Pages

Friday, June 20, 2014

“መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል” 1 ጢሞ. 6፣16



በቀሲስ ጥላሁን ታደሰ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሰኔ 13 ቀን፣ 2006 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለመንፈስ ልጁ ጢሞቴዎስ በላከለት የመጀመሪያው መልእክት ማጠቃለያ ላይ የምናገኘው ኃይለ ቃል ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስይህንን መልእክት ከአቴና በደቀ መዝሙሩ በቲቶ በኩል ልኮለታል፡፡ ይሄንን የመጀመሪያ መልእክት ቅዱስ ጳውሎስ ወደ መቄዶንያ በሔደጊዜ፤ ደቀ መዝሙሩ ጢሞቴዎስን በሃገረ ኤፌሶን ትቶት ሔዶ ነበር፡፡ በዚያ ቆይታው ስለ መንፈሳዊ አገልግሎቱና /እርሱም/ በመንፈሳዊሕይወቱ ሊፈጽማቸው ስለሚገቡ ጉዳዮች ሊያስረዳው ጽፎለታል፡፡


ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በዚሁ መልእክቱ ላይ /ለደቀመዝሙሩ/ ለጢሞቴዎስ በመንፈሳዊ ተጋድሎ ውስጥ ካሉት ለክህነት ማዕረግ መመረጥ የሚገባቸው በኑሮዋቸው ምን መምሰል እንደሚገባቸው፣ ከባልቴቶች ሴቶች ጋር ሊኖሩ ወይም ሊለያዩ የሚገባቸው እንዴት እንደሆነ አስረድቶታል ሌላውበዚህ የመጀመሪያ መልእክቱ ላይ ያካተተው ፍሬ ነገር ደቀ መዝሙሩ ጢሞቴዎስ በሥራው፣ በአነጋገሩ ለምእመናን በጐ ምሳሌ እንዲሆናቸው፣ጉልምስና ከሚያመጣው ፍትወት በመራቅ በሥራው ሁሉ ራሱን ለጽድቅ እንዲያስገዛ የመከረው ምክር ነው፡፡

የመንፈሳዊውን ተጋድሎ ጥቅም እና ጣዕም በመረዳት ልጁ ጢሞቴዎስ መልካሙን የእምነት ገድል እንዲፈጽም የራሱን የተጋድሎ ሕይወት ግልጽ በማድረግምመክሮታል፡፡መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ፤ ሩጫዬንም ጨርሻለሁ፤ ሃይማኖቴን ጠብቄያለሁ፡፡ ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል…” እንዲል /2ጢሞ. 47-9/፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ተጋድሎ የክርስቲያኖችን ሕይወት ለታላቅ ክብር የሚያበቃ መሆኑን ለጢሞቴዎስ ብቻ ሳይሆን፤ ለቆሮንቶስ ምእመናንምበምሳሌ ባስረዳቸው ትምህርት ላይ እናገኛለን፡፡በእሽቅድምድም ሥፍራ የሚሮጡት ሁሉ እንዲሮጡ፤ ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋውን እንዲቀበልአታውቁምን? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ /ተጋደሉ/፡፡ የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል፡፡ እነዚያም የሚጠፋውን አክሊልሊያገኙ ነው፤ እኛ ግን የማይጠፋውን፡፡ ስለዚህ እኔ ያለ አሳብ እንደሚሮጥ ሁሉ እንዲሁ አልሮጥም፤ ነፋስን እንደሚጐስም ሁሉ እንዲሁአልጋደልም፤ ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጐሰምሁ አስገዛዋለሁ፡፡” /1ቆሮ. 924-27፡፡ስለሆነም ክርስቲያናዊ ሕይወት ረድኤተ እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ በሚፈጸም መንፈሳዊ ተጋድሎ መንፈሳዊ ፍሬ የምናፈራበት ነው፡፡ከወገናችንም ያሉት ደግሞ ፍሬ ቢሶች ሆነው እንዳይቀሩ የግድ ስለሚያስፈልገው ነገር በመልካም ሥራ እንዲጸኑ ይማሩበማለት እንደመከረውበመንፈሳዊ ሕይወት ፍሬያማ ለመሆን መልካሙን የእምነት ተጋድሎ መፈጸም ይገባል /ቲቶ. 314/፡፡

