Friday, April 22, 2016

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : ስግደት (ክፍል 1)


በፍጹም ልብ በፍጹም ነፍስ በፍጹም ኃይል (ዘዳ.65) የሚወደድ የሆነውን አምላካችን እግዚአብሔርን ስናመልከው ሥጋችንንም፣ ነፍሳችንንም፣ መንፈሳችንንም አስተባብረን መሆን አለበት፡፡ መጻሕፍትን በማንበብ፣ ለብዎትን /ማስተዋልን/ በመጠቀም፣ ዕውቀትን ገንዘብ በማድረግ፣ ነቢብን /ንግግርን/ በማስገዛት፣ ሀልዎትን /መኖርን/ በመሠዋትና በመሳሰሉት እግዚአብሔርን ማምለክ ባሕርያተ ነፍስን ለአምልኮተ እግዚአብሔር ማስገዛት ነው፡፡ ጾም/ከሥጋ ፍላጎት መከልከል/ እና ስግደትን የመሳሰሉት ደግሞ በሥጋ እግዚአብሔርን የምናመልክባቸው፣ ሥጋችንን የምናስገዛባቸው መንገዶች ናቸው፡፡ (ይህ ማለት ግን ስግደት ለሥጋውያን ብቻ የተገባ ነው ማለት አይደለም፤መላእክቱ ሁሉ ስገዱለት”/መዝ.977/ እንዳለ መላእክትም የሚሰግዱ ናቸውና፡፡) ፍቅር፣ ቸርነት፣ ምኅረት፣ መመጽወት እና የመሳሰሉት የመንፈስ ሥራዎች ደግሞ ወደ ፍጹምነት የሚወስዱን የሥጋን ድካምና የነፍስን ሐልዮት የምንቀድስባቸው እንዲሁም መንፈሳችንን ለአምልኮተ እግዚአብሔር የምናስገዛባቸው መንገዶች ናቸው፡፡
ስለዚህ ስግደት የሰው ልጅ የተፈጠረበትን ዓላማ (የሰው ልጅ የተፈጠረበት ዓላማ እግዚአብሔርን ማምለክ ነው) ከሚያሳካባቸው መንገዶች አንዱ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር የሰው ልጅ ካለስግደት ሥጋውን ፍጹም መኮነን(መግዛት) አይችልምና ሰብእናው ምሉዕ አይሆንም፡፡ Read More here= መቅረዝ ዘተዋሕዶ : ስግደት (ክፍል 1)

Monday, April 18, 2016

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : ሰማዕታት

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : ሰማዕታት: (መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሚያዝያ 17 ቀን 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!         ሰማዕት የሚለው ቃል ስርወ ቃሉ “ሰምዐ” የሚል ሲኾን ይኸውም ሰማ፣ አደመጠ፣ አስተ...

Sunday, April 17, 2016

ኒቆዲሞስ


(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሚያዝያ 9 ቀን 2008 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ኒቆዲሞስ ማለት ድል አድራጊ፣ የሕዝብ አለቃ ማለት ነው፡፡ እውነትም ይህ ሰው አለቃ ነበር፡፡ አለቅነቱስ እንደ ምን ነው? ቢሉ በሦስተ ወገን ነው፡-

() በሹመት፡-
የአይሁድ ሸንጎ - ማለትም የሳንሄድሪን - አባል ነበርና፡፡ ይህ እንግዲህ (ምንም እንኳን የሚያውክ ንጽጽር ቢኾንም) በእኛ ስናየው የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የኾነ አንድ ሊቀ ጳጳስ እንደ ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ዝቅ ብሎ ሊማር መጣ፡፡ ከማን? ብለን ስንጠይቅ ደግሞ ይበልጥ እንደነቃለን፡፡ ምክንያቱም ምንም እንኳን ጓደኞቹ ትምህርትን የማይወዱ፣ እውነትን የሚጠሉ፣ ጌታችንን ለመግደል ዕለት ዕለት የሚመክሩ ቀናተኞች ቢኾኑም ኒቆዲሞስ ግን ከእነርሱ ተለይቶና ሹመቱ ሳያስታብየው በሥጋ ዕድሜ ከእርሱ ከሚያንስ ከጌታችን ዘንድ ሊማር ነውና የሚመጣው፡፡ እስኪ ትልቅ ጥምጣሙን አድር ከጌታችን እግር ሥር ቁጭ ብሎ ሲማር በዓይነ ሕሊናችሁ ሳሉት! እንደ ምን ያለ ትሕትና ነው? እንዴት እውነትን የተጠማ ሰው ነው? “ቀን አይመቸኝምና ማታ አልሔድም፤ እንደዉም ጥሩ ምክንያት አገኘሁአላለም፡፡ ከጓደኞቼ ጋር ተመሳስዬ ልኑር አላለም፡፡ ጌታችን የወደደውና ለትውልድ ኹሉ የተረፈ ምሥጢር - ስለ ጥምቀት - ያስተማረውም ስለዚሁ ግሩም ትሕትናውና ቅንዓቱ ነው፡፡ሥራህን ትተህ ለምን በቀን አትመጣም?” አላለውም፡፡አንተን ብቻ አላስተምርምአላለውም፡፡ለምን ጓደኞቼ ያዩኛል ብለህ ፈራህ?” አላለውም፡፡ለምን እንደ ዕሩቅ ብእሲ ቈጥረህ መምህር ትለኛለህ?” አላለውም፤ በፍጹም፡፡ ሹመቱና እልቅናው ሳይታሰበው ዝቅ ብሎ ሊማር መጥቷልና፡፡አለቃ ስኾን እንዴት ለመማር - ያውም በጨለማ - እሔዳለሁ?” አላለምና፡፡ በመኾኑም ቸሩ ጌታችን እንደ ሳምራይቱ ሴት ለብቻውም ቢኾን የማታ ክፍለ ጊዜ አዘጋጀለት፡፡ 

FeedBurner FeedCount