Pages

Friday, October 2, 2015

ቅዱስ ቀሌምንጦስ ዘሮም



በሥርጉተ ሥላሴ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ መስከረም 21 ቀን 2008 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
በጥንታዊቱ ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያትን አህለው ሐዋርያትን መስለው ከተነሡ እጅግ ከሚታወቁት ሐዋርያነ አበው መካከል፥ የቅዱስ ጴጥሮስና የቅዱስ ጳውሎስ ደቀ መዝሙር የነበረው ቅዱስ ቀሌምንጦስ ዘሮም አንዱ ነው፡፡ ስለዚሁ ቅዱስ ሰው ብዙ ዓይነት አመለካከት ያለ ሲኾን፥ አውሳብዮስ ዘቂሳርያ፣ አባ ጀሮም እና ሌሎች አርጌንስን ተከትለው የቅዱስ ጳውሎስ ደቀ መዝሙር እንደ ነበረ ያስተምራሉ /ፊልጵ.4፥3/፡፡ “የንጉሥ ድምጥያኖስ የአጎት ልጅ ነው” የሚሉም ያሉ ሲኾን፣ ሌሎች ደግሞ “እጅግ ጥበበኛና የተማረ ሰው የነበረና በኋላም ዕውቀትን ፍለጋ ወደ ፍልስጥኤም ሲሔድ ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር ተገናኝቶ ክርስቲያን ኾኗል” ይላሉ /አባ ቴዎድሮስ ያ.ማላቲ፣ ሐዋርያነ አበው፣ ገጽ 64/
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ. ሊቃውንት የሚታመነውና ሕዳር 29 የሚነበበው ስንክሳር እንደሚነግረን ደግሞ፥ ቀሌምንጦስ ዘሮም ትውልዱ ከንጉሣውያን ቤተ ሰቦች ነው:: አባቱ “ቀውስጦስ” የሮማው ንጉሥ የጦር አለቃ የነበረ ሲን፥ በቅዱስ ጴጥሮስ ስብከት አምኗል:: በአንድ ወቅት “ቀውስጦስ” ወደ ሮማው ንጉሥ ዶ ለብዙ ቀናት ቢዘገይ ወንድሙ ሚስቱን ለማግባት ፈለገ:: የቀሌምንጦስ እናት ይህንን ማ ቀሌምንጦስንና ታናሽ ወንድሙን ይዛ አባታቸው እስኪመለስ ድረስ ፍልስፍና ይማሩ ብላ ወደ አቴንስ ከተማ ለመድ ተነሣች:: በመርከብ ተሳፍረው ሲዱ ሳሉ ግን ኃይለኛ ማዕበል ተነሥቶ መርከቧን ሰባበራት ንም በታተናቸው:: ቀሌምንጦስንም ከቤተ ሰቦቹ ለይቶ እስክንድርያ አደረሰው:: ቅዱስ ጴጥሮስ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ እስክንድርያ ከተማ ገብቶ ሲያስተምር ከቀሌምንጦስ በቀር አማኝ አላገኘም:: ቀሌምንጦስ የቅዱስ ጴጥሮስን ስብከት ሲሰማ በጌታችን አምኖ የክርስትና ጥምቀት ተጠመቀ፤ ከዚችም ሰዓት ጀምሮ የቅዱስ ጴጥሮስ ደቀ መዝሙር ፡፡
ቅዱስ ሄሮኔዎስ እንደሚነግረን፥ በኋላ ላይ የሮማ ከተማ አራተኛው ሊቀ ጳጳስ ኗል /በእንተ መናፍቃን፣ ሣልሳይ መጽሐፍ 3:3/፡አውሳብዮስ ዘቂሳርያም ከዚህ ተነሥቶ “ጊዜው ከ92 እስከ 101 ዓ.ም. ነው” ይላል፡፡

