Pages

Sunday, September 30, 2012

ከሰው ይልቅ እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት


አባታችን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በጊዜው የነበረችው ጨካኝ ንግሥት (ኤውዶክስያ) በክፋት ተነሣስታ በመንፈቀ ሌሊት አስጠርታ በፈረስ በሠረገላ አድርጋ ወደ ደሴተ አጥራክያ ስታግዘው ለራሱ እንዲህ አለ፡- ንግሥቲቱ ከከተማ ስታስወጣኝ ምንም ዓይነት ንዴት አልተሰማኝም፤ ይልቁንም ለራሴ እንዲህ አልኩ እንጂ፡-
ንግሥቲቱ ልታግዘኝ ብትወድ ታግዘኝ፤ ምድር ሁሉ የጌታ ናትና፡፡ በመጋዝ ሰነጣጥቃ ልትገድለኝ ብትሻ አርአያ የሚሆነኝ ኢሳይያስ አለ፡፡ ወደ ባሕር ልትወረውረኝ ብትፈቅድ ዮናስን አስባለሁ፡፡ ወደ እቶን እሳት ልትጥለኝ ብትፈልግ ሠለስቱ ደቂቅም እንዲህ ተወርውረው ነበር፡፡ ለሚናጠቁኝ አውሬ አሳልፋ ብትሰጠኝ በአንበሳ ጕደጓድ የተጣለውን ዳንኤል አስባለሁ፡፡ በድንጋይ እወገር ዘንድ ብትፈልግ ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስን ከፊቴ እመለከታለሁ፡፡ አንገቴን በሰይፍ መቅላት ከፈለገችም መጥምቀ መለኰት ቅዱስ ዮሐንስን እመለከታለሁ፡፡ ከእናቴ ማኅፀን ራቁቴን ወጥቻለሁ፤ ራቁቴንም ይህችን ዓለምም ትቻት እሄዳለሁ፡፡ ጳውሎስም እንዲህ እያለ ያሳስበኛል፡- “ሰውን ደስ ላሰኝ ብወድስ የክርስቶስ ባርያ ባልሆንኩ፡፡”

1 comment:

  1. Kale hiowot yasemalin egziabher amlak yeaglgilothin zemen yibark aemirohin ende mekrez yabralih Amen

    ReplyDelete