remains in bondage?....www.orthodoxconvert

    ReplyDelete
  4. ..... but why the protestant understand is meaningless....የዮሐንስ ራእይ 3 5 ድል የነሣው እንዲሁ በነጭ ልብስ ይጐናጸፋል፥ ስሙንም ከሕይወት መጽሐፍ አልደመስስም፥ በአባቴና በመላእክቱም ፊት ለስሙ እመሰክርለታለሁ። 6 መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ።መልዕክቱ እንግዲህ ለአብያተ ክርስቲያናት ማለትም በክርስቶስ አምነው ለዳኑና ክርስቶስም የእኔ ናቸው ለሚላቸው አማኖች የተላከ ነው።

    በዚሁ ለአማኞች በተላከ መልዕክት ጌታ ሲናገር "ድል የነሣው እንዲሁ በነጭ ልብስ ይጐናጸፋል፥ ስሙንም ከሕይወት መጽሐፍ አልደመስስም" ይላል። ይህ ክፍል ያለ ጥርጥር የሚያሳየን በሕይወት መጽሐፍ መጻፍ እንዳለ ሁሉ፡ ከሕይወት መጽሐፍ መደምሰስም እንዳለ ነው።የዮሐንስ ወንጌል15
    1 እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፤ ገበሬውም አባቴ ነው። 2 ፍሬ የማያፈራውን በእኔ ያለውን ቅርንጫፍ ሁሉ ያስወግደዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውንም ሁሉ አብዝቶ እንዲያፈራ ያጠራዋል። 3 እናንተ ስለ ነገርኋችሁ ቃል አሁን ንጹሐን ናችሁ፤ 4 በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም። 5 እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል። 6 በእኔ የማይኖር ቢሆን እንደ ቅርንጫፍ ወደ ውጭ ይጣላል ይደርቅማል፤ እነርሱንም ሰብስበው ወደ እሳት ይጥሉአቸዋል፥ ያቃጥሉአቸውማል።

    በዚህ ክፍል ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን እንደ እውነተኛ የወይን ግንድ ይመስላል። አብን ደግሞ እንደ የወይኑ ገበሬ። አማኞችን ደግሞ በወይኑ ግንድ ማለትም በክርስቶስ ላይ እንዳሉ ቅርንጫፎች። በዚህ ክፍል ጌታ ሊያስተላልፈው የሚፈልገው መልዕክት ያለ ክርስቶስ አማኞች ከግንዱ እንደ ተለየ ቅርንጫፍ ብቻቸውን ሕይወት ሊኖራቸው እንደማይችልና ያለ ክርስቶስ ሊያፈሩ እንደማይችሉ ነው።

    በቁጥር ሁለት ላይ ጌታ "ፍሬ የማያፈራውን በእኔ ያለውን ቅርንጫፍ ሁሉ ያስወግደዋል“ ይላል። ልክ ቅርንጫፍ ከግንዱ ሊቆረጥ እንደሚችል እንዲሁ ከክርስቶስ መወገድ ወይም መቆረጥ እንዳለ በግልጽ ያሳየናል። መወገድ ብቻ ሳይሆን ከመወገድ ጋር ተያይዞ ደግሞ መድረቅና ተሰብስቦ ወደ እሳት መጣል እንዳለም በቁጥር 6 ያስጠነቅቃል። "በእኔ የማይኖር ቢሆን እንደ ቅርንጫፍ ወደ ውጭ ይጣላል ይደርቅማል፤ እነርሱንም ሰብስበው ወደ እሳት ይጥሉአቸዋል፥ ያቃጥሉአቸውማል።" እዚህ ጋር ልብ ማለት ያለብን ከክርስቶስ ስለመወገድ፡ ወደ ውጭ ስለመጣል እንዲሁም በእሳት ስለመቃጠል ጌታ የሚያወራው በዓለም ስላሉ ዓለማውያን ሳይሆን በክርስቶስ ስላሉ ቅርንጫፎች ማለትም ስለ አማኞች ነው።

