Pages

Friday, March 14, 2014

ምኩራብ ዘቀዳሚት ሰንበት



በዲ/ን ስመኘው ጌትዬ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ መጋቢት 5 ቀን፣ 2006 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

 ሰማይን እንደ ድንኳን በዘረጋው፣ ምድርን በውኆች ላይ ባጸናት፣ ፀሐይንም መላእክትንም በሚመግባቸው፣ ከዋክብትንም እየመራ በነፋስ ሰረገላ በሚያመላልሰው፣ የወንጌልን ወተት ከኦሪት ወለላ ጋር ባጣፈጠ፣ የነቢያት ትንቢት ሽቶንም ከሐዋርያት የሃይማኖት ዘይት ጋር ባዋሐደ፣ በእግዚአብሔር ስም ሰላም ይሁንላችሁ:: (መጽሐፈ ምሥጢር)


  ገሰፀ ባሕረ ወነፋሳተ ወኲሉ ፍጥረት ያከብርዋ ለሰንበት በኃይለ መስቀሉ አጋንንተ አውጽአባሕርን እና ነፋሳትን ገሠጸ፡፡ ፍጥረት ሁሉ ሰንበትን ያከብሯታል፡፡ በመስቀሉ ኃይል አጋንንትን አወጣ፡፡ ለምፃምን አነፃ፡፡ ድውያንን ፈወሰ፡፡ ተዐምርን አደረገ፡፡ የዕውራንን ዐይን አበራ፡፡ ሁሉን ጨርሶ በሰንበት አረፈብሎ የቀዳሚት ሰንበት ድርሰቱን ከኃጢአት እንጂ ከምስጋና ፈጽሞ እረፍት የለም እያለ እያዜመ ይጀምርልናል::

 የቀደመችውን ሰንበትፍጥረታትን ከመፍጠር አረፈ” ቢባልለትም በሐዲስ ደግሞ መልካሙን ሁሉ እየፈጸመ የቀደመችውን ሰንበት ይበልጥ በተገለጠ በእጁ ስራ አከበራት:: “ውእቱ ቀደሰ ሰንበታተእርሱ ሰንበታትን ቀደሰ(አከበረ)፡፡ በመስቀሉ ገነትን ከፈተ፡፡ ለእረፍት ሰንበትን ሠራ፡፡ በመስቀሉ አጋንንት ተሰደዱ::”

 የቀደመው አዳም ከገነት በእንጨት ቢሰደድም ስደቱን የወደደ ጠላቱ ደግሞ በእንጨት ስደት ሆነበት፡፡ የማያርፈው አምላክ ማረፍን ባስተማረባት በቀዳሚዋ ሰንበት የሥጋና የነፍስ ነፃነት ተሰበከባት፡፡ ተፈጸመባት፡፡ በዚህች ቀን የገነት መከፈት ምልክት ታየባት፡፡ እኛንም የእርሷ ጌታ አደረገን::

 እስመ ውእቱ ኖኅሃ ሐደፈእርሱ ኖኅን አስተምሯል፡፡ አብርሃምንም መርቷል፡፡ ከያዕቆብ ጋር ተሰዷል፡፡ በእንጨት መስቀል ተሠቀለ፡፡ የሰንበት ጌታዋ ይቅር በለን:: የሰንበትን ቀን ቀደሳት፤ አከበራትም ወልድ በመስቀሉ ገነትን ከፈተ::” ይድን ዘንድ የመረጠውን ኖኅን በእንጨት መርከብ ከመጣው መዓት ሰወረው:: ጥፋቱም ማለፉን በእርግብ ዘንድ በእንጨት መምጣት ብስራት ሆነለት:: ልጅነትን ፈልጎ ስለተሠደደው ያዕቆብም ዝም አላለም፡፡ በሁሉ ስደቱን ባረከለት:: በእንጨት እርግማናችንን ያለፈውን ሊመጣ ያለውን ሁሉ ተሸክሞ ከእኛ ሸክማችንን በመስቀሉ አስወገደልን:: እንጨት ተበልቶባት የከዳችንን ገነት በተተከለ እና የድኅነት ፍሬን ባፈራች የእንጨት መስቀል አስታረቀን:: እንደ ቀዳማይ አዳም በእንጨት አጠገብ ሕግን በመጣስ ሳይሆን ሕግን በእንጨት ላይ በመፈጸም ትሕትናን አሣየን:: በመስቀሉ ኃይል ሰላምን አሣየን ወደ ሰላም መራን:: ሰላሙን ያድለን:: አሜን!

No comments:

Post a Comment