Pages

Saturday, June 16, 2012

በግ መሳይ- በልዑል ገ/እግዚአብሔር!


በሌሊቱ በረት ገባሁ
ያደሩትን በጎች አየሁ
ታውከዋል...
በየዋህነታቸው አሉ
በበግነታቸው ይጮሀሉ

ነጋ.....
በበረት እንዳደሩ
ለግጦሽ ሲሰማሩ
በጎቹን አየሁ
ድምፃቸውን ሰማሁ

በጎቹ.....
አረማመዳቸው የበግ:-
............................
ጎተት ጎተት
አጋጋጣቸው የበግ:-
.......................
ገመጥ ገመጥ
አጯጯሀቸው የበግ:-
.............................
በአ..በአ..

ሲቆይ.....
አንዱ ተለየብኝ
በግነቱ አጠራጠረኝ

እንግዳው.....

መልኩ የበግ:-
..........................
ያቀረቀረ
ልብሱ የበግ:-
.............................
የጠጎረ
ቅርጹ የበግ:-
.............................
የሰደረ

ግና.....
አረማመዱ እንደ ውሻ:-
.............................
ሮጥ ሮጥ
አበላሉ እንደ ውሻ:-
...................
ስልቅጥ ስልቅጥ
አጯጯሁ እንደ ውሻ:-
..............................
......

በጥርጥር ቀረብኩት
አገላብጬ አየሁት
ለካ.....
አይኑ የሌላ:-
......................'
ሚያጉረጠርጥ
አፍንጫው የሌላ:-
........................'
ሚቀላውጥ
እዝኑ የሌላ:-
.........................'
ማያዳምጥ

በግ አይደለ.....
ቀንዱ ጠፍቷል
ላቱ ቀጥኗል
ድምጹ ይለያል

እሱማ.....
በግ መስሎ በግ ሊበላ
ለምድ ለብሶ ቆዳው ሌላ
የውሻ ዘር ስሙ ተኩላ

እህ.....
ከሩቅ ሳየው:-
......
አንገቱን የደፋው
ስቀርበው በግ መሳይ:-
.....
ለካንስ ተኩላ ነው::
..........
ተጠበቅ! ...........


(
ሰኔ06/2004..)

No comments:

Post a Comment