በቅዱስ
ዮሐንስ አፈወርቅ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ጥር 27 ቀን 2008 ዓ.ም.)፡- በስመ
አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ለአንድ
ክርስቲያን መከራው ለጥቅሙ የሚሰጠው ነው፡፡ ለአንድ ክርስቲያን መከራን
መቀበል ማለት ከሰማያዊ ክብር መሳተፍ ነው፡፡ ይህስ እንደ ምን ነው ያልከኝ እንደ ኾነም እንዲህ ብዬ እመልስልኻለሁ፡- ስንፍናንና
ክፉ ፈቃድን የሚያርቅ፣ ዓለማዊ ግብርን መውደድን፣ ውዳሴ ከንቱ መውደድን የሚያርቅ ነውና የክርስቲያን መከራው ክብርን ያስገኛል፡፡
ነፍስን የሚረዳ፣ በክብር ላይ ክብርን የሚያገኝ ነውና የክርስቲያን መከራው የሚያሳዝን መከራ አይደለም ብዬ እነግርኻለሁ፡፡