Pages

Wednesday, August 26, 2015

ትምህርተ ሃይማኖት - ክፍለ ዐሥራ አራት



(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ነሐሴ 21 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
የሰኞ (ሠኞ) ፍጥረት
ሰኞ የሚለው ቃል “ሰነየ - ሰኑይ” ከሚል የግእዝ ቃል የተገኘ ሲኾን፥ ትርጓሜውም መሰነይ፣ ኹለት ማድረግ፣ ኹለተኛ ዕለት ማለት ነው፤ ሥነ ፍጥረትን ለመፍጠር ኹለተኛ ቀን ነውና፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ፥ ሠኑይ ማለት ሠነየ፣ ሠናይ፣ አማረ፣ ተዋበ፣ በጌጥ በመልክ ደስ አሰኘ ማለት ነው፤ ይኸውም በዚህ ዕለት ብርሃን ስለ ተፈጠረ ነው፡፡
      ለሰኞ አጥቢያ በጊዜ ሠርክ (የመጀመሪያው ሰዓተ ሌሊት) እግዚአብሔር በዕለተ እሑድ “ብዢ ተባዢ፤ ስፊ ተስፋፊ” ብሏት የነበረችው ውኃ ከምድር ጀምራ እስከ ኤረር ድረስ መልታ ነበር፡፡ በዚሁ ዕለት ማለትም በዕለተ ሰኑይም፥ ጠፈርን ፈጠረ /ዘፍ.1፡6-9/፡፡ እግዚአብሔር ጠፈርን በፈጠረ ጊዜም በዓለም መልቶ የነበረው ውኃ በአራት ተከፍሏል፡-
ü  የምናየው ሰማይ (ጠፈር) (ሥዕለ ማይ)፣
ü  ከጠፈር በላይ የተሰቀለው ሐኖስ፣
ü  ለምድር ምንጣፍ የኾነ ውኃና፣
ü  በምድር ዙርያ እንደ መቀነት የተጠመጠመው ውኃ (ውቅያኖስ) ተብሎ፡፡ በምድር ላይ የምናያቸው ውኆች በምድር ዙርያ ከተጠመጠመው ከዚህ ውቅያኖስ የቀሩ እንጥፍጣፊ ናቸው፡፡

Tuesday, August 18, 2015

መንፈሳዊ አገልግሎት



በዲ/ን ሕሊና በለጠ ዘኆኅተብርሃን
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ነሐሴ 12 ቀን 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
አገልግሎት የሚለው ቃል ገልገለ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ እንደሆነ ይጠቁማል፡፡ ገልገለ (አገለገለ) ማለት ተገዛ፣ ታዘዘ፣ ዐገዘ፣ ረዳ፣ ጠቀመ፣ ማንኛውንም ሥራ ሠርቶ ጌታውን  ደስ አሰኘ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ አገልግሎት ማለት መታዘዝ፣ መገዛት፣ መርዳት፣ መጥቀም…ማለት ይሆናል፡፡  ማንኛውም ሥጋዊና መንፈሳዊ ሥራ አገልግሎት ነው፡፡ ለመንግሥት የሚሠራ የመንግሥት አገልጋይ፣ ለግለሰብ የሚሠራ የግለሰብ አገልጋይ፣ ለእግዚአብሔርም የሚሠራ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ አገልጋዮችን በተለያየ ስያሜ ጠርቷል፡፡ ምንም አይነት መብት በራሱ ላይ የሌለውንና በጌታው ሐሳብ ፍፁም አዳሪ የሆነውን ተገዢ ባሪያ በማለት ገልፆታል፡፡ ንዋይ ኅሩይ ቅዱስ ጳውሎስ ‘ከሰው ሁሉ አርነት የወጣሁ ስሆን የሚበልጡትን እንድጠቅም እንደባሪያ ራሴን ለሁሉ አስገዛለሁ’ በማለት የተናረው ይህን ያጠናክራል፡፡ (1ቆሮ. 9÷19) አብሮት የሚያገለግለውን ቲኪቆስንም  ‘በጌታም አብሮኝ ባሪያ የሆነ’ በማለት ጠርቶታል፡፡ (ቁላ 4፡7) ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስም አርነት ወጥታችሁ እንደ እግዚአብሔር ቅዱሳን ባሪያዎች ሁኑ በማለት አገልግሎታችን በፍፁም መገዛት እንዲሆን ይመክረናል፡፡ (1ጴጥ. 2‘፡16) በራሱ ላይ ሙሉ ነፃነት ያለውን አገልጋይ መጽሐፍ ቅዱስ ሠራተኛ ይለዋል፡፡ (ሉቃ 10፡2፣ ቁላ 4፡11፣ 2ጴጥ 1፡8) ይህ ከባሪያ ይልቅ በራሱ ላይ የመወሰን ሥልጣን ያለው ነው፡፡ ከፈለገ አለማገልገል ይችላል፡፡ በባሪያና በሠራተኛ መካከል ነፃነቱ መካከለኛ የሆነው ደግሞ ብላቴና፣ ሎሌ ተብሎ የተጠራው ነው፡፡