ቅዱስ ጴጥሮስ ከጌታችን ያገኘውን ጥልቅ ምሥጢር በሙሉ ለተማሪው ለቀሌምንጦስ ነግሮታል:: የቤተ ክርስቲያንን አደራ ከብዙዎች ሐዋርያት በተለይም ከቅዱስ ጴጥሮስ ተቀብሏል:: ቅዱሳን ሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን የምትመራበትን ቀኖናና ሥርዐት (ዲድስቅልያን፣ አራቱ ከፍል ሲኖዶስን) አስረክበውታል:: ቀሌምንጦስ ዘሮም ገድለ ሐዋርያትንና በላውያን ነገሥታት ፊት በእምነት መመስከራቸውን ጽፏል::
መጽሐፈ ቀሌምንጦስ
ቅዱስ ቀሌምንጦስ ዘሮም፥ ከመምህሩ ከቅዱስ ጴጥሮስ እየጠየቀ ብዙ ምሥጢራትን የተረዳ ሲን ይህንንም ጽፎ አስቀምጦልናል - መጽሐፈ ቀሌምንጦስ የሚባል ይህ ነው:: በስሙ የተሰየመለት ይህ መጽሐፍ ይዘቱ ምን እንደሚመስል ከዚህ ቀጥለን በአጭሩ እንመለከታለን::
መጽሐፈ ቀሌምንጦስ ቤተ ክርስቲያናችን ከምትቀበላቸው 81 (ሰማንያ አሐዱ) ቅዱሳት መጻሕፍት ቍጥር ሲን ከስምንቱ የሥርዐት መጻሕፍት መደብ ነው:: 11 ምዕራፍም አለው፡፡ ቅዱስ ቀሌምንጦስ መጽሐፉን ለመጻፍ ምክንያት የነው ነገር እንዲህ በማለት ያስቀምጣል፡- “የኦሪትና የነቢያት ዕውቀት ስላልነበረኝ አይሁድ ስለ አዳም አፈጣጠር እና ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም በጠየቁኝ ጊዜ መልስ መስጠት አልቻልኩም፤ [የጌታችንን መምጣት ለማስታበል ትንቢቱ አልተፈጸመም ለማለት እመቤታችንን ከይሁዳ ወገን አይደለችም እያሉ ይከራከሩት ነበር]:: በዚህ ጊዜ መምህሬ ጴጥሮስን ሉንም ያስረዳኝ ዘንድ ጠየቅሁት፤ እርሱም አዘነ በቅንአትም ኖ በቅድሚያ ስለ ዓለም አፈጣጠር ቀጥሎም ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ከይሁዳ ወገን እንደ ነች እነግርሃለሁ አለኝ /ምዕራፍ 1፥11-13/፡፡ በዚህ ዓይነት ቀሌምንጦስ እየጠየቀ ቅዱስ ጴጥሮስ እየመለሰ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ እስከ ዳግም ምጽአት ያለውን ምሥጢር ነግሮታል::
ሀ) ሥነ ፍጥረት
እግዚአብሔር ከዘመናት በፊት በቅድምና የነበረ ዘላለማዊ፣ ውሳጤ አፍኣ የሌለው፣ ዐይን ማየት በማይችለው ብርሃን ውስጥ የሚኖር፣ ስብሐቲሁ ዘእምኀቤሁ - ምስጋናው ከባሕርዩ የነ፣ ፍጥረታትን በሙሉ የፈጠረ እንደ ነ በመናገር ይጀምራል:: በዕለተ እሑድ ሰማይና ምድር፣ መላእክትም አሥር ወገን ነው እንደ ተፈጠሩ፤ ከሉም መላእክት በማዕርግ የሚበልጠው የሳጥናኤል ወገን እንደ ነበረ፣ በዕለተ ሰኑይ እግዚአብሔር በምድር ባሉ ውችና በሰማይ ባሉ ውች መካከል ልዩነትን (ጠፈርን) እንዳደረገ፣ በዕለተ ሠሉስ ከሰማይ በታች ያሉ ውች በአንድ ቦታ እንዲሰበሰቡ እንዳዘዘ እና የብሱም እንደ ታየ፣ አዝዕርትንም ዛፎችንም እንደ ፈጠረ፣ በዕለተ ረቡዕ ፀሐይ ጨረቃ ከዋክብት እንደ ተፈጠሩ፣ በዕለተ ሐሙስ ውች የዓሣዎችን ዓይነት ያወጡ ዘንድ እንደ ታዘዙ፣ በነፋስ የሚበሩትንም አስደናቂ ትላልቅ አንበሪዎችንም እንደ ፈጠረ፣ በዕለተ ዓርብ ከምድር አራዊትን እንስሳትን እንደ ፈጠረ፣ በመጨረሻም ከአራቱ ባሕርያት ትንሽ ትንሽ ወስዶ ሰውን በአርአያውና በምሳሌው እንደ ፈጠረ ሔዋንንም ከአዳም ከጎኑ ዐፅም እንዳስገኛት ይናገራል:: እግዚአብሔር አዳምን (ሰውን) በማይነገር ክብር እንደ ፈጠረው፤ የመለኮት ብርሃን በአዳም ፊት ያበራ እንደ ነበር፣ የፊቱ ብርሃን ከፀሐይ የሚበልጥ ሰውነቱ እንደ ንጋት ኮከብ የሚያበራ እንደ ነበር፣ እግዚአብሔር ለአዳም የምስጋና አክሊል፣ ልብሰ መንግሥት፣ የግርማ ከፍተኛነት እንዳለበሰው፣ የመንግሥትን አክሊል እንዳቀዳጀው ንጉሥነትንና ነቢይነትን እንደሰጠው መላእክት በታላቅ ግርማ እና ምስጋና ባዩት ጊዜ እንደ ፈሩት፤ አራዊት እንስሳት አዋፍ እግዚአብሔር የፈጠራቸው ፍጥረታት ሉ ተሰብስበው ለአዳም እንደ ሰገዱለት ሰይጣን የአዳምን ጸጋና ክብር አይቶ እንደ ቀና የሚያስትበትንም ምክንያት ይፈልግ እንደ ነበር ይናገራል /ምዕ.1፥14-49/::
ለ) የአዳም ውድቀት
በዚህ ክፍል ሰይጣን በአርዌ ምድር ተሰውሮ ሔዋንን ዕፀ በለስ ጣፋጭ እንደ ነች የአምላክነትንም ክብር እንደምታሰጥ ዋሽቶ እንዳሳታት፣ አዳምም ሔዋንም አምላክ ሊኑ ዕፀ በለስን እንደ በሉ፤ ያደረባቸው ክብር እንደ ተገፈፈ ከጸጋ እንደ ተራቆቱ ከገነት እንደ ወጡ :: መፍቀሬ ሰብእ - ሰውን ወዳጅ የነው እግዚአብሔር ግን በውድቀታቸው ስንኳ ፍቅሩን እንዳልቀነሰባቸው ይልቁንም እንደ ጎበኛቸው እንዳፅናናቸው ይተርካል:: ኪዳነ አዳም በመባል የሚታወቀው አባቶቻችን በስብከት አብዝተው የሚጠቅሱት፣ የኪዳናት ሉ ቁንጮ: መጀመሪያ: መነሻ የነው ቃል ኪዳን የሚገኘው በዚሁ በመጽሐፈ ቀሌምንጦስ ነው:: እግዚአብሔር ለአዳም እንዲህ ሲል ቃል የገባለት: “ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ::” እግዚአብሔር ለአዳም ዐፅሙን ለልጅ ልጅ እንደሚያስብቅለት: ዐፅሙም በተቀመጠበት ቦታ መድኃኒትን እንደሚያደርግለት /በዚያ እንደሚሰቀል/ እንደ ነገረው አዳምና ሔዋን ከገነት ከወጡ በኋላ ከገነት በታች ባለ ተራራ በደብር ቅዱስ መኖር እንደ ጀመሩ፤ አዳም ለሔዋን በመካከላችን ምስክር ይን: አምኃነቱም ወልደ እግዚአብሔር ወደዚህ ዓለም ሲመጣ ይናል በማለት ወርቅ ዕጣን ከርቤ እንደ ሰጣት ልጆችም እንደ ወለዱ ቃየል የእናት አባቱን ምክር ባለመስማት መልከ ጥፉይቱን የአቤልን መንትያ አላገባም እንዳለ፣ በቅንአት ተነሳስቶ አቤልን እንደገደለው ተቅበዝባዥም እንደ ነ ይጠቅሳል:: አዳም የረፍቱ ጊዜ ሲደርስ ልጆቹን የልጅ ልጆቹን