Pages

Thursday, April 3, 2014

ገብር ኄር ዘዓርብ



በዲ/ን ስመኘው ጌትዬ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ መጋቢት 25 ቀን 2006 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
 እንደ ሱራፌል ቃል በምናመሰግነው፣ የሰው ልጅ በማይነካው፣ የሟችም ሕሊና በማይመረምረው፣ በጽርሐ አርያም አትሮኑሱን ያኖረ፣ በተራሮች ራስ ላይ የጉምን ተን በሚያተን፣ ያለጩኸት በሚያስወግደው፣ በአየራት ውስጥ በሚያመላልሰው፣ ሰፊውን የሰማይ ገጽ የደመና ግምጃን በሚያላብሰው፣ ክብርና ምሥጋና በሚገባው በእግዚአብሔር ስም ሰላም ለእናንተ ይሁን::


 ዋካ ይእቲ ወብርሃን መድኃኒት ቤተክርስቲያንቤተክርስቲያን ብርሃንና መድኃኒት ናት:: የዋሃንን እና የሚታገሱትን ወደ ሕይወት መርታ ወደ እግዚአብሔር ታደርሳቸዋለች፤ እንዲህም ትላቸዋለች: እነሆ ምዕመናን ልጆቼ ሁልጊዜ በእኔ ዘንድ በጠዋት ለስምህ ይሰግዳሉ::” እንደ ሁልጊዜው ቅዱስ ያሬድ ነጋ እኛም እናመሰግናለን:: የምንጾመው ከምግብ እንጂ ከአንተ ምሥጋና አይደለም ይለናል:: በጠዋት አንቃኝ፤ የነፍሴን መድኃኒት አንተን እሰማ ዘንድ ጆሮዬን ክፈትልኝ::

  ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ዘይቤ ሐዋርያ ናሁ እሰይምሃሌ ሉያ! ቅድመ ዓለም የነበረ፣ ዓለሙን አሳልፎ የሚኖር፣ ሐዋርያው እንዲህ አለ: እነሆ የማዕዘን ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ፤ የተመረጠች፣ የተከበረች፣ እንግዳን የምትወድ፣ እሺ የምትል፣ ሰላማዊት፣ ለነገሥታትም ሰላምን ትሰጣለች::” ከአንተ ሌላ አምላክ ከአንተ ሌላ ራስ አታውቅምና ለቤተክርስቲያን ፍርድህን ሰላምህን ስጣት:: የአንተን ፈቃድ ውድህንም እንሰራ ዘንድ በቤትህ አጽናን::

  ቤተክርስቲያን መርዓቱ ለአልፋ ታቦቱ መሃትዊሃ ፯ቱ ከዋክብቲያሃ ሰማዕታት እሙንቱቤተክርስቲያን ሙሽራው፣ ለአምላክ ማደሪያው፣ ሰባቱ መብራቶቿ ሰማዕታት እነርሱ ኮከቦቿ ናቸው::” ዛሬ በሦስት ሠዓት መስቀልህ ለሕዝበ ክርስቲያኖች ሁሉ ብርሃን ሆነ፤ ለጻድቃንም መሪ ሆነ::

 ቤተክርስቲያን ተቀደሲ በጽድቅ ተሐደሲ እምሐዘን አንፍሲ ኃይለኪ ጽዮን ልበሲቤተክርስቲያን ጽዮን ሆይ ተቀደሺ፣ በጽድቅም ታደሺ፣ ከሐዘን እረፊ፣ ኃይልሽንም ልበሺ::”

 ከዚህ በኋላ ደግሞ የጾምን ጥቅም እያነሳ ይመክረናል:: ጾም ትረዳለች፤ ምግባር ታሰለጥናለች:: ወንድሞቼ በሃይማኖት ጽኑ፤ እርስ በእርስ ተፋቀሩ፤ ፍቅር የሁሉ ማሰሪያ ሁሉን የሚሸፍን ነው::

 በንጹሕ ዘጾመ በከናፍሪሁ ማዕፆ ዘሤመ ሐዳስ ይትዋረስ ዓለመበንጹሕ የጾመ ለአፉ (ለከንፈሩ) መዝጊያን ያደረገ (የሾመ) አዲስ ዓለምን ይዋረሳል (ይወርሳል)::” ዛሬ በስድስት ሰዓት መስቀልህ ረዳት ጋሻና መድኃኒት ሆነን፤ በሰማያት ላለህ ለአንተ ምሥጋና ይገባል::

  በጾም ወበጸሎት ፍትወተ ሥጋ አግረሩ ከመ አንስርት በአክናፍ ትሥርሩእንደ ንሥሮች በክንፎች ትበሩ ዘንድ በጾምና በጸሎት የሥጋ ፈቃድ ጸጥ ተደረጉ (ተገዙ)::” ዓርብ የመስቀልህ ነገር ይበልጥኑ ይነገራል:: እሌኒ ጠየቀች፤ አዋጅ አስነገረች፤ ንጉሥን አስጠራች፤ ጢስንም አስጤሰች፤ መድኃኒት አገኘች፤ የክርስቶስን መስቀል ገንዘቧ አደረገች::

 ኃዳፌ ነፍስ ወሥጋ ዓቢተነ በጸጋ በመንፈስ ቅዱስ እንግልጋ እምእሊአከ ኢንኩን ንትጋነፍስና ሥጋን የምታነፃ በመንፈስ ቅዱስ አደባባይ በጸጋህ አሳድረን፤ እኛ የተጎዳን አንሁን::” ዛሬ ዘጠኝ ሰዓት የሚረዳ መስቀልህ አዳምን በመንገዱ መርቶ ወደ ገነት ሲያስገባው ያንን የቀኝ ወንበዴ ደግሞ በዐይን ጥቅሻ መረጠው:: በመስቀሉ ገነትን ከፈተ በመስቀሉ ሰላምን አደረገ::

 መስቀል በሉ ኪያሁ ተወከሉ በመስቀሉ ውእቱ ይዕቀብክሙ አምላከ ሰላም የሃሉ ምስሌክሙ ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስመስቀል መስቀል በሉ፤ በእርሱም ታመኑ፤ እርሱም ይጠብቃችሁ፤ እርሱ የሰላም አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናንተ ጋር ይሁን::” አሜን!

No comments:

Post a Comment