Pages

Wednesday, March 4, 2015

በመጽሐፍ ምረቃ ቀን እንዲገኙ ተጋብዘዋል



(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ረቡዕ የካቲት 28 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
     ሰላመ እግዚአብሔር ይብዛላችሁ ውድ የመቅረዝ አንባብያን፡፡ እንደምን ሰነበታችሁ? እግዚአብሔር ቢወድና ቢፈቅድ ቀጣይ ቅዳሜ ማለትም የካቲት 28 ቀን 2007 ዓ.ም. በገ/ጽ/ቅ/ጊ/ቤተ ክርስቲያን (ፒያሳ) ስብከተ ወንጌል አዳራሽ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ዠምሮ ኹለት መጻሕፍት አንድ ላይ ይመረቃሉ፡፡ አንደኛው መጽሐፍ በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመው የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ መጽሐፍ ሲኾን ኹለተኛው መጽሐፍ ደግሞ የዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት የትምህርት ክፍል ሰብሳቢ በኾኑት በመምህር ዘሪኹን መንግሥቱ የተዘጋጀ ነው፡፡

     “ሰማዕትነት አያምልጣችሁ” በሚል ርእስ በተዘጋጀው የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ መጽሐፍ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ዳሰሰ ይቀርባል፡፡ መጋቤ ሐዲስ ዳሰሳውን ከማቅረባቸውም በላይ፡-
·        በስምንቱ ብሔረ ኦሪት ላይ የተሠራ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትርጓሜ በግእዝ መኖሩን፤
·        የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ የቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊና የቅዱስ ኤፍሬምን በብዛት ያካተተ ትርጓሜ መልእክታተ ጳውሎስ እንዳለ፤
·        እነዚኽ የግእዝ በግእዝ ትርጓሜ መጻሕፍት የት እንዳሉ፤
·        እነዚኽ የሊቃውንቱ መጻሕፍት ወደ አማርኛ እንዴት፣ በማን ይተርጐሙ በሚሉና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ይዳሰሳሉ፡፡ 




በዚኹ አጋጣሚ ከዚኽ በፊት የሊቁ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ መጻሕፍት የኾኑትንመልክአ ሕማማት ወይም የሰባቱ ጊዜያት የጸሎት መጽሐፉንሙሉውን ንባቡና ትርጓሜውን በአንድምታ በኹለት መቶ ስድሳ አራት ገጾች፤ በመቀጠልምመጸሐፈ ሰዓታቱንሙሉው ንባብና ትርጓሜውን በአራት መቶ ስምንት ገጾች አዘጋጅተው ያቀረቡልን መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ አኹንም ረድኤተ እግዚአብሔርን አጋዥ አድርገው በሰማያዊ ምስጢራት የተመላውንየመዐዛ ቅዳሴን ንባቡና ትርጓሜውን በአንድምታአዘጋጅተው ያቀረቡልንን መጽሐፍ በዕለቱ ያገኙታል፡፡

     ነጽሮተ ሀገር” ስለ ተሰኘው ኹለተኛው መጽሐፍ በዲያቆን ዳንኤል ክብረት ዳሰሳ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል፡፡ 

በዕለቱ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ዘማርያን፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የሚገኙ ሲኾን ሌላ አጋጣሚ በመኻል ካልተፈጠረ በቀር እጅግ የምንወዳቸው መምህራችን መጋቤ ሐዲስ (የኔታ) እሸቱ ዓለማየኹም ተገኝተው መልእክት ያስተላልፋሉ፡፡ በመኾኑም ይኽን ድግስ ከወዳጆችዎ ጋር ስንጋብዝዎት እጅግ ደስ እያለን ነው፡፡ ብዙ ነገር ይጠቀማሉ፡፡ሰማዕትነት አያምልጣችሁ፡፡ ለወዳጆችዎ በማካፈልም መልእክቱ ለኹሉም እናድርሰው፡፡

No comments:

Post a Comment