Pages

Friday, September 19, 2014

"እርግና"



በዲ/ን ዶ/ር ቴዎድሮስ በለጠ


(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ መስከረም 9 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

የእድሜ ጅራፍ ግርፋቱ = ከግንባሬ
የክብር ሸማ ሽበቱ = ከጠጉሬ
የአዝማናት ፍኖት ንቃቃት = ተረከዜ
የምድር ሩጫ ሥጦታ = "ደም- ወዜ"
ለቁጥር መሳፍርት = ብልጥግና
ዳግም ለንሰሃ ............ ዳግም ለምስጋና
ጊዜ ለእርጋታ..... ጊዜ ለጥሙና
ፍፃሜ መዋዕል ......... ድህረ ውርዝውና

"እርግና"
አቤቱ አምላኬ .......የጽድቅ መኮንን
በሰጠኸኝ ጊዜ በንሰሃ ዘመን
የሥጋ ፈቃዴ ኃጢዓቴ እንዳይመዝን
ከጸጋህ ተራቁታ በነፍሴ እንዳላዝን
ጠዋት...... ቀንም....... ማታ
ድምጽህን ሰምቼ ከማርፍበት ቦታ…………..
ከምህረት ሰገነት ከመቅደስህ ደጃፍ
ከመስቀልህ በታች ከመንግስትህ በራፍ
ትሁን ፍጻሜዬ የእርግናዬ ምዕራፍ !!!
+++
አሜን +++


1 comment:

  1. ቃለ ሕይወት ያሰማልን። "እርግና /እርጅና ብቻህን ና ጓዞችህ ብዙ ናቸውና" ይባል የለ። በእርግናቸው ላሉ ተጨማሪ ጠሎት ሆነላቸው። ለኛም ትምህርት። በእርጅና ዘመናቸው የመጠጥ ቤትን ያጣበቡት አረጋውያን ወደ ንስሐ ደጅ የሚገቡበት። የመሰንቆውን አሽሙር እና የአዝማሪውን አሽሙር ትተው የካህናቱን ዝማሬ የዕጣኑን ሽታ የወንጌልን ማዕድ የሚቋደሱበት ያድርግልን።

    ReplyDelete