Pages

Tuesday, July 3, 2018

ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ



ገብረ እግዚአብሔር ኪደ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሰኔ 26 ቀን 2010 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !

 ማስታወሻ! ይህ ጽሑፍ ለሥልጠና ተብሎ በ “Power Point” ከተዘጋጀ ማስታወሻ እንደ ወረደ የቀረበ ስለ ኾነ በየንኡስ ርእሱ የቀረቡ አሳቦች በዝርዝር የቀረቡ አይደለም፡፡ ኾኖም ግን ዋናውንና ጠቋሚውን ብዬ ያሰብሁትን አሳብ ስላስቀመጥሁ አንባብያን ይህን መነሻ አድርገው እንደ ንባባቸውና ዕውቀታቸው እንደ ልምዳቸውም ሊያስፋፉት ይችላሉ !

 መግቢያ !
   ሕፃናትን ኦርቶዶክሳዊ አድርጎ ለማሳደግ መጀመሪያ ወላጆች ኦርቶዶክሳውያን መኾን አለባቸው፡፡
      ስለዚህ ስለ ሕፃናት ስናስብ ገና ከትዳር አጋራችን አመራረጥ መጀመር አለብን፡፡
      ምንጩ ከደፈረሰ ወንዙ ይደፈርሳልና፡፡
      ጌታችንም ሲናገር፡- “ከእሾኽ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን?” ብል (ማቴ.7፡16)፡፡
      ሐዋርያውም፡- “ሰው የሚዘራውን ኹሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳል” ብል (ገላ.6፡7)፡፡
      ስለዚህ የምንዘራውን ዘር ማስተካከል የግድ አስፈላጊ ነው፡፡
በመኾኑም፡-