መንፈሳዊ ተጋድሎ ምንድን ነው?
ተጋድሎ ማለት አንድ ሰው የሚያምንበትን እምነት፣ የሚመራበትን ሕግ፣ የሚያልመውን ተስፋ ተከትሎ ከግቡ ለማድረስ ማድረግ የሚገባውን በማድረግ፣የማይገባውን ባለማድረግ በነጻ ፈቃዱ ወስኖ በሙሉ ልቦናው እና በሙሉ ኃይሉ የሚያደርገው የውስጥ እና የውጭ ጥረት ነው፡፡ የተጋድሎመነሻው በሕይወት የሚገጥሙ ልዩ ልዩ ፈተናዎች፣ ለነፍስም ለሥጋም የሚበጀውን መልካም ነገር የሚቃረኑ የክፋት ኃይሎች እና የመሳሰሉትነገሮች ናቸው፡፡ ሰው እነዚህን ነገሮች ለማሸነፍ ሰላማዊ ሕይወት ለመምራት የሚከፍለው መሥዋዕትነት፣ የሚያደርገው የሃይማኖት ሩጫ፣የሚታገለው ትግል መንፈሳዊ ተጋድሎ ይባላል፡፡
ክርስቲያን ደግሞ፤ ተጋድሎን በጽናት መፈጸም ይጠበቅበታል፡፡ ምክንያቱም ጊዜያዊ ያይደለ ዘለዓለማዊ፣ ምድራዊ ያይደለ ሰማያዊ፣ ለክብር አክሊል፣መንግሥተ እግዚአብሔርን ለመውረስ፣ የሚያበቃ የእምነት ተጋድሎ ነው፡፡ ያለ ትግል ድል ያለ ድል ደግሞ አክሊል የለም፡፡ ዓለምንድል ለማድረግ ረድኤተ እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ መልካሙን የእምነት ገድል ለመፈጸም ይገባል፡፡በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ…” እንዲል /ዮሐ. 1633/፡፡ ስለ ሃይማኖት የሚደርስብንን መከራ በመታገስ ድል ለማድረግእኔ ድል እንደነሣሁ ከአባቴም ጋር በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጥሁ፤ ድል ለነሣው ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ ዘንድ እሰጠዋለሁ፡፡የሚለውን ቃልኪዳን ለመጠቀም የእምነት ገድል ለሁሉም ክርስቲያኖች ያስፈልጋል /ዮሐ. 1613 ራእ. 321/፡፡

የክርስቲያኖች ተጋድሎ መንፈሳዊ ተጋድሎ ነው፡፡ የልዑል እግዚአብሔር ማደሪያ በመሆን መንፈሳቸው ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ኅብረት እና አንድነት ኖሮት፤ረድኤተ እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ የሚያካሂዱት ተጋድሎ የሚያደርጉት መንፈሳዊ እንቅስቃሴና ተግባር ነው፡፡ ክርስቲያናዊ ተጋድሎለብቻ የሚደረግ ሥጋዊ ሩጫ ሳይሆን እግዚአብሔርንና የቅዱሳንን ጸሎት አጋዥ በማድረግ የሚፈጸም ነወ፡፡ ስለሆነም አቤቱ ንጹሕ ልብንፍጠርልኝ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ፡፡ ከፊትህ አትጣለኝ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ አትውሰድብኝበማለት ዘወትር መጸለይይገባል /መዝ. 50 10-11/፡፡
መንፈሳዊ ተጋድሎ መልካም የሆነውን የመንፈስ ፍሬ ፍቅርን፣ ደስታን ሰላምን ትዕግስትን፣ ቸርነትን፣ በጐነትን፣ እምነትን፣ ራስን መግዛትንበማፍራት ለመንግሥተ እግዚአብሔር የምንዘጋጅበት ነው /ገላ. 522-23/፡፡

መንፈሳዊ ተጋድሎ ለምን?
መንፈሳዊ ተጋድሎን ገንዘብ ስናደርግ ቅዱስ ጳውሎስእኔ ያለ አሳብ እንደሚሮጥ ሁሉ እንደዚሁ አልሮጥም፡፡ ነፋስም እንደሚጐስም ሁሉ እንደዚሁአልጋደልምእንዲል እኛም፤ ለምን በመንፈሳዊ ተጋድሎ እንደምንጋደል ማወቅ እና መረዳት ይገባናል /1ቆሮ. 926/፡፡ መንፈሳዊተጋድሎን ስንፈጽም መጾማችን፣ መጸለያችን፣ መስገዳችን፣ መመጽወታችን፣ ንስሐ መግባታችን፣ የምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ተካፋይ መሆናችን፣ማገልግላችን ሳናውቀው ሳንረዳው ከሆነ የመንፈሳዊ ተጋድሎ መገለጫዎች ሁሉ እንዲሁ ከንቱ ድካም ይሆንብናል፡፡
መንፈሳዊ ተጋድሎን በእውነት፣ በመረዳት፣ በዓላማ ሲፈጸሙ ዋጋ ያሰጣሉ፡፡ እነርሱም ለሥጋም፣ ለነፍስም ሰማያዊ በረከት የሚያስገኙ ናቸው፡፡ጥቂቶቹ፡-

