Pages

Saturday, March 1, 2014

ቅድስት (ይህች ዕለት የተቀደሰች ናት)


(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ የካቲት 22 ቀን፣ 2006 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ

ጸልዩ እምቅድመ ንባበ ዝንቱ ክርታስ
 ከአንድ ግንድ ላይ በቅለን ከአንዱ ከኢየሱስ ክርስቶስ አካል ሆነን ከአንዱ ከኢየሱስ ማዕድ የምንበላ የአንዱ አባት ልጆች የሆንን እንደ ብሉይ ሳይሆን በእርሱ ስም ተሰይመን በእርሱ ክርሰቲያን የምንባል አንድነታችን በሞት እንኳን የማይፈታ ቤተሰቦቼ ! ዘለዓለማዊ በሆነው በእርሱ ሰላምታ ደስታ ይሁንላችሁ እላላሁ ። ይህ የሚገባ ነውና ደስ ያላችሁ ደስ ይበላችሁ ብዬ ሰላምታዬን ወደ እናንተ ላክሁ።
 በዚህ ሳምንት አባታችን ቅዱስ ያሬድ ዜማውንዛቲ ዕለት ቅድስት ይእቲ ለውሉደ ሰብእ መድኀኒት …. ” ብሎ ይጀምራል ይህች ዕለት የተቀደሰች ናት ። ለሰው ልጆችም መድሃኒት ናት። በየጊዜውና በየሰአቱ መሪ ትሁነን እግዚአብሔር ሰንበትን ቀደሰ።ልብ በሉ መቼም ሁላችሁም ሳምንቱ ምን ይባላል ብላችሁ፣ ቅድስት እንደምትሉኝ አልጠረጥርም። ለምን ቅድስት ተባለ ብላችሁ ደግሞ ቅዱስ ያሬድ ሰየመው ወይም ተዛማጅ መልስ ትሰጡኛላችሁ ። መልካም ነው ። አሁን ደግሞ ከላይ ያለውን ቀለም ካነበባችሁ በኋላ ቅድስት መባሉዛቲ ዕለት ቅድስት ይእቲብሎ በመጀመሩ ነው በሉ፤ዘምሩ።
 በዚህ ሳምንት ሰንበት ቁመት ዋዜማ ከላይ በተጻፈው ቀለም ጀምሮ የሰንበትን ቅድስና እና እኔ ቅዱስ እንደሆንኩ እናንተም ቅዱሳን ሁኑ በሚሉ ኃይለ ቃላት እስከ ቅዳሜ ድረስ የሚቆይ ጣዕመ ዝማሬ ነው። ሙሉ ዜማውን እዚህ ባናዜመው ባንሰማው ባንጽፈውም ጌታ ነፍሳችን ልትሰማው ዓይናችን ልታነበው ልባችን ልታኖረው በሕይወታችን ልንደምረው የፈቀደልንን አንዳንድ ቃላት አለፍ አለፍ እያልን ከደራሲው ጋር እናመሰግናለን።
 ሁልጊዜ መሀሪ ሰውን ወዳጅ ክርስቶስ የዓለም ንጉሥ ሕዝቡን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው ሰንበትን በእውነት አክብሩ ከላይ እያዜመ ሰንበትን ቅድስት እያለ መጥቶ ሐዲስ ላይ ይገባና በሐዲስ በእርሱ ስም ለተወለድን ለእስራኤል ዘነፍስ ሰንበት የተባለች ሰንበተ ክርስቲያንን እንድናከብር አዘዘን ። በዚህችም ቅድስት በተባለች ሰንበትመዋደድን ገንዘብ አድርጉ ሰንበትን አክብሩ ጽድቅንም ስሩ ትልና ነቀዝ የማይበላውን የማያረጀውን የማይጠፋውን ሰማያዊ መዝገብ (ሃብት) አከማቹእያለ እንዲህ ያለች ቅድሰት እንዴት ያለ ቅዱስ ስራ እንደሚሰራባት ይገልጥልናል።እንደቀደመችው ሰንበት ያጠፍነውን ሳንዘረጋ፣የቋተርነውን ሳንፈታ እንዋልባት አላለም ። ነገር ግን ሰማያዊ ባዕለ ጸጋ የምንሆንበትን በሰው ለሰው ያልሆነ ተሸጦ ተለውጦ የማይጠፋውን እናከማችባት ዘንድ ተፈጠረች አለን እንጂ።
 ከዚህ በኋላ ወደ ኋላ ተመልሶሰንበትን በእውነት ያከብሩ ዘንድ ሙሴ አዘዛቸው ሰንበትስ ለሰው ተፈጠረች፤ አብ ሰንበትን ከዕለታት ሁሉ ታላቅ አድርጎ ቀደሳት አከበራት ከፍ ከፍም አደረጋትእያለ ከላይ ያዜመልንን አጸናልን። ሰንበት ለሰው ልጆች እንጂ ሰው ለሰንበት አልተፈጠረም፤ እናም ሰው የሰንበት ባሪያ ሳይሆን ጌታ ነው ማለት ነው። በሰንበት እንደ አይሁዳውያን ታስሮ አይውልም።አንድም ያለ ስራ ቁጭ ብሎ አንድም በኃጢአት ታስሮ አይውልም። ሰማያዊ መዝገብን ሲያከማች ይውላል እንጂ፣ ሰንበትን ከፈጠራት አምላክ አልቆ በእስራት ከአምላኩ አይራቆትም።
 እንዲህ በሰንበት ስለ ሰንበት እያለ ይቆይናእግዚአብሔርም አለይለናል ሊቁ፡፡እግዚአብሔርም አለ እኔ ቅዱስ እንደሆንኩ እናንተም ቅዱሳን ሁኑ ሰንበትን በእውነት አክብሩ፣ለእግዚአብሔር ምስጋናን ሥጡ አቅርቡ ሰንበትን የቀደሳት እና ያከበራት ሰላምን ይስጣችሁብሎ ሰንበትን በማክበር በእርሷም መልካምን በመስራት እርሱን እንመስል ዘንድ በእርሱ ሰላም ይመርቀናል ። አሜን ! ብለናል። እርሱ የሚሰጠን ሰላም አለም እንደምትሰጠን ሰላም ሳይሆን እረፍት የሚሰጥ ነውና።
 ስለ ሰንበት ቅድስትነት በእያንዳንዱ ቀለሙ እያዜመ ይቆያል። ሰንበትን አብ ቀደሳት ወልድም ከፍ ከፍ አደረጋት ከስራው ከመፍጠሩ ሁሉ እንዳረፈባት ለሰው ልጆችም እረፍት አደረጋት። እርሱ ድካም የሌለበት ሰርቶ ማረፍን ሊያስተምረን አረፈ ተባለለት፤ በሰማይ መላእክት በምድር ሰዎችና እንስሳት በባህር አሳት አረፉባት
 .ያሬድ ቀጥሏል፤ አሁንንጹም ጾመብሎ ያመጣዋል ። በዚህች ቀን እንጹም ማለቱ አይደለም፤ ነገር ግን በጾማችን ጊዜ በተለይም በዚህች ቅድስት እለት የታመመን ጠይቁ፣ የታሰረን ጎብኙ፣ የተራበውን ከቤታችሁ ደጃፍ የወደቀውን አስቡ፣ ካላችሁ ትንሽም ቢሆን አካፍሉ፡፡ወናፍቅር ቢጸነ ወናትሕት ርእሰነራሳችንን ዝቅ አድርገን በልቡናችን አጎንብሰን ከእኛ በታች ንቀናቸው ያሉትን በዚህች ቅድሰት ቀን እናስባቸው
 ወንድሞቼ ዕለተ ሞታችሁን አስቡ እንደምትመጣባችሁም አስቧት ሰፊ መንግስቱ የክርስቶስም መምጫ ጊዜ ቀርባለችና ። ክብር ሃብትም ሃላፊ ነው። ቀጭን ልብስም የሚያረጅ ነው። ሰንበትን በእውነት አክብሩ ወንድሞቼ ስጡ አበድሩ ትልና ነቀዝ የማያበላሸውን ሌባም የማይሰርቀውን ሰማያዊ ሀብትን አከማቹ ፡፡” እንግዲህ እዚህ ላይ ምን እንጨምራለን ሞቱን የሚያስብ ብጹእ ነው ከማለት ውጪ፡፡ በሃብቱ ሳይሆን በእርሱ በአምላከ ሰንበት የሚመካ የታደለ ነው ከማለት ውጪ፡፡ በልብሱ ማማር የማይኮፈስ ሀብቱ ሰማያዊ ነው ከማለት ውጪ
 በመጨረሻ ጠቅለል አድርጎናሁ በጽሐ ጊዜ ሣህሉ ለእግዚአብሔር ጹሙ ወጸልዩ በንጹሕ ልብ እንዘ ታከብሩ ሰንበተ በጽድቅብሎ ያዜምልንና ወደሚቀጥለው ቀን ይሸኘናል፡፡እነሆ የእግዚአብሔር የይቅርታው ጊዜ ደርሷል ሰንበትን በእውነት ስታከብሩ በንጹህ ልብ ጹሙ ጸልዩም፡፡” አዎ ሰንበትን ካላይ እንዳልነው በንጽህና መልካም ሰርተን ምንቀደስባት ያድርግልን።
 ለእርሱ ልጅነት የማልበቃ ደካማ ስሆን የማይገባኝን ነገር ስለፃፍኩ ስለእኔ ፀልዩልኝ፡፡ አሜን በጾሙ ሰላምን ይስጠን ጾሙን በሰላም ያስፈጽመን አምላከ ቅዱስ ያሬድ ይጠብቀን፡፡

