Pages

Friday, May 11, 2012

ማን ሊናገረው ይችላል? /በቅ.ዮሐንስ አፈወርቅ/


በበደልን ጊዜ እግዚአብሔር ፈርዶብን ነበር፡፡ እግዚአብሔርንና ሰውን የሚያስማማ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ በመጣ ጊዜ ግን ሁለቱንም አስታረቃቸው፡፡ መለኰት የአባቱ ገንዘብ ነው፤ የእርሱም ገንዘብ ነው፡፡ ሥጋ ግን የእኛ ገንዘብ ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እነዚህ ሁለቱን ባሕርያት እርስ በእርሳቸው በተዋሕዶ አንድ አደረጋቸው፤ አንድ አደረጋቸው፡፡ እንዲህ መለያየትንም አጠፋ፡፡ ሊቀ ካህናችንም ስለሆነን የለበሠውን ሥጋ መሥዋዕት አድርጎ ወደ አብ አቀረበው፡፡ ከዚህ መሥዋዕት የተነሣም አብ አደነቀ፡፡ ስለዚህም ይህ አስቀድሞ መሬት ነህና ተብሎ የነበረው ማንነታችን ልጁ በተዋሐደው ሥጋ በእውነት አስነሣው፤ ከእርሱ ጋርም በክብር አሮረው፡፡ ይህ ሥጋ ከሰማያት በላይ መሆን አልበቃውም፤ በመላእክት ቦታም አልተወሰነም፤ ይህም ክብር አልበቃውም፡፡ ከመላእክት በላይ ሆነ፤ ከሱራፍኤል በላይ ከፍ አለ፤ ወጥቶ ከሊቃነ መላእክት በላይ ሆነ እንጂ፡፡ ወደ ላይ መውጣት ብቻም አልበቃውም፤ ወደ መንግሥት ዙፋን ወጥቶ በላዩ እስከመቀመጥ ደረሰ እንጂ፡፡ እግዚአብሔር ቀድሞ ሰውን ካወረደበት ቦታ በታች (መሬት ከመሆን የሚያንሥ) ምንም የለም፤ ዛሬም ሰውን ካወጣበት በላይ (አምላክ ከመሆን የሚበልጥ) ምንም የለም፡፡ ይህ ግሩም መለኰታዊ ፍቅር እንዴት ይረቅ? እንዴትስ ይደንቅ? ለእኛ ያደረገልን የቸርነቱን ብዛትስ ማን ሊናገረው ይችላል?

4 comments:

  1. ቃለ ሕይወት ያሰማልን ወንድማችን፡፡

    እግዚአብሔር ሰውን ከራሱ ጋር ያስታረቀበት /ዓለሙን ያዳነበት/ ጥበቡ ዕጹብና ድንቅ እንደመሆኑ መጠን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ለኛ ሊገባን በሚችል መልኩ እንዲህ አሳምሮ ማስቀመጡ እውነትም አፈወርቅነት ይገባዋል፡፡ ብዙዎች ይህንን እውነት መረዳት ተስኗቸው ከእምነት ጠገግ /ድንበር/ በአፍአ ሲሆኑ በሚታዩበት በዚህ ዘመን፤ በዚያ ዘመን /በ3ኛ መ/ክ/ዘ / የነበረው ቅዱስ ዮሐንስ እንዲህ ለሁሉ ሊረዳ በሚችል መልኩ ማስቀመጡ ይደንቃል፡፡ አሁንም እውነትንና የእግዚአብሔርን ፍቅር ይረዱ ዘንድ መለኮታዊት ብርሃን ትርዳቸው እንላለን፡፡

    ወንድማችንም እንዲህ ዓይነት ለሁሉ የሚጠቅሙ የቀደምት አበውን ምዕዳናትና ትምህርቶች ማስነበቡን በርታበት፡፡ እግዚአብሔር እጆችህን ያበረታልህ ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን፡፡ አሜን

    ReplyDelete
  2. ቃለ ሕይወት ያሰማልን!!!

    ReplyDelete
  3. ቃለ ሔይወት ያሰማልን!

    ReplyDelete