1. ኃጢአትን እና ዲያብሎስን ድል ለማድረግ
ኃጢአት ማለት ሰህተት፣ ክፍት፣ ሕግን መተላለፍ፣ ዐመፃ፣ በጐ ማድረግን አውቆ አለመሥራት፣ በእምነት መሠረት ላዳ አለመኖር፣ በአጠቃላይከፈቃደ እግዚአብሔር ውጭ መሆን ተብሎ ይተረጐማል፡፡ ኃጢአት ሰውን ከክብር የሚያዋርድ፣ ከጸጋ እግዚአብሔር የሚያርቅ፣ በፍርሐትውስጥ የሚጥል፣ ተቅበዝባዥ የሚያደርግ፣ ሰውን በባርነት የሚይዝና ከመንግሥተ እግዚአብሔር የሚለይ የሰው ልጆች ጠላት ነው፡፡

ኃጢአት የሞት መንገድ ቀያሽ በመሆኑ በአምላካችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ለሰው የተሰጠውን ነጻነት የሚያሳጣ ሰውን በባርነትየሚይዝ ነው፡፡ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስኃጢአትን የሚያደርግ ሁሉ የኃጢአት ባሪያ ነው፤ ባሪያም ለዘለዓለም በቤትአይኖርምበማለት እንዳስተማረው /ዮሐ. 834/፡፡

መንፈሳዊ ተጋድሎ ከዚህ ባርነት ነጻ ለመውጣት እና በነጻነት ለመኖር፣ ሰላማዊ ሕይወትን ለመምራት፣ በእምነት መሠረት ላይ ለመኖር፣ ከዐመፅ፣ከክፋት፣ ከስህተት ለመጠበቅ የበጐ ሥራ ተባባሪ ለመሆንና በፈቃደ እግዚአብሔር ለመኖር የምንችልበትን መንፈሳዊ ኃይል የምናገኝበትየእምነት መሣሪያ ነው፡፡ መንፈሳዊ ተጋድሎ ሐዋርያት በትምህርታቸውወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ /ተጋድሎ/ እንገባዘንድ ያስፈልገናልበማለት እንዳስተማሩት የማታልፈውን ዘለዓለማዊት መንግሥት፤ መንግሥተ ሰማያትን ለመውረስ የሚያስችለን መንገድነው /ሐዋ. 1422/፡፡

ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገዳመ ቆረንቶስ በጾም፣ በጸሎት፣ በትሕርምት ሆኖ ሦስቱን አርእስተ ኃጣውእ ማለትም ስስትን በትዕግሥት፤ትዕቢትን በትኅትና፤ ፍቅረ ንዋይን በጸሊኦ ንዋይ ድል እንደነሣ እኛም በመንፈሳዊ ተጋድሎ በመጽናት እና ረድኤተ እግዚአብሔርና የቅዱሳንንምልጃ አጋዥ በማድረግ ዐበይት እና ንዑሳን ኃጣውእን ድል ለማድረግ መትጋት ይገባናል፡፡ ማር ይስሐቅ በእነዚህ ኃጢአቶች እንዳትያዝበሥራህ /በተጋድሎህ/ ሁሉ ልል ዘሊል አትሁንበማለት ይመክረናል፡ /ማር ይስሐቅ ምዕ.4/፡፡ ስለሆነም በመንፈሳዊ ተጋድሎ በመኖርበነፍሳችሁ ዝላችሁ እንዳትደክሙ ከኃጢአት ጋር ተጋደሉበማለት ሐዋርያው እንዳስተማረን ልንኖር ይገባል፡፡ /ዕብ. 123/፡፡

መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ሥፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያንሠራዊት ጋር ነው እንጂበማለት ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ለኤፌሶን ምእመናን እንዳስተማረው በመንፈሳዊ ተጋድሎ መጽናት ዲያብሎስን እና ሠራዊቱን ድል ለማድረግ እና ከአሸናፊዎቹ ቅዱሳን ጋር ለመደመር ያበቃል፡፡ /ኤፌ. 712/፡፡የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ፡፡በማለትም እንደመከረን ዘወትር መንፈሳዊ ኃይል የምናገኝበትን ሕግጋተእግዚአብሔርና ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንን በመፈጸም መልካሙን የእምነት ገድል ሕይወታችን ልናደርገው ይገባል /ኤፌ. 611/፡፡ ሊቀሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስም በመጀሪያዪቱ መልእክቱበመጠን ኑሩ፤ ንቁም፣ ባለጋራችሁ ደያብሎስ የሚውጠውን ፈልጐ እንደሚያገሳ አንበሳይዞራልና በዓለም ያሉት መንድሞቻችሁ ያን በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት፡፡” /1ጴጥ. 58-9/ በማለትእንዳስተማረን በክርስትና ሕይወት ስንኖር ዘወትር የሰው ልጆችን ከክብር ለማውረድ የማይደክመውን ጠላት ዲያብሎስን የምንቃወምበትእና በእግዚአብሔር ልጅነታችን የምንጸናበትን መንፈሳዊ ተጋድሎ ገንዘብ በማድረግ ልንጸና ይገባል፡፡