) ኦርቶዶክሳዊ የትዳር አጋርን ከመምረጥ ይጀምራል!
ü  ወጣቶች ወደ ትዳር ከመግባታቸው በፊት የትዳር አጋር አመራረጥ ላይ ብዙ ሊደክሙ ይገባል፡፡
ü  አንድ ዕቃ ስንገዛ ለምንገዛው ዕቃ በቂ የሚባል መረጃ እንሰበስባለን፤ ለትዳር አጋር ደግሞ ከዚህ በላይ!
ü  ፈቃደ እግዚአብሔርን መጠየቅ!
ü   የትዳር ዓላማን መረዳት! “ቅዱሳን ልትኾኑ ለተጠራችሁእንዲል ጽድቅ መኾኑን በደንብ መረዳት ያስፈልጋል (ሮሜ.17)
ü ይህ ነገ ለምንወልደው ልጅ ኦርቶዶክሳዊ ኾኖ ማደግ እጅግ ወሳኝ ነው!
ለ) ኦርቶዶክሳዊ የሰርግ ሥርዐትን መከተል
v  በቃና ዘገሊላ ለመጨረስ በቃና ዘገሊላ መጀመር!
v  እግዚአብሔር፣ ቅዱሳን እንዲኖሩ ማድረግ!
v  ስለዚህ በተክሊል ወይም በመዓስባን ሥርዓት ወደ ትዳር በዓት መግባት !
v  ሲመሠረት ዓለት ላይ ሳይኾን አሸዋ ላይ ከኾነ አይጸናም ! ፈተና ሲገጥመው፣ ጎርፍ ሲጎርፍበት፣ ንፋስ ሲነፍስበት ይወድቃል (ማቴ.7፡25-26)!
ሐ) ወደ ትዳር በዓት ገብተው ትንን ቤተ ክርስቲያን መመሥረት (ሮሜ.16፡5)!
      ለትን ቤ/ክ. የሚኾኑ ንዋያት ማዘጋጀት፡- ቦታ፣ ሥዕላት፣ መጻሕፍት፣ መብራቶች !
      ንስሐ አባት ማስባረክ!
      አገልግሎን ማከናወን፡- ጸሎት፣ ትምህርት (ስብከተ ወንጌል)
ከዚህ በኋለስ?
ሀ) ከእናታቸው ማኅፀን መጀመር !
      ፅንስ ይሰማል፤ የእናቱን እንቅስቃሴ ያዳምጣል!
       በእናቱ ዓይን ያያል፤ በእናቱ ጆሮ ይሰማል!
       እናት ስታዝን ያዝናል፤ ስትደሰትም ይደሰታል!
       እናት ትወደው እንደ ኾነና እንዳልኾነ ያውቃል!
       ቅዱስ የኾነ ተግባር አከናውና ስትደሰት አብሮ ይደሰታል!
       ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚኾነን መጥምቁ ዮሐንስ ነው!
      ስለዚህ አንዲት እናት ስታረግዝ ልትጸልይ፣ ልጅዋን ልትወድ፣ ሆድዋን በፍቅር ልትደባብስ፣ መጻሕፍት ልታነብ፣ መዝሙር ልትዘምር፣ በአጠቃላይ መንፈሳዊ ሕይወት ልትኖር ይገባል!
      ወላጆች የቅድስና ሕይወት ሊኖሩ ይገባል !
       ወላጆች ንስሐ የሚገቡ፣ የሚያስቀድሱ፣ የሚቆርቡ ቢኾኑም እንን የሚወቃቀሱና የሚጣሉ ከኾነ ልጆቻቸው ላይ ጠባሳ ያሳድራል፤ ልጆች አድገው ትዳር ሲይዙ የሚጣሉ ሊኾኑ ይችላሉ! 
ለ) ከተወለዱ በላም፡-
ለ.1.) ከልክ በላይ አለመንከባከብ
      በኹሉም ረገድ እንዳይበስሉ ያደርጋቸዋልና !
     ኹሉንም ነገር እኛ የምንጨነቅላቸው ከኾነ ራሳቸው ማድረግ የሚገባቸውን አያደርጉምና!
      ስለዚህ ልብሳቸውን መልበስ የሚችሉበት ዕድሜ ሲኾኑ ራሳቸው መልበስ አለባቸው!
      ጫማቸውን ማውለቅና ማድረግ የሚችሉ ከኾነ እነርሱ ራሳቸው ይህን ማድረግ አለባቸው!
      ገላቸውን ራሳቸው እንዲታጠቡ ማድረግ!
      መከራን እንዲለምዱ ማድረግ - ለምሳሌ ሌሊት መነሣትን፣ ብርድን፣ ረሃብን
      እያንዳንዱን ነገር አትንካ ማለት አይገባም፤ እሳትም ቢኾን! እየተከታተልነው እሳቱ እንደሚያቃጥል ማወቅ አለበት ! 
ለ.2.) ስለ እነርሱ ብዙ መጸለይ!
      እናት ልን ሥጋዊ ምግብ ብቻ ልትሰጠው አይገባም!
      በጸሎትም ልታስበው፣ ልታግዘው ይገባታል!
     ይህ በምሥጢር ልጆቹን መጠበቅ ነው!
      ብዙ እናቶች ልጆቻቸውን ይቆጣሉ፤ ይመክራሉ ይዘክራሉ፡፡ የሚጸልዩላቸው ግን ጥቂቶች ናቸው፡፡
      ብዙ ቁጣና ምክር ግን ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡
      ምክንያቱም ቁጣና ምክር ጆሮ ላይ ነው፤  ጸሎት ግን ልብን ይለውጣል!
ለ.3.) ብዙ ጸሎት፣ ጥቂት ቃላት!
      ልጆቻችንን የምንወድበት መውደድ እንዲሁ ዕሩቅ ፍቅር ሳይኾን ቅዱስ ፍቅር ሊኾን ይገባል
      ሲያጠፉ ጥፋታቸውን ለማስተካከል ጥቂትና አግባብ ባለው መልኩ ተቆጥተን ቀጥተንም ብዙ ልንጸልይላቸው ይገባናል !
      ስንቀጣቸው እንን ሰይጣን አብሮ እንዳይቀጣቸው ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል !
      “አምላክ ሆይ! ለልጆቼ ማስተዋልን ስጥልኝ፡፡ እነሆ እነዚህን ልጆች ሰጠኸኝ፤ ነገር ግን እነርሱን ወደ አንተ ለመምራት ደካማ ነኝና እርዳኝ፡፡”
      ያን ጊዜ እግዚአብሔር ያናግራቸዋል፤ “ወላጆቼን ላሳዝን አይገባም” እንዲሉ ያደርጋቸዋል፡፡
      ስለዚህ እኛ ለእግዚአብሔር እንንገረው፤ እግዚአብሔርም ልጆቻችንን ያናገራል
ለ.4.) ምሳሌያዊ ሕይወት መኖር!
      እግዚአብሔርን በልጆቻችን ማየት ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ ቅዱስ የኾነ ፍቅር ለልጆቻችን መስጠት!
      የጸሎት ደም ሊኖራቸው ይገባል፤ ጸሎትን የሚማሩ ሊኾኑ ይገባል!
      ልጅ እንዲህ አድርግ ስለ ተባለ ብቻ የተባለውን አያደርግም፤ የሚያደርገው ሲደረግ ያየውን ነው፡፡
      ስለዚህ ቤ/ክ. እንዲኼድ ከመምከር ይልቅ መርቶ መውሰድ ያስፈልጋል!
      ስንጸልይ፣ ንስሐ ስንገባ፣ ስንቆርብ ሊያዩን ይገባል፡፡
      መጻሕፍትን ስናነብ ሊያዩን ይገባል፡፡
      ስንመጸውት ሊያዩን ይገባል፡፡
      ከአፍአ ሲታይ ከባድ ይመስላል፤ ከሕፃንነታቸው አንሥተው ከተለማመዱት ግን ቀላል ነው፡፡
ለ.5.) ረድኤተ እግዚአብሔርን እንዲለምኑ ማለማመድ!
      ሕፃናት አንድን በጎ ነገር ሲያከናውኑ ዘወትር ማመስገን አይገባም!
      ራሳቸውን ዝቅ እንዳያደርጉና ውዳሴ ከንቱን የሚወዱ ያደርጋቸዋል! ኹሉም ሰው እንዲያመሰግናቸው ይፈልጋሉ!
      ችግር ሲፈጥሩ እንን መመስገንን እንጂ መገሠጽን አይፈልጉም፡፡
      ወደ ቅዱሳን አባቶች ስንኼድ አያመሰግኑንም፡፡ “ይህ ይቀርሃል፤ ይህን ደግሞ አድርግ” ነው የሚሉን!
      ዓለም በሥነ ልቡና ባለሙያዎች ይህን አለአግባብ እየጫነችብን እንደ ኾነ መገንዘብ ያስፈልጋል!
      ስለዚህ አንድ በጎ ነገር ሲያከናውኑ እግዚአብሔርን አጋዥ አድርገው እንደ ሠሩትና ምስጋናውም የሚገባው እርሱ እንደ ኾነ እነርሱ ግን ራሳቸውን ዝቅ ማድረግን ማለማመድ ያስፈልጋል!
ለ.6) ኦርቶዶክሳዊ አናቅጸ ሕይወትን ማነጽ
      አንደበት፡- በጎ ቃልን ማለማመድ፤ “ቃልህ ለጉሮሮዬ ጣፋጭ ነው” እንዲል (መዝ.118፡103)
      ጆሮ፡- በመጽሐፍ ቅዱስና በቅዱሳን ታሪክ ማነጽ !
      አፍንጫ፡- በዕጣኑ በጎ መዓዛ ማሳደግ፣ …
      ዓይን፡- ሊያዩት የሚገባውን መምረጥ
      ገሲስ፡- ምቾት ተኮር ብቻ ሊኾን አይገባም !
ለ.7) ሰብእናን ማሳደግ
      ልብ፡- በጎ መዝገብን የሚያወጣ፣ ራሱን የሚገዛ፣ የማይቆጣ እንዲኾን ማለማመድ! ለምሳሌ ይህን የተመለከተ ታሪክ ነግሮ በታሪኩ መሠረት መተንኮስ!
      ምኞት፡- በጎ ምኞት! ዝሙትን የሚቀሰቅሱ ትርኢቶችንና ዜማዎችን ማራቅ! ጾም፣ ጸሎት ማስለመድ! ዕድሜው ሲደርስ እንደ ደኛ ማድረግና በግልጽ መጨዋወት!
      አመክንዮ፡- የዚህን ዓለም ብልጭልጭ ነገሮችን ሳይኾን አስቀድሞ ጽድቁንና መንግሥቱን እንዲሻ ማድረግ!  
አበውስ ምን አሉ?
      “ልብህ በእምነትም በፍቅረ እግዚአብሔርም ሲበለጽግ ይህን የሃይማኖት ዓቅም ለልጅህ በብዙ መንገድ ማስተላለፍ ይቻልሃል” ቅዱስ ሄሬኔዎስ
      “ልጆችን ለማስተማር ውጤታማው ዘዴ ጥቂት ቃላት፣ ብዙ ምሳሌያዊ ሕይወትና የማይታጎል ጸሎት ነው” አንድ ቀሲስ
      “አባቶች እናቶችም ሆይ! ልጆቻችሁን ወደ ቤ/ክ. ይዛችቸው ኑ” ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ 

ወስብሐት ለእግዚአብሔር !

No comments:

Post a Comment