Tuesday, September 8, 2015

Wednesday, August 26, 2015

ትምህርተ ሃይማኖት - ክፍለ ዐሥራ አራት



(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ነሐሴ 21 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
የሰኞ (ሠኞ) ፍጥረት
ሰኞ የሚለው ቃል “ሰነየ - ሰኑይ” ከሚል የግእዝ ቃል የተገኘ ሲኾን፥ ትርጓሜውም መሰነይ፣ ኹለት ማድረግ፣ ኹለተኛ ዕለት ማለት ነው፤ ሥነ ፍጥረትን ለመፍጠር ኹለተኛ ቀን ነውና፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ፥ ሠኑይ ማለት ሠነየ፣ ሠናይ፣ አማረ፣ ተዋበ፣ በጌጥ በመልክ ደስ አሰኘ ማለት ነው፤ ይኸውም በዚህ ዕለት ብርሃን ስለ ተፈጠረ ነው፡፡
      ለሰኞ አጥቢያ በጊዜ ሠርክ (የመጀመሪያው ሰዓተ ሌሊት) እግዚአብሔር በዕለተ እሑድ “ብዢ ተባዢ፤ ስፊ ተስፋፊ” ብሏት የነበረችው ውኃ ከምድር ጀምራ እስከ ኤረር ድረስ መልታ ነበር፡፡ በዚሁ ዕለት ማለትም በዕለተ ሰኑይም፥ ጠፈርን ፈጠረ /ዘፍ.1፡6-9/፡፡ እግዚአብሔር ጠፈርን በፈጠረ ጊዜም በዓለም መልቶ የነበረው ውኃ በአራት ተከፍሏል፡-
ü  የምናየው ሰማይ (ጠፈር) (ሥዕለ ማይ)፣
ü  ከጠፈር በላይ የተሰቀለው ሐኖስ፣
ü  ለምድር ምንጣፍ የኾነ ውኃና፣
ü  በምድር ዙርያ እንደ መቀነት የተጠመጠመው ውኃ (ውቅያኖስ) ተብሎ፡፡ በምድር ላይ የምናያቸው ውኆች በምድር ዙርያ ከተጠመጠመው ከዚህ ውቅያኖስ የቀሩ እንጥፍጣፊ ናቸው፡፡

Tuesday, August 18, 2015

መንፈሳዊ አገልግሎት



በዲ/ን ሕሊና በለጠ ዘኆኅተብርሃን
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ነሐሴ 12 ቀን 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
አገልግሎት የሚለው ቃል ገልገለ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ እንደሆነ ይጠቁማል፡፡ ገልገለ (አገለገለ) ማለት ተገዛ፣ ታዘዘ፣ ዐገዘ፣ ረዳ፣ ጠቀመ፣ ማንኛውንም ሥራ ሠርቶ ጌታውን  ደስ አሰኘ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ አገልግሎት ማለት መታዘዝ፣ መገዛት፣ መርዳት፣ መጥቀም…ማለት ይሆናል፡፡  ማንኛውም ሥጋዊና መንፈሳዊ ሥራ አገልግሎት ነው፡፡ ለመንግሥት የሚሠራ የመንግሥት አገልጋይ፣ ለግለሰብ የሚሠራ የግለሰብ አገልጋይ፣ ለእግዚአብሔርም የሚሠራ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ አገልጋዮችን በተለያየ ስያሜ ጠርቷል፡፡ ምንም አይነት መብት በራሱ ላይ የሌለውንና በጌታው ሐሳብ ፍፁም አዳሪ የሆነውን ተገዢ ባሪያ በማለት ገልፆታል፡፡ ንዋይ ኅሩይ ቅዱስ ጳውሎስ ‘ከሰው ሁሉ አርነት የወጣሁ ስሆን የሚበልጡትን እንድጠቅም እንደባሪያ ራሴን ለሁሉ አስገዛለሁ’ በማለት የተናረው ይህን ያጠናክራል፡፡ (1ቆሮ. 9÷19) አብሮት የሚያገለግለውን ቲኪቆስንም  ‘በጌታም አብሮኝ ባሪያ የሆነ’ በማለት ጠርቶታል፡፡ (ቁላ 4፡7) ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስም አርነት ወጥታችሁ እንደ እግዚአብሔር ቅዱሳን ባሪያዎች ሁኑ በማለት አገልግሎታችን በፍፁም መገዛት እንዲሆን ይመክረናል፡፡ (1ጴጥ. 2‘፡16) በራሱ ላይ ሙሉ ነፃነት ያለውን አገልጋይ መጽሐፍ ቅዱስ ሠራተኛ ይለዋል፡፡ (ሉቃ 10፡2፣ ቁላ 4፡11፣ 2ጴጥ 1፡8) ይህ ከባሪያ ይልቅ በራሱ ላይ የመወሰን ሥልጣን ያለው ነው፡፡ ከፈለገ አለማገልገል ይችላል፡፡ በባሪያና በሠራተኛ መካከል ነፃነቱ መካከለኛ የሆነው ደግሞ ብላቴና፣ ሎሌ ተብሎ የተጠራው ነው፡፡

Saturday, August 15, 2015

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የእሑድ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የእሑድ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ: ገ/እግዚአብሔር ኪደ (መቅረዝ ዘተዋሕዶ ነሐሴ ፲፪ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም.)፡-  በዚህ ዕለት እመቤታችን ከወትሮው ይልቅ ቀደም ብላ መጥታለች፡፡ “ዛቲ ዕለት ተዓቢ እምኩሎን ዕለታት፤ ወውዳሲያቲሃኒ የዓብያ እምኵሉ ውዳሴያት...

FeedBurner FeedCount