1 comment:

  1. ይሄን ጉድ ሰምታችሁዋል!!!!!!!!!!
    አሸናፊ መኮንን ግብረ ሰዶማዊ መሆኑን ታውቃላችሁ?
    በርካታ እሱን ሲከተሉ የነበሩ የመንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ሁሉ የሚያወሩት ግብረ ሰዶማዊ መሆኑን ነው። በዛ ላይ ውሸታም ሀሰተኛ ነቢይ እና ገንዘብ አፍቃሪ ነው። እድሜውን ሙሉ ሙዳይ ሙጽዋት አቅፎ የሚኖር ሰው ነው። ሰው መስሎን እሱ ጋር ስንመላለስ ሁሌ የሚገርመን ለሙዳይ ሙጽዋት ያለው ፍቅር ነው ከቢሮው ለአፍታም አይለያትም። ከሱ በቀር ማንም አይቆጥራትም። የእግዚአብሔርን ገንዘብ እየበዘበዘ ለግል ጥቅሙ የሚያውል ጀግና ነው። በአንድ አመት ውስጥ ብቻ ሌላ ምንም ተጨማሪ ገቢ ሳይኖረው ራቫ 4 መኪና ገዝቷል ሱቅ ከፍቷል። ይቅርታ የሚል መጽሀፍ ለስሙ ጽፏል ነገር ግን በምድር ላይ እሱን የሚወዳደር ቂመኛ የለም።
    አታግቡ የሁል ጊዜ ምክሩ ነው። ምነው ቢሉ ለሱ እንዲመቸው ነዋ።
    በእግዚአብሔር ስራ ውስጥ የስጋ ጥቅሙን የሚያሳድድ ሸፍጠኛ ግለሰብ አያስፈልግም።
    በዛ ላይ ያለበት የእውቀት ችግር በግልጽ የሚታይ ነው። ሊቅ መስሎን ለተጠጋነው የመንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች የህጻን ትምህርት አስተማረን። ከዛ ቢያንስ የሚናገረው ትንሽ እውቀት እንዲኖረው በተለያየ መንገድ ኮሎጅ ገብቶ እንዲማር ለማድረግ ሞከርን መቸ ሰምቶ እራሱን ሊቀ ሊቃውንት አድርጎ ያስቀመጠ ጀግና ነው።
    አሁን ደግሞ እንደ ጳጳስ ያደርገዋል አሉ።
    በእውነት ብትቀርቡ እና ሕይወቱን ብትመረምሩ እንዲህ ያለ ግለሰብ እንዴት የኛን አገልግሎት ተቀላቀለ? ትላላችሁ። አሳዛኝአሳፋሪ እና አቅሙን የማያውቅ ግለሰብ ነው። እኔ እማዝነው ለበርካታ የዋህና ጨዋ ተከታዮቹ ነው።
    የተሃድሶ ነገር ያሳዝናል

    ReplyDelete