Friday, January 22, 2016

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የተረጐመው የኦሪት ዘፍጥረት መጽሐፍ በገበያ ላይ ዋለ!


(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ጥር 13 ቀን 2008 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
     በ388 ዓ.ም. ዐቢይ ጾም መግቢያ ላይ ተጀምሮ፥ በቀጣዩ ዓመት ጥቅምት መጨረሻ ላይ የተጠናቀቀው የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የኦሪት ዘፍጥረት የትርጓሜ መጽሐፍ የመጀመሪያ ቅጹ በገበያ ላይ ዋለ፡፡ ይህ ከሐዋርያት ዘመን አንሥቶ በተመሠረተውና በንጉሥ ቆስጠንጢኖስ እንደ ታነፀ በሚነገረው ፓላዪያ (The Palaia) በተባለ በታላቁ ቤተ ክርስቲያን የተሰጠው ትምህርት ጠቅለል ባለ መልኩ ሲታይ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያለውን እጅግ የጠለቀ ፍቅርና የሰው ልጅም ምን ያህል ክቡር ፍጥረት እንደ ኾነ የሚያስረዳ መጽሐፍ ነው፡፡

ይህን መጽሐፍ እሑድ እሑድ ብቻ ሳይኾን በየቀኑ ይማሩ የነበሩት ምእመናን የቤት እመቤቶችና በተለያየ የሙያ ሥራ የተሰማሩ ሠራተኞች ሲኾኑ የሚማሩትም በዐቢይ ጾም ምንም እኽል ሳይቀምሱ ነው፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍትን ዕለት ዕለት በቤታቸው ውስጥ የሚያጠኑ ነበሩ፡፡ ሊቁም ይህን እንዲያደርጉ በእጅጉ ያበረታታቸው ነበር፡፡ በሊቁ የማስተማር ስልት ምእመናን ሰማዕያን ብቻ እንዲኾኑ አይፈቅድላቸውም፡፡ ወደ ቤታቸው ከሔዱ በኋላ ያስተማራቸውን ትምህርት እንደ ገና ሊያጠኑት፣ ከቤተሰባቸው አባል ጋር ሊወያዩበት - ለዚህም አባወራዎች ኃላፊነቱን መውሰድ እንዳለባቸው አጽንቶ ይነግራቸው ነበር፡፡ ከቤተሰብ አባላት ጋር ብቻ ሳይኾን ከጎረቤቶቻቸው፣ ከጉባኤው ከቀሩት እንዲሁም ከጓደኞቻቸው ጋር በየመንገዱ ሳይቀር መጽሐፍ ቅዱስን እያጠኑና እየተወያዩ እንዲሔዱ ይመክራቸው ነበር፡፡ በመኾኑም፥ ምእመናኑ መጽሐፍ ቅዱስን አዘውትረው የሚያነቡና የሚያጠኑ ነበሩ፡፡
እርስዎም እነዚህን ምእመናን በመምሰል ይህን መጽሐፍ አንብበው ክርስቲያናዊ ሕይወትዎን ያሳድጉበት፤ የቅድስናን ጎዳና ይያዙበት፤ የዘመኑ ሐራጥቃዎች (ተሐድሶአውያን) ስማቸውን ከቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አገናኝተው መናገራቸው እውነት ይኹን ውሸት እርስዎ ራስዎ የሊቁን ትምህርት አንብበው ይረዱበት፡፡
v የመጽሐፉ የገጽ ብዛት - 273
v የመጽሐፉ ዋጋ - 82 ብር
የበለጠ መረጃ ለማግኘትም ኾነ መጽሐፉን በብዛት ለማከፋፈል ከወደዱ፡-
ü 0912 07 45 75 ብለው በቀጥታ ወይም በቫይበር መደወል ይችላሉ፡፡
ü ከዚህም በተጨማሪ በኢሜይል አድራሻ gebregzabher@gmail.com ብለው መገናኘት እንችላለን፡፡
          መልካም የተግሣጽ ጊዜ ይኹንልዎት!!!

4 comments:

  1. ገብረ እግዚአብሔር ቃለ ህይወት የያሰማልን አገልግሎህ እግዚአብሔር ይባርክልህ

    ReplyDelete
  2. እግዚአብሔር ይባርክልን እድሜና ጤና ይስጥልን እሺ እንገዛለን፡፡

    ReplyDelete
  3. እግዚአብሔር አገልግሎትህን ይባርክልህ፣ ወደፊትም ሌሎች መጻሕፍትን እንጠብቃለን፣ መልካም የአገልግሎት ዘመን ይሁንልህ

    ReplyDelete
  4. እግዚአብሔር አገልግሎትህን ይባርክልህ፣ ወደፊትም ሌሎች መጻሕፍትን እንጠብቃለን፣ መልካም የአገልግሎት ዘመን ይሁንልህ

    ReplyDelete

FeedBurner FeedCount