Pages

Thursday, November 15, 2012

…………. ገሊላ እትዊ …………..


በልዑል ገ/እግዚአብሔር

ደመና በወርኃ ጽጌ በበረሃ ሰፈፍ
ከገሊላ ወጥቶ በምስር ላይ ሲከንፍ
ዝናም ጣለለት ለዚያ በረሃ ግለቱ
የሐዲስ ኪዳን ምስራች አማናዊነቱ!
የሄሮድስ ጦር
ስልምልም ነው ከእሳት አይዋጋም
አዛይቱን
አዛኝቱን እመ መለኮትን አይጠጋም!
ሕጻን ከሰማይ የወረደ ድንቅ ቸር አድራጊ
ባለ እልፍ ሠራዊት ጋሸኛ ከእኩያት ተዋጊ
ብርሃን ያጣ የጨለማ መሬት ብርሃን ወጣለት
በድርሳን ቀለም ተቀልሞለት መዝገብ ተጻፈለት
የስደቱ አንድምታ ውሃ አፍስሷልና ላያደርቀው
ደመና በበጋ በግብጽ ታይቷልና ተአምር ነው!


አውሬ አፉን ከፍቶ ጥርሱን ስሎ መጥቷል
አንድ ልጅ ሊበላ ባልጠገበው ከርሱ ጎምዥቶታል
መልዕክተ ሰይጣንን በልቡ አትሞታል
ደቂቀ ቤተልሔምን በሰይፍ አስፈጅቷል!
ንግስት
ንግስት እንጂ አንቺማ ንግስተ ሰማይ ወምድር
የባህሪዬ መመኪያ አክሊለ ዘውድ የገነት በር
የወርቅ ጫማ የተገባት……... በባዶ እግር
ቤተ መንግስት የሚያንስባት በጫካ ዱር!
እኔን
እኔን እኔን እመቤቴ ራብ ጥሙ ለኔ ይሁን በደለኛው
ወርቄን ባመድ ያኖርሁ ይሁዳዊ አደራ በል ከዳተኛው!
የጋድ ምድር ሐሩር ታጥሮበታል
ከፍ ብሎ ዝቅ ብሎ እሳት ነዶበታል
ሳዕን አልባ እግርሽ ከላይ ነጉዶበታል
ምድሩን ሲቀድሰው መከራውን አይቷል!
ፍቅርኪ ማርያም በማኅበረ ጻድቃን ተወደሰ
………..…
ወፈድፋደሰ በላዕለ ኃጥኣን ነግሰ
ፍቅር ይሰድዳል የጣኦት አገር ተባረከ
ወንጌል የጠማው ጆሮ እውነትን ተሰበከ
ጋኔን ብርክ ብርክ ብሎት እምድጃ ገብቷል
የፀሐይን እናት ሲያያት መጽናት ተስኖታል!
ሀገረ ጌርሳም አቡጊዳ ፊደል ዘመድ ሁነኝ
ፍቅረ ወልድን ፍቅረ ማርያም አስተምረኝ
ግባ በሰላምንዒ ንዒ ኦፍየበልላት
መማጠኛ ከተማ ናትና አገር ዘምርላት!
እኔማ የእግርሽን ትቢያ ስሜ በተባረክሁ
የስደት መስመርሽን ፍኖትሽን በተከተልሁ
ድንቅ ብስራት በረሃ አበባ ታየበት
ለከረፋው ሰሀራ መዓዛሸ ሸተተለት!
ያቺ ወፍ
አርባ ሁለት ወራት ከገሊላ ርቃ በራለች
ፍኖተ ጽድቅ ሰርታ ከልጅ ባርካለች!
ይበቃል እናት ዓለም
አፈወ ሮማን ማርያም
ልጄን ከግብጽ ጠራሁትምስራች ተሰምቷል
መንከራተት መንገላታት ራብ ጽምዑ ተገትቷል
አሳዳጅ አረመኔ ነፍሰ በላ ከመቃብር ገብቷል
መልስ የሌለው የሞት መንኮራኩር አሳፍሮታል!
ያች ቅድስት አገርንዒ ንዒትላለች
በረከቷን ነቅታ እናትና ልጅን ተርባለች
ሀገረ ኩሽ ማረፊያ አስራትሽ ናት
በማይነጥፍ ቃሉ ልጅሽ የባረካት
በዝች አገር ስምሽ ዱካሽ ዘላለም ይታያል
አፈሯ አጸዷማርያም ማርያምይላል!
እኔ ግን
ሽባ መንፈስ እንዳላዝል ጠብቆትሽ ልቤን አደራ
የስደትሽ ማኅተሙ ማኅቶት ሆኖኝ እንዲያበራ
በሕርያቆስ በአባ ጽጌ ቃናንዒ ንዒስልሽ
የከረፋ ማንነቴ በግማቱ ከበር አይመልስሽ!
አዘክሪ
መዓዛ ህይወት መራኄ ጽድቅ ቀጺመታት
ምክኀ ደናግል ማርያም እመ ሰማዕታት
አዘክሪ ድንግል….
የበረሃ ግለቱን ቁረ ሌሊቱን
ከልጅሽ መሰደዱን መገፋቱን!
አዘክሪ ድንግል….
ራብና ጥሙን በችግር መድከሙን
በባዶ ሆድ በጥም መዐት መቃጠሉን!
አዘክሪ ድንግል ንገሪው ለልጅሽ አሳስቢው
በበደል ጦር የቆሰልን ማር ማር እንድትይው!
እናትና ልጅን ገሊላ ናፍቃለች
እጇን ዘርግታባርክኒትልሻለች!



ድንግል ሆይ
በጥማቱ አትድከሚ በማጣቱ አትራቢ
ነይ ነይከሰላሙ አገርሽ ከገሊላ ግቢ!
እመቤቴ
በቤተ ትእማን አልገኝ ከኮቲባነት ሰውሪኝ
በክንፍሽ ከልለሽ በደብረ ቁስቋም አኑሪኝ!
……………....…..
አሜን …….....…………
…………….…...... =//= …...……………..





No comments:

Post a Comment