ሰብሰቦ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንዲጠብቁ፣ ከቃየል ልጆች እንዲርቁ፣ ዐፅሙንና አምኃውን እንዲጠበቁ እንዳዘዛቸው፤ በተለይም ለልጁ ለሴት ብዙ ትእዛዛትን: ትንቢታትን እንደ ነገረውጌታ ከድንግል ማርያም እንደሚወለድ: እንደ ሰው እንደሚመላለስ: ሕሙማንን እንደሚፈውስ: እንደሚሰቀል: አዳምንና ዘሮቹን እንደሚያድን፣ ስለ ቃየል ልጆች ኀጢአት ማየ አይህ - የጥፋት ውሃ እንደሚመጣ እንደ ነገረው ከዚህ በኋላ ከቃየል ልጆች በስተቀር ሉም በሴት መሪነት ትእዛዘ አዳምን በመጠበቅ በንጽና በቅድስና በደብር ቅዱስ እንደ ኖሩ [ደቂቀ ሴት የሚባሉ፣ ከንጽናቸውም የተነ የመላእክት ልጆች የሚባሉ እነዚህ ናቸው]፤ የቃየል ልጆች ግን ከደብር ቅዱስ በታች በኀጢአት እንደ ኖሩ ከአዳም በኋላ ሴትን ጨምሮ የተለያዩ አበው ደቂቀ ሴትን እየመሩ ሲሞቱም ሕዝቡን ትእዛዘ አዳምን እንዲጠብቁ፣ ከቃየል ልጆች እንዲርቁ በደመ አቤል እያስማሉ እንዳለፉ ከአዳም ተቀብሎ ሴት: ከእርሱም በኋላ ሄኖስ: ቃይናን: መላልኤል: ያሬድ በየተራ ሕዝቡን እንደ መሩ በያሬድ ጊዜ ከደቂቀ ሴት የአባቶቻቸውን ትእዛዝ የማይጠብቁ ሰዎች ተነተው አንድ አንድ እያሉ ከደብር ቅዱስ እየወረዱ ከቃየል ልጆች እንደ ተጨመሩ፤ በመብል በመጠጥ በዘፈን በዝሙት እንደ ረከሱ ሄኖክ ሲሰወር ከሦስቱ አበው (ማቱሳላ: ላሜህ: ኖኅ) በስተቀር ሉም ወደ ደቂቀ ቃየል እንደ ወረዱ ይናገራል::
ከማቱሳላ እና ከላሜህ በኋላ ኖኅ የቀሩትን ደቂቀ ሴት እንደ መራቸው እግዚአብሔርም ለኖኅ ማየ አይህ እንደሚመጣ ገለጠለትና መርከብ እንዲሠራ እንዳዘዘው መርከቡንም ከታች ደቂቀ ቃየል ካሉበት ወርዶ ሉም እያዩት: ስለ መርከቡ ለሚጠይቁት ስለ ማየ አይህ መምጣት እየነገረ እንዲሠራ እንዳዘዘው ከዚህ በኋላ ኖኅ እና ልጆቹ የደብር ቅዱስን ድንጋዮቿን እንጨቶቿን በዘን እየሳሙ፣ ቀደምት አበውን እየተማጸኑ ዐፅመ አዳምንና አምኃውን ይዘው ከደብር ቅዱስ እንደ ወረዱ ኖኅም መርከቡን ሠርቶ ሲጨርስ ማየ አይህ ጀመረ፤ ደቂቀ ሴት ቢፀፀቱም የሚረዳቸው እንዳላገኙ እግዚአብሔር በነቢዩ ዳዊት ስለ ደቂቀ ሴት በተናገረበት ትንቢቱ:- “አንሰ እቤ አማልክት አንትሙ ወደቂቀ ልዑል ኩልክሙ አንትሙሰ ከመ ሰብእ ትመውቱ ወከመ አሐዱ እመላእክት ትወድቁ - እኔ ግን አማልክት ናችሁ፥ ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁአልሁ፤እናንተ ግን እንደ ሰው ትሞታላችሁ፥ ከአለቆችም እንደ አንዱ ትወድቃላችሁ” እንዳላቸው ያስተምራል /መዝ.81(2):6-7/፡፡ ቅዱስ ቀሌምንጦስ መርከብ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ እንደ ነች፣ ኖኅ ከመርከብ ወጥቶ ወይን ጠጥቶ ሰክሮ ተኝቶ ሳለ የሳቀበት ካምን ተነቶ እንደረገመ - ክርስቶስ  3 ቀን 3 ሌሊት በንዋመ መቃብር ቆይቶ ከትንሣኤ በኋላ ሰይጣንንና ሰቃልያንን የመርገሙ ምሳሌ መኑን ተርጉሞ አስቀምጧል:: ከኖኅ በኋላ ሴም በመልአከ እግዚአብሔር መሪነት ዐፅመ አዳምን ወደ ማእከለ ምድር ጎልጎታ በስውር ወስዶ መልከ ጼዴቅን በዚያው ትቶ አስጠብቆታል::