    ሰው ወንጌልን ተቀብሎ ከዳነ በኋላ ደህንነቱን ሊያጣ እንደሚችል የሚያስጠነቅቀን ሌላው ክፍል የሚገኘው ደግሞ በዕብራውያን 10 ላይ ነው።
    Quote:
    ወደ ዕብራውያን 10
    26 የእውነትን እውቀት ከተቀበልን በኋላ ወደን ኃጢአት ብናደርግ ከእንግዲህ ወዲህ ስለ ኃጢአት መሥዋዕት አይቀርልንምና፥ 27 የሚያስፈራ ግን የፍርድ መጠበቅ ተቃዋሚዎችንም ሊበላ ያለው የእሳት ብርታት አለ። 28 የሙሴን ሕግ የናቀ ሰው ሁለት ወይም ሦስት ቢመሰክሩበት ያለ ርኅራኄ ይሞታል፤ 29 የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ ያንንም የተቀደሰበትን የኪዳኑን ደም እንደ ርኵስ ነገር የቆጠረ የጸጋውንም መንፈስ ያክፋፋ፥ እንዴት ይልቅ የሚብስ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል? 30 በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ ያለውን እናውቃለንና፤ ደግሞም፦ ጌታ በሕዝቡ ይፈርዳል። 31 በሕያው እግዚአብሔር እጅ መውደቅ የሚያስፈራ ነው።

    ይህ ክፍል ከዳኑ በኋላ ወደው ወይም ሆን ብለው ኃጥያትን ለሚለማመዱ ሰዎች የተሰጠ ማስጠንቀቂያ ነው። ወንጌልን ተቀብለው ንስሐ ከገቡና በክርስቶስ መሥዋዕት ምህረትን ካገኙ በኋላ ወደው ኃጥያትን የሚለማመዱ ከእንግዲህ ወዲህ መሥዋዕት እንደማይቀርላቸውና ይልቁንም የሚያስፈራ ፍርድ እንደሚጠብቃቸው የሚያሳይ ክፍል ነው። እንደነዚህ አይነት ሰዎች ስለሚጠብቃቸው ፍርድም ሲናገር "ተቃዋሚዎችንም ሊበላ ያለው የእሳት ብርታት“ ይላል። አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ክፍል "የሚቀረው ግን የሚያስፈራ ፍርድና የእግዚአብሔርን ጠላቶች የሚበላ ብርቱ እሳት መጠበቅ ብቻ ነው።“ ይለዋል።
    Quote:
    ወደ ዕብራውያን 10 (አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
    26 የእውነትን እውቀት ከተቀበልን በኋላ ሆን ብለን በኅጢአት ጸንተን ብንመላለስ፤ ከእንግዲህ ለኅጢአት የሚሆን ሌላ መሥዋእት አይኖርም። 27 የሚቀረው ግን የሚያስፈራ ፍርድና የእግዚአብሔርን ጠላቶች የሚበላ ብርቱ እሳት መጠበቅ ብቻ ነው።"ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንጸጋው ሃጢያተኝነትን ክደን እግዚአብሔርን በመምሰል እንድንኖር የሚያስችል ሃይል ነው እንጂ በኃጢአት እንድንጨማለቅ የሚገፋፋና የሚጋብዝ ሃሰተኛ መንፈስ አይደለም። ከጸጋ በታች ሆንን ወይም ጸጋው በዛልን ማለት፤ ኃጢአት አይገዛንም፣ ኃጢአትን ድል እንድናደርግ ያስችለናል ማለት ነው እንጂ በኃጢአት ጸንቶ መኖር ማለት አይደለም የጸጋ መብዛት ምልክት፤ እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ፦
    Quote:
    ወደ ሮሜ ሰዎች
    6፥14 ኃጢአት አይገዛችሁምና፤ ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች አይደላችሁምና።
    6፥15 እንግዲህ ምን ይሁን? ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች ስላይደለን ኃጢአትን እንሥራን? አይደለም።ም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤" ቲቶ 2፥12-13ከኋጢአት ንስሐ ሊገቡ የማይፈልጉና በኃጢአት ጸንተው የሚኖሩ የዘላለም ሕይወት አይወርሱም። ሰው ደግሞ በክርስቶስ ከሆነ በኋላም በፈቃዱ በኋጢአት ተፈትኖ ወይም የዚህ ዘመን የዓለም ኑሮ አታልሎት ከክርስቶስ ሊለይ ይችላል። ያለዚያማ ሰይጣን ለምን ይፈትነናል እኛ ፈጽሞ ልንወድቅ የማንችል ከሆነ? ሰው እምነቱንም እንኳን ሊያጣ ይችላል። ከዳነበትና ከተመዘገበበት ከህይወት መጽሐፍ ሊደመሰስ ይችላል።thats is why protestant understanding is meaningless.iyesus.com

