Showing posts with label ለመላው ኦርቶዶክሳውያን ፦ ታላላቅ የአንድነት የስብከትና የዝማሬ ጉባኤያትን ስለማዘጋጀት - ጥቆማ. Show all posts
Showing posts with label ለመላው ኦርቶዶክሳውያን ፦ ታላላቅ የአንድነት የስብከትና የዝማሬ ጉባኤያትን ስለማዘጋጀት - ጥቆማ. Show all posts

Thursday, January 9, 2014

ለመላው ኦርቶዶክሳውያን ፦ ታላላቅ የአንድነት የስብከትና የዝማሬ ጉባኤያትን ስለማዘጋጀት - ጥቆማ



በታምራት ፍሰሓ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ጥር ፪ ቀን፣ ፳፻፮ ዓ.ም.)፡- ኦርቶዶክሳዊት እምነታችን በብዙ መስክ (በቅዳሴ ፡ በማህሌት ፡ በሰአታት ፡ በሰርክ ጉባኤያት ፡ በበዓላት ዝግጅቶች) በልዩ ስርአት ና ወጥነት ሐዋርያዊ መሰረተ እምነቷን ለምእመናን ስታስተላልፍ ቆይታለች ፡ አሁንም በማስተላለፍ ላይ ትገኛለች፤ በቅዳሴው ለተካፈለ ፡ በማህሌቱም ለተሳተፈ ፡ በሰአታቱም ለተገኘ ፡ በሰርክ ጉባኤውም ላልቀረ ይህ እሙን ነው፡፡ ነገር ግን ስንቶቻችን በነዚህ ተገኘን? ካልተገኘንስ እንደምን እምነታችንን ልናውቅ ፡ በእምነታችንስ ልንፀና ይቻለናል?

ብዙወቻችን ደግሞ የቤተክርስቲያን ታላላቅ በዓላትን (ደመራ ፡ ጥምቀት) መሰረት በማድረግ ተገኝተን እናከብራለን ፡ ይህም በጣም ብዙ ኦርቶዶክሳዊ በአንድነት የሚገናኙባቸው ክስተቶች ቢሆኑም ፡ ነገር ግን እኒህ ልዩ በዓላት እንደመሆናቸው የራሳቸው የሆነ የአከባበር ስርአትና ይዘት ያላቸው በመሆኑ በዚህ ጊዜ ለሚገኙ ምእመናን የሚገባውን ያህል ትምህርት ሰጥተው የሚያልፉ አይደለም ፡ ይልቅስ በነዚህ በዓላት ጥቂት ከመዘመርና በዓሉን የመታዘብ ያክል ከተመለከትን በኅላ ወደቤታችንም ሆነ ወደሌሎች ጉዳዮች የምንመለስ ብዙወች ነን፡፡ ስለዚህም ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ በአንድነት ተሰባስበን የቤተክርስቲያናችንን ስብከቷን ፡ ዝማሬዋንም ሆነ ልዩ ልዩ ሃሳቦቿን የምንረዳባቸው ፡ የምንሳተፍባቸውና የምንወያይባቸው መድረኮች የሉንም፡፡

FeedBurner FeedCount