Pages

Monday, May 14, 2012

ብሒል ወምክረ አበው- ቁጥር ሁለት!!


©        “ወንጌል ነፍሰ ጡር ነች፤ መምህራንም ያዋልዷታል፡፡”
©       “ተዋሕዶ መናፍቃን የወገባቸውን ጥይት የሚጨርሱባት ሃይማኖት ነች፡፡”
©       “በእግዚአብሔር ዘንድ የሽንት ምርመራ የለም፡፡ ሲፈውስም ተረፈ ደዌ የለውም፡፡”
©       “ሰው ማለት ትልቅ ኢንዱስትሪ ነው፡፡ የሚበላውም ሁሉ ጥሬ ዕቃ ነው፡፡”
©       “አፍህና ልብህ እኩል መሥራት አለባቸው፡፡”
©       “ኦሪት እንደ እስላም የመሸኛ ጫፍ ትፈትጋለች፤ ወንጌል ግን የልብን ሳንኮፋ ትቆርጣለች፡፡”
   (መምህር ደጉዓለም ካሣ)!
v  የፍልስፍና ጣርያው የዋኅና ጥበበኛ መሆን ነው፡፡
v  ዓለም ማለት ልክ እንደ አምፊቲያትር ነች፡፡ ብዙ ተመልካች በዙርያዋ አለ፡፡ ተዋያናዩም ክርስቲያኑ ነው፡፡ ነገር ግን የሚተውነው ጭምብል አጥልቆ ሳይሆን እውነተኛ ሕይወቱን በማሳየት ነው፡፡
v  ልብህ ማየት መመኘትም ካማረው እግዚአብሔር ቀላል መፍትሔ አስቀምጦልሃል፡፡ ይኸውም ሚስትህን በደምብ አድርገህ ማየትም መመኘትም ትችላለህ፡፡ ይህን የሚከለክል ሕግ የለምና፡፡
v  ግብዞች ምጽዋትን ሲሰጡ ለተራበ ሰው አዝነው ሳይሆን እጀ ሰፊ ናቸው ብሎ አላፊ አግዳሚው እንዲያጨበጭብላቸው ስለሚወዱ ነው፡፡ ከዚህ የበለጠ ወንድምን መጥላት ግን የለም፡፡ ምክንያቱም ወንድማቸው በረሀብ እየተሰቃዬ እነርሱ ስለ ክብራቸው ይጨነቃሉና፡፡ አንተ ግን መንፈሳዊነትህ እያደገ ስትሄድ ከእንዲህ ዓይነቱ ከንቱ ነገር ሽሽ፡፡ የሰጠኸውም ሁሉ ሊቆጠር ከማችል ወለዱ ጋር ከላይ ይጠብቅሀል፡፡ መልሶም ላንተ ይሰጥሃል፡፡
     (ቅ.ዮሐንስ አፈወርቅ)! 

No comments:

Post a Comment