    ReplyDelete
  5. but what was orthodox understanding? God wishes to work in us and through us, not over and above us. He wants to work with us in a relationship of love and joy. Thus, when Jesus ask them what they should do, they say that we need to send the people away. But Christ, who could have turned the bread into stone before their eyes and amazed the crowds with such a miracle, instead tells the disciples to feed them.

    What do they have? Five loaves and two fish which is hardly enough for my own family. I have a wife and three kids, one a teenager, so you know what I'm taking about. There was no way that this little food was enough to feed that crowd. Yet, Jesus does not despise it. He does not cast it aside as negating His divine power and grace. Rather, He takes what we offer Him and by grace makes it sufficient for the job it needs to do. In all our lives, this is our relationship with our "works". They are totally insufficient to gain us points with God, they would not even pay for one brick in a heavenly mansion. However, in God's grace, our "works" offered to Him do not return void, but obtain for us eternal value and reward in union with God.ጸጋው ግን ኃጢአትን ድል አድርጎ ለመኖር የሚያስችል ኃይል ነው እንጂ ጸጋ ማስተማር ማለት ምንም ብታደርግ ድነትህን አታጣውም እያሉ ወደ ኃጢአት ሰዎችን በተዘዋዋሪ መገፋፋት ማለት አይደለም። የትም ቦታ ጸጋው እንደፈለጋችሁ ብትኖሩም ድነታችሁን አታጡትም ብሎ አያስተምርምiyesus .com ወደ ሮሜ ሰዎች
    8፥13 እንደ ሥጋ ፈቃድ ብትኖሩ ትሞቱ ዘንድ አላችሁና፤ በመንፈስ ግን የሰውነትን ሥራ ብትገድሉ በሕይወት ትኖራላችሁ።
    ገላትያ ሰዎች 6
    7 አትሳቱ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና፤
    8 በገዛ ሥጋው የሚዘራ ከሥጋ መበስበስን ያጭዳልና፥ በመንፈስ ግን የሚዘራው ከመንፈስ የዘላለምን ሕይወት ያጭዳል።There is no work of man that is of value in and of itself apart from God's grace. But we have been created to have a grace of God within us. The fall did not totally destroy that which God had done in us. Though we lost the likeness to God because of death, we retained the image by which we could still respond to God not as a senseless animal, but as one who can commune in love with Him. In Himself, the unknowable God has made us living images of His glory that we might commune with Him in it. In this He maintains His complete control and yet does not violate thereby our free will to accept or reject His love for us. He wants all men to be saved, and it is His will that not one of these little ones should perish. There is not an arbirary decision on God's part, based completely separate from our inner spirit, to chose who would be saved and who would not. Those who are the "chosen" are those who respond in their hearts to the grace of God around them.http://www.orthodoxconvert.info/ grace and invest it in their lives, to take action, IOW, to work out your salvation in fear and trembling. So when the master returns, the only one who really gets in trouble is not the one who earned less, and even the one who earned nothing, you do not get the impression that it was because of this he stood condemned. It was because he failed to invest that which he had been given into his life.Mat 25:14-30www.orthodoxconvert.

    ReplyDelete