መንፈሳዊ ተጋድሎ ለልዑል እግዚአብሔር በፍጹም ሕይወታችን የመገዛታችን እና ዲያብሎስን የመቃወማችን መገለጫ ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብበመልእክቱእንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙት ከእናንተም ይሸሻል ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባልበማለት እንደመከረን፤ ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበትን እና ለእግዚአብሔር የምንገዛበትን መንፈሳዊ ተጋድሎ ልንይዝ ይገባናል /ያዕ.47 መዝ. 7228/፡፡

እንግዲህ በዓለም ሳለን ከዲያብሎስ እና ከሠራዊቱ የሚመጣብንን ልዩ ልዩ መከራ /ፈተና/ እና ከሥጋ ፈቃዳችን በሚመነጩ ክፉ ምኞት እንዲሁምከሌሎች የፈተና ዓይነቶች ለመጠበቅ እና ድል ለማድረግ መልካሙን የእምነት ገድል መጋደል ያስፈልጋል፡፡እንግዲህ ወገባሀችሁን በእውነትታጥቃችሁ የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ በሰላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ፡፡ በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትንየክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነት ጋሻ አንሡ የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔርቃል ነው፡፡” /ኤፌ. 614-17/፡፡

2. ጸጋ እግዚአብሔርን ለማግኘት
ጸጋ ማለት እግዚአብሔር ለልጆቹ በነጻ የሚያድላቸው ሰጦታ ማለት ነው፡፡ ይኸውም የሚገኘው በመንፈሳዊ ተጋድሎ ነው፡፡እኛም በክርስቶስፍጹም የምንሆን ሰውን ሁሉ እናቀርብ ዘንድ ሰውን ሁሉ እየገሠጽን፣ ሰውንም ሁሉ በጥበብ ሁሉ እያስተማርን የምንሰብከው እርሱን ነው፡፡ለዚህም ነገር ደግሞ በእኔ በኃይል እንድሚሠራ እንደአሠራሩ እየተጋደልሁ እደክማለሁ፡፡በማለት በመንፈሳዊ ተጋድሎ መኖር እንደሚገባሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ አስተምሯል፡፡ /ቆላ. 128-29/፡፡

የክርስትና ሕይወት ራስን ለእግዚአብሔር በመስጠት፤ እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ የሚኖሩበት፣ የሚጸኑበት እንጂ፤ በራስ ኃይል እና ጥበብ የሚኖሩበትሕይወት አይደለም፡፡ በመሆኑም ይሄንን የጸጋ ስጦታ ለማግኘት ሰው በክርስትናው ዓለም የአቅሙን መትጋት ይጠበቅበታል፡፡ ልበ አምላክቅዱስ ዳዊትእግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ ሠራተኛ በከንቱ ይደክማል፤ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ ጠባቂዎች በከንቱ ይደክማሉ፡፡በማለት እንዳስተማረው ድካማችን ከንቱ ድካም እንዳይሆን በእግዚአብሔር ቸርነት እንደምንድን አውቀን በአቅማችን በመትጋት መንፈሳዊነትንመላበስና በመንፈሳዊ ተጋድሎ አለመመረር ይገባል፡፡
መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል በማለት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳስተማረ ለነቢያት፣ ለሐዋርያት፣ ለአበው ቅዱሳን እና ለቅዱሳት እናቶቻችንየተሰጠውን የእግዚአብሔር ጸጋ ለማግኘትና ዲያብሎስን ድል ለማድረግ በጾም፣ በጸሎት፣ በንስሐ፣ በአገልግሎት በአጠቃላይ ፈቃደ እግዚአብሔርየሆነውን ሁሉ በመፈጸም መልካሙን የእምነት ገድል ፈጽመን የመንግሥቱ ወራሽ ለመሆን ራስን ማዘጋጀት ይገባል፡፡ ለዚህም የእግዚአብሔርቸርነት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን ጸሎት፣ ረድኤት አይለየን፡፡ አሜን፡፡                   
© ይህ ጽሑፍ በሐመር መጽሔት ላይ የወጣ ነው

No comments:

Post a Comment