ከዚህ በኋላ የኖኅ ልጆች ዝርዎት /መበተን/ እንደ ነ: አምልኮ ጣዖት: መተት ሟርት እንደ ተጀመረ ይገልጻል:: አብርሃም በ75 ዓመቱ ወደ ከነዓን ምድር እንደ ተጠራ: ይስሐቅን አዳም በተፈጠረበት ኋላም በተቀበረበት በደብረ ማኖስ ሊሠዋው እንደ ወሰደው: ይውም ርስቶስ የተሰቀለበት ቦታ እንደ ነ፣ በዚህም አብርሃም አምሳለ ስቅለትን እንዳየ፤ ጌታም “አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ወደደ አየም ደስም አለው” ያለው (ዮሐ.8፥56) ይህንን እንደ ነ ይጠቅሳል:: ሌላም ስለ አብርሃም እና ስለ ልጆቹ ደት ይተርካል፤ በተለይም እያንዳንዱን ታሪክ ለነገረ ሥጋዌ /ለክርስቶስ ሰው መን/ ትንቢት እንደ ነ ይተረጉማል:: ለምሳሌ ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ ያየው ምሥጢር አምሳለ ስቅለት እንደ ነ፣ ዘቅተ ያዕቆብ የቅድስት ጥምቀት አምሳል እንደ ነ፣  ልያ እና ራሔል የቤተ እስራኤል እና የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ እንደ ኑ. . . እንዲሁም ስለ ያዕቆብ ልጆች: ስለ ሙሴ: ስለ ኢያሱ: ስለ መሳፍንት: ስለ ዳዊት: ስለ ሰሎሞን: ስለ መንግሥት ለለት መከፈል ይተርካል . . .
ሐ) ጴጥሮስ ለቀሌምንጦስ ሌሎች ብዙ ምሥጢራትን እንደ ገለጠለት
ጌታ ለጴጥሮስ የገለጠለትን እርሱም በተራው ለቀሌምንጦስ እንደ ገለጠለት ስለ ምሥጢረ ሥላሴ - ሥላሴ ከሉ በላይ እንደ ኑና ፈጣሬ ፍጥረታት እንደ ጌታ ለጴጥሮስ እንዲህ እንዳለው:- ሉን ችዬ የምኖር ቦታ እኔ ነኝ: በምስጋና መንበሬ ላይ ነበርኩ: በጸጋዬ ሀብት ነበርኩ፡ አብ በእኔ ዘንድ አለ: በእኔም ዘንድ መንፈስ ቅዱስ አለ: በእኛ ዘንድ መቅደምና ወደ ኋላ ማለት የለም: ከመካከላችንም ፊተኛና ኋለኛ ተብሎ የሚነገርለት የለም: መጀመሪያና መጨረሻም የለንም:: የእኛ ህላዌ የእኛ መገኘት በሉ ዘንድ ነው: የኀይላችን ታላቅነት በሉ ይገኛል: እኛ የፈጠርነው ሉ ከእኛ በታች ኖ ይኖራል: ርዝመታችንና ስፋታችን በሰው አእምሮ አይገመትም: ሉን እንችላለን ሉ ግን ማንነታችንን ሊረዳ አይችልም: እኛ ከሉ በላይ ነንና የኀይላችንም ታላቅነት ሉን ይዟልና:: ግራና ቀኝ የለንም: ውስጥና ውጭም በእኛ ዘንድ የለም: ውስጥ እኛ ነን ውጭ እኛ ነን: ምስጋናችንና የጸጋችን ሀብት ከእኛ ዘንድ ነው: ከባዕድ የሚያስፈልገን ነገር ፈፅሞ የለም: አብ እውነተኛና ትክክለኛ ነው እኔም ይቅርታና ምሕረት ነኝ መንፈስ ቅዱስ ኀይልና ጥበብ ነው:: እኛን መሸከም የሚቻለው ሰማይ የለም ምድርም የለም: ከግብር ወደ ግብር መለዋወጥ በእኛ ዘንድ የለም: ከቦታ ወደ ቦታም አንመላለስም: የሰው ዐይን እኛን አያይም: ሰውም በመራቀቅና በመመራመር እኛን ሊያውቅ አይችልም:: በእኛ ዘንድ ጭማሪም ነ ሕፀ የለም: አብ አእምሮ ነው እኔም ሥምረት ነኝ መንፈስ ቅዱስም ኀይል ነው: እኛ ብዙዎች አይደለንም: አንለያይም: ልዩነት አያገኘንም: ጥፋትም አያገኘንም: አብ በእኔ ሉን ፈጠረ በመንፈስ ቅዱስም ተፈፀመ:: አብ ነቢብ ነው እኔም ቃል ነኝ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ ሕይወት ነው: የሚመሳሰለን የለም እኛ ከመመሳሰል በላይ ነንና: እንደኛ የሚን የለም እኛ ከሉ በላይ ነንና: አባቴ እሳት ነው ብርሃኑም እኔ ነኝ ሙቀቱም መንፈስ ቅዱስ ነው: አባቴ ው ነው እኔም ጣዕሙ ነኝ መንፈስ ቅዱስም ሕይወት ነው: አባቴ ክብር ነው እኔም ክብር ነኝ መንፈስ ቅዱስም ጸጋ ነው: ከእኛ ውጪ ፍጥረት የለም: ሰማያት ሳይፈጠሩ እኔ ከአብ ጋር ነበርኩ: አባቴ ግርማ ነው እኔ ደግሞ ጸጋ ነኝ መንፈስ ቅዱስ ፍፃሜ ነው:: እኔ በአብ አለሁ: መንፈስ ቅዱስ በአብና በእኔ አለ: አባቴ ጥበብ ነው እኔም ቃል ነኝ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ የቃል ድምፅ ነው: በጥበባችን ሉን የፈጠርን እኛ ነን: ቀዳሚዎችም እኛ ነን: መጀመሪያና መጨረሻም የለንም:: ዘመናችን በፍጡራን ዘንድ አይታወቅም: ከዘመንና ከአዝማን በፊት እኛ ነን: ከእኛ ዘንድ የሚቀርብ የለም: የሰው ሊናና የመላእክት አእምሮ ሊደርስብን አይችልም: እኛ ከሊናት ሉ በላይ ነንና: ምስጋናችንም ከራሳችን ነው:: እኛ መጀመሪያና መጨረሻ የለንም: ከፍቅራችን ብዛት የተነሳ ዓለምን እንፈጥር ዘንድ ወደድን /ምዕ.6፥13-18/ ሌሎችም ብዙ ምጢራት እንደ ገለጠለት - ስለ ምሥጢረ ሥጋዌ: ስለ ዳግም ምጽአት: ስለ ሐሳዊ መሲሕ: ስለ ነገደ መላእክት: ስለ ገነት: ስለ ቤተ ክርስቲያን ምንነት
መ) ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን
ጳጳሳት ካህናትና ምእመናን እንዴት መመላለስ እንደሚገባቸው የቅዱስ ጴጥሮስ ትእዛዝ አዘውትሮ ወደ ቤተ ክርስቲያን መገስገስ እንዲገባ: በትጋት ስለ መጸለይ: ስለ ንጽና. . . በተለይ ጥንቆላንና ሟርትን: አምልኮ ጣዖትን: ስካርና ዝሙትን አጥብቆ ያወግዛል - እነዚህን የሚያደርግ ተወግዞ ከቤተ ክርስቲያን መለየት እንዲገባው ካህናትን ያቃለለ ኩነኔ እንዲገባው፣ ካህናት ሳያፍሩና ሳይፈሩ በድፍረት ማስተማርና መገሠጽ እንዲገባቸው. . .
