Pages

Wednesday, July 9, 2014

ለመቅረዝ ዘተዋሕዶ ድረ ገጽ ወዳጆች

(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሐምሌ ፪ ቀን፣ ፳፻፮ ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!



መቅረዝ ዘተዋሕዶ መንፈሳዊት ድረ ገጽ አድራሻ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህሕዶን እምነት ሥርዓት ትውፊትና ታሪክ መሠረት ያደረጉ ትምህርታዊ የኾኑ ጽሑፎች በአራት በተለያዩ ቋንቋዎች ላለፉት ዓመታት ወጥተዋል፡፡ እነዚኽ ትምህርቶች በሀገር ውስጥም ኾነ ከሀገር ውጪ የኢንተርኔት አቅርቦት ላላቸው ምዕመናን በተቻለ መጠን ለማድረስ ተሞክሯል፡፡ ነገር ግን እነዚኽን መንፈሳውያን ጽሑፎች በዓቅም ማነስ ምክንያት ቴክኖሎጂውን መጠቀም ላልቻሉ  ምዕመናን ሊዳረሱ አልቻሉም፡፡


አንባብያንም በተለያየ ጊዜኧረ የመጽሐፍ ያለኽሲሉ በተደጋጋሚ ጠይቀዉኛል፡፡ በተለያየ ጊዜ እነዚኽን ጽሑፎች ወደ ምዕመናን ለማድረስ የዓቅሜን ያኽል መንገዶችን ሳፈላልግ ቆይቻለኹ፡፡ ነገር  ግን  በተለያዩ ምክንያቶች እስከ አኹን ሊሳካልኝ አልቻለም፡፡
በመኾኑም ይኽን በጐ ሐሳብ የሚደግፉ  ለፍልሰታ ማርያም የመዠመሪያውን መጽሐፍ  ለማሳተም  በዝግጅት ላይ ስለምገኝ መጽሐፉ ምዕመን ዘንድ ተደራሽ ለማድረግ ያስችለኝ ዘንድ ለሕትመቱ መሳካት እርስዎ የዓቅሞትን ያኽል ስፖንሰር  በማድረግ  ክርስቲያናዊ ግዴታዎን ከመወጣት በተጨማሪ ከበረከቱ  ተካፋይ  ይኾኑ  ዘንድ በእግዚአብሔር ስም እጠይቅዎታለኁ፡፡

ተጨማሪ መረጃ የሚፈልጉ ከኾነ በዚኽ አድራሻ ማግኝት ይቻላል፡- 

ስልክ + 251 912 074 575
የባንክ ሒሳብ ቍጥር፡-  የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  ተክለ ሃይማኖት ቅርንጫፍ01730 6992 4500

 




“ፍቅራችኊ ያለ ግብዝነት ይኹን፡፡ ክፉውን ነገር ተጸየፉት፤ ከበጐ ነገር ጋር ተባበሩ፡፡” /ሮሜ.፲፪፡፱/፡፡

No comments:

Post a Comment