Saturday, August 15, 2015

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የእሑድ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የእሑድ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ: ገ/እግዚአብሔር ኪደ (መቅረዝ ዘተዋሕዶ ነሐሴ ፲፪ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም.)፡-  በዚህ ዕለት እመቤታችን ከወትሮው ይልቅ ቀደም ብላ መጥታለች፡፡ “ዛቲ ዕለት ተዓቢ እምኩሎን ዕለታት፤ ወውዳሲያቲሃኒ የዓብያ እምኵሉ ውዳሴያት...

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የቅዳሜ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የቅዳሜ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ: ገ/እግዚአብሔር ኪደ (መቅረዝ ዘተዋሕዶ ነሐሴ ፲፩ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም.)፡- በዚህም ቀን እመቤታችን ትመጣለች፤ የብርሃን ድባብ ይዘረጋል፤ የብርሃን ዙፋን ይነጠፋል፡፡ ከዚያ ላይ ኹናም ሊቁን ባርካው ምስጋናዉን ጀምሯል...

Friday, August 14, 2015

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የዓርብ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የዓርብ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ: ገ/እግዚአብሔር ኪደ (መቅረዝ ዘተዋሕዶ ነሐሴ ፲ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም)፡- ይህ ዕለት ለምስጋና አምስተኛ ለፍጥረት ስድስተኛ ቀን ነው፡፡ በዚህም ቀን እመቤታችን ትመጣለች፤ የብርሃን ድባብ ይዘረጋል፤ የብርሃን ዙፋን ይነ...

Wednesday, August 12, 2015

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የሐሙስ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የሐሙስ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ: ገ/እግዚአብሔር ኪደ (መቅረዝ ዘተዋሕዶ ነሐሴ ፱ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም)፡- ይህ ዕለት ለምስጋና አራተኛ ለፍጥረት አምስተኛ ቀን ነው፡፡ በዚህም ቀን እመቤታችን ትመጣለች፤ የብርሃን ድባብ ይዘረጋል፤ የብርሃን ዙፋን ይነ...

Tuesday, August 11, 2015

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የረቡዕ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የረቡዕ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ: ገ/እግዚአብሔር ኪደ (መቅረዝ ዘተዋሕዶ ነሐሴ ፰ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም.)፡-  ለምስጋና ሦስተኛ፣ ለፍጥረት አራተኛ ቀን በሚኾን በዚህ ዕለት ከወትሮ ይልቅ መላእክትን አስከትላ እመቤታችን ትመጣለች፤ የብርሃን ድባብ ይዘረ...

Monday, August 10, 2015

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የማክሰኞ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የማክሰኞ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ: ገ/እግዚአብሔር ኪደ (መቅረዝ ዘተዋሕዶ ነሐሴ ፯ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም)፡- ለምስጋና ኹለተኛ፣ ለፍጥረት ሦስተኛ ቀን በሚኾን በዚህ ቀንም እመቤታችን ትመጣለች፤ የብርሃን ድባብ ይዘረጋል፤ የብርሃን ምንጻፍ ይነጸፋል፡፡ ከ...

Sunday, August 9, 2015

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የሰኞ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የሰኞ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ: ገ/እግዚአብሔር ኪደ (መቅረዝ ዘተዋሕዶ ነሐሴ ፭ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም.)፡- ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም እመቤታችን ከባረከችው በኋላ ምስጋናውን የጀመረው “ፈቀደ እግዚእ…” ብሎ ነው፡፡ ፩. በ መቅድመ ወንጌል “ ወ አልቦቱ ...