ከብዙ በጥቂቱ ስለ መጽሐፈ ቀሌምንጦስ ይህን ያህል ካልን ሙሉውን መጽሐፉን አንብባችሁ እንድትረዱ በትሕትና እንጋብዛለን:: ከዚህም መጽሐፍ የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮዋ: ዶግማዋና ቀኖናዋ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ስልቷ ወ.ዘ.ተ. ከሐዋርያት ሲያያዝ የመጣ እንደ ነ፣ በቅዱስ ጴጥሮስ እና በሌሎችም ቅዱሳን ሐዋርያት የእምነት መሠረት ላይ የታነጸች መኗን ልብ ይሏል::
ወደ ቆሮንቶስ የተላከ መልእክት
ይህ መጽሐፍ በቅዱስ ቀሌምንጦስ ዘሮም እንደ ተጻፈ የሚታመንና በሌሎች አኀት አብያተ ክርስቲያናት እንዲሁም በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ዘንድ ተቀባይነት ያለው ነው፡፡ ከላይ ካየነውና የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ. ከምትቀበለው መጽሐፍም የተለየ ነው፡፡ መጽሐፉ 59 ምዕራፍ ያለው ሲኾን፡- ምእመናን መጽሐፍ ቅዱስን ኹልጊዜ ማንበብ እንደሚገባቸው፣ ኔሮን ቄሳር ስላደረሰው ስደት፣ መሠረታዊ ስለሚባሉት የቤተ ክርስቲያን ትምህርቶች (ስለ ቅድስት ሥላሴ፣ ስለ እምነትና ምግባር፣…)፣ በጥንታዊቱ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ቅዳሴ ምን ይመስል እንደ ነበር፣ ፌኖሽያ ከተባለች ወፍ ጋር በማያያዝ ስለ ትንሣኤ ሙታን መኖር እንዲሁም ሌሎች ብዙ ነገሮችን ያስተምራል፡፡
ዕረፍቱ
አባታችን ቅዱስ ቀሌምንጦስ ዘሮም በብዙ ከተሞች ወንጌልን ሰብኳል፤ ብዙዎችንም  እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ መርቶ አሳምኗል:: ይህንን የሰማው የወቅቱ የሮማ ንጉሥ ጠራብሎስ ወታደሮቹን ልኮ አስመጣው፤ ክርስቶስን ክዶ ጣዖታትን እንዲያመልክ አዘዘው:: ትእዛዙንም እንዳልሰማ ባየ ጊዜ ሕዝቡን ፈርቶ በዚያ ማሰቃየትን ስላልወደደ ወደ ሌላ ከተማ ሰደደው:: የከተማይቱንም ገዥ በብዙ ማሰቃያ እንዲያሰቃየው አዘዘ፤ ያም ገዥ ከባድ ብረት በአንገቱ አስሮ ወደ ባር ወረወረው:: ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ አደራ ሰጠ እንዳስተማሩ ሐዋርያትም የሰማዕትነትን አክሊል ተቀዳጀ:: በዓመቱም የቀሌምንጦስ ሥጋው በባሩ ላይ ታየ በጥልቁም እንደ ሕያው ያስተምር ነበር:: ምእመናን ሥጋውን አውጥተው ለመውሰድ ፈልገው አልንቀሳቀስ ላላቸው ፈቃዱ እንዳልውቀው ትተውት ዱ:: በየዓመቱም ሥጋው ይገለጥላቸው ነበር እነርሱም እየመጡ ይባረኩ ነበር፤ ከሥጋውም ብዙ ልዩ ልዩ ተአምራት ይደረጉ ነበር /ሕዳር 29 የሚነበብ ስንክሳር/::


ለእግዚአብሔር ምስጋና ይኹን፤ እኛንም በሐዋርያ ቀሌምንጦስ ጸሎት ይማረን፤ በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር፤ ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

1 comment: