Pages

Monday, March 17, 2014

መጻጉዕ ዘሠሉስ



በዲ/ንስመኘውጌትዬ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ መጋቢት 8 ቀን፣ 2006 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

 በአብና በወልድ በመንፈስ ቅዱሥ ስም፣ አንድ የናዝራውያን አምላክ፣ የማይለወጥ የሃይማኖት ምሰሶ፣ የማይፍገመገም የመርከባችን አለቃ፣ የማይጨልም የፋናችን ብርሃን፣ ከዘመናት አስቀድሞ በህልውና አንድ የሆነ፣ በስምና በስልጣን የሰለጠነ፣ የመለኮቱ አንድነት በማይለወጥ፣ የመንግስቱ ስፋት በማይወሰን፣ የብልጥግናው ክብደት በማይለካ፣ በአንዱ በእርሱ ስም ሰላም ይደረግልን፡፡


  በጠዋት ተነስተን ለነፍሳችን የሚሆን ቁርስ ፍለጋእምነ ጽዮን በሀ ቅድስት ቤተክርስቲያን ሥርጉት በስብሐት አረፋቲሃ ዘመረግድእናታችን ጽዮን ቤተክርስቲያን ሰላም ላንቺ ይሁን፡፡ ቅድስት ቤተክርስቲያን መሠረቶቿ መረግድ ናቸው:: በምስጋና ተሸልማለች፡፡ አዳራሿም በቢረሌ:: ከሰማዕታት ከገድላቸው ጽናት የታላቁ ንጉሥ የሕግ ታቦት መሠረትሽ የእውነት ፀሐይ ያበራልሻል::” ሰው የሥጋውን እንቅልፍ ሲጨርስ ከሁሉ አስቀድሞ ለነፍሱ ሰላምን ያገኝ ዘንድ የወለደችው እናቱን ሰላም ይላታል:: እንደ እናታችን ያማረ ውብ የለም:: ስለዚህ በዚህች ውብ ፊት ለነገ ስንቅ የሚሆነንን ሃብት በጠዋት እንደ ጎበዝ ገበሬ እናዘጋጃለን:: እርሷን እያየን የሚመጣውን ቤታችንን በእርሷ አምሣል እንገነባለን:: ወደዚያች ቤት መቼ እንደምንሄድ ባናውቅም::

  ስለዚህ ሊቁ እንዲህ ይለናል፡-ድልዋኒክሙ ንበሩ እስመ ኢተአምሩ ጊዜ ዘይመጽዕባለቤት የሚመጣበትን አታውቁምና ተዘጋጅታችሁ ኑሩ:: በሠርክ ቢሆን፣ በመንፈቀ ሌሊት ቢሆን፣ በጧት ቢሆን አታውቁምና ተዘጋጅታችሁ ኑሩ::” አቤቱ የንጥቂያ ሠዓት መቼ እንደሆነ አናውቀውምና በጨለማ ሳለን አትውሰደን::

 መራሕከነ በጸጋከ ውስተ ሕይወትበጸጋህ ከጨለማ አውጥተህ ወደ ሕይወት መራኸን:: የክብር ምሥጋና የመንግስት ጌጥ የሞት ስልጣኑ በመስቀል ተሸነፈ::” በእኛ ችሎታ ሳይሆን ዘለዓለማዊ ሕይወት የምንወርስበትን ልምምድ በጠዋት አንስተህ ወደቤትህ እንድንገሠግሥ በማድረግ የምሥጋና ወታደሮች አደረግኸን:: ስለዚህምነአኩተከ አበ ልዑላን ዘትነብር መልዕልተ አርያምበአርያም የምትኖር የልዑላን አባት እናመሰግንሃለን፡፡ ከእንቅልፍ አንቅተህ ወደዚህ የጸሎት ቤት ያስገባኸን የልዑላን አባት እናመሰግንሃለን፡፡” አንተ ወደ እርሷ የገሰገሰ አይደክምም ብለሃል እንለምንሃለን፡፡ እንማልድሃለን ቃልኪዳንህን አስብ:: ዳዊት በመዝሙር እንደተናገረ ከሰማይ ሆነህ የመቅደስህን አዳራሽ ጎብኝ:: ያንጊዜ፣ አንተ በቤተክርስቲያን በጎበኘኸን ጊዜ ልጅነታችን ይጸናል::

  ከመዝ ይቤላ እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያንእግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን እንዲህ ይላታል፡- ለአንቺ የሚገዙ ልጅነታቸውን ያድሳሉ::”

 ዜማው ይቀዳል፤ ከላይ ይፈሳል፤ የምሥጋናው ውሃ እንደ ክረምት ዝናም ይወርዳል:: “ዘአንተ ሠራዕከ ጎሐጽባሕአቤቱ የጠዋትን ንጋት የሠራህ በአንተ እንድንረባ አድርገን፡፡ የእውነት መቅጃ የበረከት ምንጭ ጸሎታችን እና ልመናችን ከአንተ ፊት ትድረስ::” ስለጸሎታችን መስመር መልካም ጾምን እንጾም ዘንድ እርዳን::

 ቢጽ ምስለ ቢጽ ዘኢያስተዋዲወንድም ከወንድም ጋር የማያጣላ፣ ዝም በማለት የሚቆይ በጾምና በጸሎት እዳውን ይከፍላል:: እንዲህ አይነቱን ነጋዴ ዘዋሪ አይችለውም::” ዝምታ፣ አርምሞ በጾም ጊዜ የምትመረጥ በጎ ዕድል ናት::

እናዚም!ወያዕቆብ ኀረዮ ትዕግስተ ወርእዮ አምሳለ ጾምያዕቆብስ ትዕግስትን መርጦ የጾምን ምሳሌ አይቶ በረከትን ወረሰ:: ዛሬም ወንድሞቼ እኛ እንጹም፡፡ ወደን እንጣር፡፡ በጾምም እናገልግለው፡፡ ዋጋ እናገኝ ዘንድ መንግሥተ ሠማያትን እንዲያድለን፡፡ ከመላእክት ጋር አንድነትን ይሠጠን ዘንድ:: ልብ ላለውበጾም ትዕግስትን፣ በረከትን፣ ዋጋን፣ ከመላእክት ጋር መሆንን፣ መንግሥተ ሠማያትን የምታሠጥ ናት” ይለናል አባታችን:: ጾም ከሞት ታድናለች፤ እንደ ዳንኤል፡፡ ጾም ከሰው ለይታ ከፍ ታደርጋለች፤ እንደ ኤልያስ፡፡ ጾም ከእሳት ታድናለች፤ እንደ ሠለስቱ ደቂቅ፡፡ ጾም ፊትን ታበራለች፤ እንደ ሙሴ፡፡ ጾም ሕዝብን ትታደጋለች፤ እንደ ነነዌ፡፡ ጾም የንጉሥን አዋጅ ታሽራለች፤ እንደ ዘመነ አስቴር፡፡ ጾም እውነትን ትወልዳለች፤ እንደ ነቢያት:: ስለዚህ በፍቅር እንጹም:: በምድር ሰላም በሰማይ ምሥጋና ለአንተ ይሁን አሜን!

No comments:

Post a Comment