(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሰኔ 2 ቀን፣
2007 ዓ.ም.)፡- በስመ
አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
የእሑድ
ዕለት ፍጥረታት
የእሑድ
ሰዓተ ሌሊት ፍጥረታት
እሑድ
ማለት የዕለታት መጀመሪያ ማለት ሲኾን ይኸውም እግዚአብሔር ፍጥረቱን የፈጠረበት የመጀመሪያው ቀን ነው፡፡ በዚህ ዕለት ስምንት ፍጥረታት
የተፈጠሩ ሲኾን፥ እነርሱም፡-
ü በመጀመሪያ ሰዓተ ሌሊት - አራቱ
ባሕርያተ ሥጋ እና ጨለማ፣
ü ከኹለተኛው ሰዓተ ሌሊት እስከ ዘጠነኛው ሰዓተ ሌሊት - ከእሳት
ሙቀቱን ትቶ ብርሃኑን ወስዶ ሰባቱ ሰማያትን፣
ü በዘጠነኛው ሰዓተ ሌሊት ደግሞ
መላእክትን ፈጠረ፡፡
እስኪ
እያንዳንዳቸውን በመጠን በመጠኑ እንመልከታቸው፡፡