Pages

Wednesday, February 26, 2014

ዘወረደ ዘረቡዕ




በዲ/ን ስመኘው ጌትዬ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ የካቲት 18፣ 2006 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ ጸልዩ እምቅድመ ንባበ ዝንቱ ክርታስ

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን ። በክርስቶስ ወገኖቼ የሆናችሁ ተወዳጆች በትናንት የማክሰኞ ድርሰቱ አባታችን ቅዱስ ያሬድ በፍቅርና በትህትና እንጹም ብሎ ጀምሮ በጾም ከአለም ልቀን ከፍ ከፍ እንድንል መክሮ ሳይተወን ከፍ ከፍ ማለታችን ደግሞ ምድራዊ ሕዋሳቶቻችንን ሁሉ በማጾም እንደሰማያዊ እንድንሆን ነው ካለን በኋላ በመጨረሻም በክርስቶስ መርቆን ተለያየን። ዛሬ በዕለተ ረቡዕ የሚያዜመውን ከዝማሜው ጋር እንደወትሮው ነፍሳችን ትሰማው ዘንድ እየጸለይን እንቀጥላለን።

ባለፉት ቀናት ስለ ጾም ጸጋ ፣ እንዴት እንዲጾም በጥቂቱ ነግሮናል አሁንም ከማያልቀው ሰማያዊ እውቀት እንዲህ ሊገስጸን ጀመረ።አንተስ አስቀድመህ ራስህን መርምርየምን ምርመራ ነው ?ስጋዊ ምርመራ አይደለም የነፍስ ህመምን እንጂ ። ወገኖቼ የጾምን በር ሳናንኳኳ አንከፍትም። ለመግባት ግን እንድንገባ ሆነን መገኘት አለብን ። ከኃጢአታችን ጋር ከበደላችን ጋር ሆነን አንገባም። ያለፈውን ተነሥኸን ያቀድነውን ኃጢአት ቀጠሮ ሰርዘን ራሳችንን የተገባ ካደረግን በኋላ የበሩን ደወል እንጫን ። አሁን ከራሳችን ጋር ከምርመራ በኋላ ታርቀናል። ቀጣዩን እርሱ ያዚምልንጹም ለእግዚአብሔርም ተገዛሰኞ እለትም እንዲሁ ብሎን ነበረ። በእውነት ዜማው ግን ይለያል፣ ቃናው ግን ይጥማል ...ዲስ ነው። ቃለ እግዚአብሔር እለት እለት አዲስ ነው ይሉታል ይህ ነው።

እንቀጥልበምሥጋና ላይ እንግዳ (ወንድም) መውደድን ጨምር፡፡አስቀድሞ አመስግኑ ሳይለን ምስጋና ላይ መውደድ ጨምሩ ማለቱ ለምን ይሆን? አዎ በትክክል የሚጾም ጾም ከምስጋናም በላይ ነው። ስለዚህ በምስጋና ጾማችን ላይ እንግዳ (ወንድም) መውደድን ጨምሩ አለን። እናስተውል ! ከዚህ በፊት በነበሩት ቀናቶች አባታችን ፍቅርን እንዴት በየእለቱ እንዳሰተማረ ተናግሬያለሁ። አሁንም እንዲሁ የተፈለጠው እንጨት(ጾም) በልጥ ፍቅር መታሰር አለበትና ውደዱ ውደዱ እያለ ሊቁ ያሳስበናል።

ከምግብህ ላይ ስጥ የተራበን አጥግብይህንን ዜማ ሰማችሁ ? አባታችን ያውቀናል ማለት ነው? በጾም ያተረፍነውን ምግብ (ቁርስ ወይም ምሳ) በምንበላ ሰአት በአይነት እንዳናካክሰው እኮ ነው እንዲህ ያለን ። ያ ያልተበላ ምግብ በገንዘብ የስጋዊ ሕይወት ኢኮኖሚ ማድለቢያ ሳይሆን የነዚያ ተርበው ፍርፋሪ የሚበሉት እንግዶች ነው። እንውደዳቸው ብሎን የለ? ታዲያ ሲርባቸው ቢያንስ በዚህ እናጥግባቸውና ፍቅራችንን የእውነት ጾማችንን የጽድቅ እናድርገው። ልብ በሉ የራባቸውን አብሉ ሳይሆን አጥግቡ ማለቱን፡፡

