Wednesday, August 21, 2019

ድንግል ማርያም ተነሥታለች!


በዲ/ን ኄኖክ ኃይሌ
(ከመጽሐፈ ገጹ የተወሰደ)
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ነሐሴ 14 ቀን 2011 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በልጅዋ ፈቃድ ከሞት መነሣት ኦርቶዶክውያን አባቶች ሲያስተምሩ ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚጠቅሱት ማስረጃ በመዝ. 1318 ላይ ያለውን ‹‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት›› የሚለውን ቃል ነው፡፡ ይህንን ጥቅስ ከድንግል ማርያም ትንሣኤ ጋር አያይዞ መጥቀስ አሁን የተጀመረ ነገር ሳይሆን ብዙ ክፍለ ዘመናትን ያስቆጠረ ነገር ነው፡፡ ሠላሳ ሦስተኛው የእስክንድርያ ፓትርያርክ ቅዱስ ቴዎዶስዮስ ከእርሱ ቀድመው የተነሡ አበው ያስተላለፉለትን የእመቤታችንን ዕረፍትና ትንሣኤ ታሪክ የዛሬ ከአንድ ሺህ አምስት መቶ ዓመታት በፊት በጻፈው ድርሳን ላይ በነገረ ማርያም ሊቃውንት ዘንድ Doctor of Dormition በመባል የሚታወቀው ሊቁ ዮሐንስ ዘደማስቆ ሐዋርያውያን አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ በድርሳኖቻቸው ላይ ስለ ድንግል ማርያም ትንሣኤ ባነሡና በዓለ ዕርገትዋን ባከበሩ ቁጥር የሚያነቡት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ‹‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት›› የሚለውን የዳዊት መዝሙር ነው፡፡ በእርግጥ ይህንን ቃል ከድንግል ማርያም ጋር ምን ያገናኘዋል? ‹ማርያም ተነሣችየሚል ነገር አለውን? የሚለውን ጥያቄ በዚህች አጭር ጽሑፍ እንመለከታለን፡፡ ወደዚህ ጉዳይ ከመግባታችን በፊት ግን አንድ ቁምነገርን እናስቀድም፡፡

Tuesday, July 3, 2018

ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ



ገብረ እግዚአብሔር ኪደ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሰኔ 26 ቀን 2010 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !

 ማስታወሻ! ይህ ጽሑፍ ለሥልጠና ተብሎ በ “Power Point” ከተዘጋጀ ማስታወሻ እንደ ወረደ የቀረበ ስለ ኾነ በየንኡስ ርእሱ የቀረቡ አሳቦች በዝርዝር የቀረቡ አይደለም፡፡ ኾኖም ግን ዋናውንና ጠቋሚውን ብዬ ያሰብሁትን አሳብ ስላስቀመጥሁ አንባብያን ይህን መነሻ አድርገው እንደ ንባባቸውና ዕውቀታቸው እንደ ልምዳቸውም ሊያስፋፉት ይችላሉ !

 መግቢያ !
   ሕፃናትን ኦርቶዶክሳዊ አድርጎ ለማሳደግ መጀመሪያ ወላጆች ኦርቶዶክሳውያን መኾን አለባቸው፡፡
      ስለዚህ ስለ ሕፃናት ስናስብ ገና ከትዳር አጋራችን አመራረጥ መጀመር አለብን፡፡
      ምንጩ ከደፈረሰ ወንዙ ይደፈርሳልና፡፡
      ጌታችንም ሲናገር፡- “ከእሾኽ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን?” ብል (ማቴ.7፡16)፡፡
      ሐዋርያውም፡- “ሰው የሚዘራውን ኹሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳል” ብል (ገላ.6፡7)፡፡
      ስለዚህ የምንዘራውን ዘር ማስተካከል የግድ አስፈላጊ ነው፡፡
በመኾኑም፡-

Monday, June 18, 2018

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : ነገረ መላእክት (Angelology)

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : ነገረ መላእክት (Angelology): (መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ቅዳሜ ታኅሳስ 18 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!! ትርጕም   ጥሬ ቃሉን ስንመለከተው መልአክ የሚለው የግእዝ ቃል ኹለት ትርጉሞች ...

Thursday, June 14, 2018

ሙስሊሞች በክርስቲያኖች ጉባኤ


በአማን ነጸረ እንደ ጻፈው
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሰኔ 07 ቀን፣ 2010 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ጥሎብኝ፣ ክርስቲያን ወንድሞቼ ስለ ቁራን በተቃርኖ ሲተረጉሙ መስማት ይጨንቀኛል፡፡ በራሴ ደርሶ ስላየሁት ይሆናል፡፡ የቤ/ ገድላትና ድርሳናት በማያምኑባቸው ሰዎች ሲተረጎሙ በአማኝ ዕዝነ ልቡና እያዳመጥኩ ብዙ ጊዜ ቅር ይለኛል፡፡ የባለቤትነትና የማንነት ስሜት በሌለህ እምነት ውስጥ ገብተህ ስትተረጉም እንደ ምዕመን ሳይሆን እንደ ፈላስፋ ሁሉን ነገር በአመክንዮ እየፈታህ ትገጥምና ጭርሱን እምነት የሚለውን ከአመክንዮ (ሎጂክ) በላይ የሆነ አስተሳሰብ ትዘነጋለህ፡፡ ያን ጊዜ መዘንጠል ይመጣል፡፡ ያለ አነባበቡ፣ ተነሺና ወዳቂ ሳይለይ የሚያነብ ሰው በድፍረት ንባቡን ሲሾፍረው ‹‹ኧረረረረረ ዘነጥልከው!›› ይላሉ የቤ/ አስነባቢዎች፡፡ ሰው የማያምነበትን ሲተረጉም ደግሞ ዝንጠላ የማያመልጠው ግድግዳ ይሆንበታል፡፡ ጥሎብኝ፣ ከዚህ ግድግዳ መላተም አልወድም፡፡

FeedBurner FeedCount