Monday, November 10, 2014

ለይሖዋ ምስክሮች ኑፋቄ የተሰጠ ምላሽ (ክፍል ሦስት)

(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ማግሰኞ ኅዳር 2 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
የሥላሴ ትምህርት በቅድመ ኒቅያ አበው
ውድ የመቅረዝ ተከታታዮች እንደምን ሰነበታችኁ? በጥያቄና መልስ ዓምዳችን ለይሖዋ ምስክሮች የስሕተት ትምህርት ኦርቶዶክሳዊ ምላሽ መስጠት ከዠመርን የዛሬው ሦስተኛው ክፍል ነው፡፡ በክፍል አንድ ምላሻችን የይሖዋ ምስክሮች የስሕተት ትምህርቶች ምን ምን እንደኾኑ፥ እንዲኹም መሠረታዊ የምሥጢረ ሥላሴን ትምህርት በመጠኑ ዐይተናል፡፡ በክፍል ኹለት ትምህርታችንም ከብሉይ እና ከሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት በማመሳከር ምሥጢረ ሥላሴ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት እንደኾነ ተመልክተናል፡፡ ለዛሬ ደግሞ እግዚአብሔር በረዳን መጠን ከሐዋርያነ አበው ዠምረን እስከ ሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበሩ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ምን ብለው እንዳስተማሩ እንመለከታለን፡፡ ይኽን የምናደርግበት ምክንያትም የይሖዋ ምስክሮች የሥላሴ ትምህርት የተወሰነው በ325 ዓ.ም. በጉባኤ ኒቅያ በንጉሥ ቈስጠንጢኖስ አስገዳጅነት ነው ስለሚሉ ነው፡፡ እግዚአብሔር ዓይነ ልቡናችንን ያብራልን አሜን!!!

Wednesday, November 5, 2014

አምስቱ ስጦታዎች

በቀሲስ ፋሲል ታደሰ




(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ጥቅምት 27 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!! 

ሥርዓተ አምልኮ ከሚገለጥበት መንገድ አንዱ ስጦታ ነው፡፡ የሰው ልጅ ከራሱ የኾነ አንዳች የለውም፤ በጎ የኾነው ኹሉ ከፈጣሬ ዓለማት ከእግዚአብሔር ያገኘው ነው፡፡ በመኾኑም ፈጣሪያችን መስጠትን እንዳስተማረን ኹሉ እኛም ተገዥነታችንን ከምንገልጥበት አንዱ ከርሱ የተቀበልነውን በፈቃደኝነት በደስታ በመስጠት ነው፡፡ ነቢዩ ዳዊት ይኽን ሲያስረዳ “ኹ ከአንተ ዘንድ ነውና፡ ከእጅህ የተቀበልነውን ሰጥተንሃልና ይኽን ያኽል ልናቀርብልህ የቻልን ማነን? በፈቃዴ ይህን አቅርቤአለሁበማለት ከእግዚአብሔር ያገኘውን ሀብት በደስታ በፈቃዱ ለቤተ መቅደስ ሥራ እንዲውል መስጠቱን በመግለጽ ስለ ስጦታ ጽፏል /1ዜና 29÷9-16/፡፡

Monday, November 3, 2014

ትምህርተ ሃይማኖት (ክፍል አምስት)


(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ጥቅምት 25 ቀን፣ 2007 ..)- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!


ሐ) ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ አረዳድ


 እንደምን ሰንበታችኁ ውድ የመቅረዝ ተከታታዮች? ትምህርተ ሃይማኖት በሚለው ተከታታይ ትምህርታችን ውስጥ ለዛሬ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ኦርቶዶክሳዊ አረዳድን እንማማራለን፡፡ በዚኽ ጽሑፍ ውስጥ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምንነት፤ በቤተ ክርስቲያን ያለው ቦታ ምን እንደሚመስልና እንዴት መረዳት እንዳለብን እና ሌሎች ተያያዥ ሐሳቦችን እንመለከታለን፡፡ መልካም ንባብ፡፡

Wednesday, October 29, 2014

ስለ አቤልና ቃየን (ለሕፃናት)

(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ጥቅምት 20፣ 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
የተዋሕዶ ፍሬዎች፣ የሃገር ተስፋዎች እንደምን ሰነበታችኁ ልጆች? “እግዚአብሔር ይመስገን ደኅና ነን” አላችችኁ? መልካም፡፡ ትምህርት እንዴት ነው? እየጐበዛችኁ ነው አይደል? ጠንከር ብላችኁ በማጥናት ከአምናው የተሻለ ውጤት ለማምጣት እንደተዘጋጃችኁ ተስፋ አደርጋለኹ፤ በርቱ እሺ?
  ዛሬ አቤል እና ቃየን ስለሚባሉ ኹለት ወንድማማቾች ታሪክ ነው ይዤላችኁ የመጣኹት፡፡ ለመስማት ዝግጁ ናችኁ አይደል? በጣም ጥሩ!!!
 አዳምና ሔዋን በገነት ይኖሩ ነበር፡፡ ሲበድሉ ግን እግዚአብሔር ከገነት አስወጣቸው፡፡ ደብር ቅዱስ ወደ ተባለ ቦታም ተሰደዱ፡፡ ከዚኽ ቦታ ኾነውም የገነት ሽታ እየሸተታቸው ይኖሩ ነበር፡፡ ወደ ገነት ግን መቅረብ አልተቻላቸውም፡፡ ሦስት ዓመት ሙሉም በጣም ያለቅሱና ያዝኑ ነበር፡፡

FeedBurner FeedCount