 ለድሃ አደጉም ፍረድድሃ አደጉ ዛሬ በጾም ከእኛ የሚፈለገው የለም? ለምኖ ስላልተሰጠው የእኛን ፍትህ ፍርድ አይሻም? የራበውን የምግብ ፍርድ ፈርደንለታል? እናም ህሊና ዳኛ ነው እንደሚባለው በዚያች ንጹህ ህሊና ፍርድ አጥቶ ለተራበው፣ ለተጠማው፣ ለታረዘው፣ ለታመመው፣ የእኛን ፍርድ ለሚጠብቀው ሁሉ እንድረስ ማለቱ ነበረ። እዝን ያለው በውሳጣዊ እዝን (ጆሮው) ይስማ። ጾማችን ምሉዕ ይሆን ዘንድ እባካችሁ ለችግሮች ሁሉ መድረስ ስንችል ቸል አንበል።  

ከምርመራ፣ ከጾም፣ ከመገዛት፣ ከምስጋና፣ ከመውደድ፣ የተራበን ከማጥገብ፣ ለድሃውም ከመፍረድ በኋላ በተፍጻሜቱይህ ለአንተ መልካም ነውብሎ ይደመድመዋል። መልካምነቱንማ እናውቀዋለን እንዳትሉኝ ያንን ሳያውቀው ቀርቶ አይደለም። ነገር ግን በሕይወታችን ባለመተርጎም መልካምነቱን እንዳናሳጣው ብሎ ነው።

ወረድ ብሎ ትናንት እንዳነሳነው ጌታም በምሳሌ አፌን እከፍታለሁ ተብሎ በነቢዩ ተጻፈውን እንደፈጸመ ደቀ መዝሙሩም .ያሬድ የጾምን ነገር በጾሙት እየመሰለ እንዲህ አለን፡- “ሙሴ ጾመ ዳንኤልም ጾመ ጌታም ስለ እኛ ጾመ ስለዚህ ጾምን ቀድሱሙሴ ቢጾም ሕግን ሊቀበል፤ ዳንኤል ቢጾም ከአናብስት አፍ ሊወጣ፤ የወገኖቹን ነፃነት ናፍቆ፣ እንኪያስ ጌታ ለምን ጾመ? እኔ ምን ልበል? ሊቁ ቀጠል አድርጎጾምን ቀድሶአርአያ ሊሆነን ፣ ጾምን ሊቀድስልን እንጂ ምን ጎድሎበት ምን ሊያገኝ ነው? ሁሉ በእጁ የተያዘ ነው ብሎ .ጴጥሮስ ነግሮን የለም? ስለዚህ እኔም ከአባቴ ጋር አልሁ ጾምን ቀድሱ ፣ ተቀድሶ ተሰጥቶናልና። ጾምን ቀድሱ ያለፈው የሞት አገልግሎት ይብቃ። ያለምክንያት አልደጋገምኩትም የአባቴ አጽንኦት ከዚህ በላይ መሆኑን ቢያንጸባርቅልኝ ብዬ ነው።

ጾምን ቀድሱ ሙሴ በሲና ጾሟልና ኢያሱም በጾም ዳነ በገባኦን ፀሐይን አቆመእና እኔ ምን እላለሁ ። ልናቆመው የሚገባን ብዙ ነገር አለን ከማለት ውጪ። ዜማው እንዳያልቅብን ብንጓጓም ዛሬ በነገ መቀየሩ ግድ ነውና ሳይሰናበተንበበጎ ሥራ ሁሉ ስትጓዙ የሰላም መንገድን ተከተሏት፤ በእርሷም ሂዱ ጾምን ፍፁም እንጹም የሰላም እህት ቅድስት ጾምን ጌታ ራሱ ጾሟታልናብሎ መክሮናል። በጾሙ ሰላምን ይስጠን ጾሙን በሰላም ያስፈጽምን።
 በረከቱን ያሳድርብን አምላከ .ያሬድ ይጠብቀን

No comments:

Post a Comment