Friday, August 7, 2015

“ኹል ጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ” ፊልጵ.4፡4



(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ነሐሴ 1 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
      ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክታቱ ላይ ደጋግሞ ከሚናገራቸው ኃይለ ቃላት አንዱ ስለ ደስታ ነው፡፡ አራት ምዕራፍ ብቻ ባላት በፊልጵስዮስ መልእክት ብቻ እንኳን “ደስ ብሎኛል፤ ወደፊትም ደስ ይለኛል፤ ደስታዬን ፈጽሙልኝ፤ ደስ ይበላችሁ፤” እያለ ዐሥራ አምስት ጊዜ ተናግሯል፡፡
ለመኾኑ ምንድነው ይኼ ደስታ? አንድን ነገር (ለምሳሌ ልጅ፣ ሥራ፣…) ባገኘን ጊዜ ደስ እንደሚለን ያለ ደስታ ነውን? ወደ መዝናኛ ስፍራዎች በሔድን ጊዜ አፀዱን፣ አዕዋፉን፣ ፏፏቴዉን ባየን ጊዜ፣ ምግቡን በበላን፣ ወይም መጠጡን በጠጣን ጊዜ ደስ እንደሚለን ያለ ደስታ ነውን? አይደለም! እንዴት ነው ታዲያ?
በልብ መታሰቡ፣ በቅዱሳት መጻሕፍት መዘገቡ፣ በቃል መነገሩ ከፍ ከፍ ይበልና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፡- “እኔ የምሰጣችሁ ሰላም ዓለም እንደሚሰጣችሁ አይደለም” ብሎ እንደተናገረው /ዮሐ.14፡27/፥ ይህ ደስታም በዚህ ዓለም በምናገኛቸው ነገሮች ወይም በምንደርስባቸው ስኬቶች የሚገኝ አይደለም፤ ከእግዚአብሔር ብቻ የምናገኘው ደስታ ነው እንጂ፡፡ ይህም ደስታ በግሪኩ “ቻራ” ይሉታል፡፡ ይህም ማለት ቋሚ ከኾነው ከእግዚአብሔር የሚገኝና፡- ብናገኝም ብናጣም፣ ብንጠግብም ብንራብም፣ በተሳካልንም ባልተሳካልንም ጊዜ፣ ጤና ስንኾንም ስንታመምም፥ በአጠቃላይ በዚህ ዓለም በዙርያችን በሚለዋወጡ ኹኔታዎች አብሮ የማይለዋወጥ ነው፡፡

Wednesday, August 5, 2015

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የውዳሴ ማርያም ትርጓሜ- መግቢያ

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የውዳሴ ማርያም ትርጓሜ- መግቢያ: ገ/እግዚአብሔር ኪደ                                                                                    (መቅረዝ ዘተዋሕዶ ነሐሴ ፩ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም.)፡- ውዳሴ፡...

Monday, August 3, 2015

ሆስፒታልና ቤተ ክርስቲያን በንጽጽር ሲታዩ



በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሐምሌ 28 ቀን 2007 ዓ.ም.):- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
እግዚአብሔር የሚወዳችሁ አንድም እግዚአብሔርን የምትወዱት ልጆቼ! ተጠራርታችሁ ወደ አባታችሁ ቤት ለመምጣት ያደረጋችሁትን ቅንአት ተመልክቼ ደስ ተሰኝቼባችኋለሁ፡፡ እኔም ይህን ቅንአታችሁን አይቼ ስለ ነፍሳችሁ ጤና ይበልጥ እንዳስብ አድርጎኛል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ቀዶ ጥገና የሚደረግባት ሐኪም ቤት ናት፡፡ የሥጋ ቀዶ ጥገና ግን አይደለም፤ የነፍስ ቀዶ ጥገና ነው እንጂ፡፡ የምናክመው የሥጋን ቁስል አይደለም፤ መንፈሳዊ ቁስልን እንጂ፡፡ መድኃኒቱም ቃለ እግዚአብሔር ነው፡፡ ይህ መድኃኒት በምድር ላይ ከሚበቅሉት ዕፅዋት የተቀመመ አይደለም፤ ከሰማያት ከሚመጣው ቃል እንጂ፡፡ ይህን መድኃኒት በቁስል ላይ ለመጨመር ሐኪሞች አያስፈልጉም፤ የሰባክያነ ወንጌል አንደበት እንጂ፡፡ ቀዶ ጥገናውን ለማከናወን ብዙ ሰዓታትን አይፈጅም፡፡ ቀዶ ጥገናው ላይሳካ ይችላል ተብሎ የሚጠረጠር አይደለም፡፡ ከጊዜ በኋላ ወይም በሌላ ሕመም ምክንያት የተደረገው ቀዶ ጥገና ሊከሽፍ ይችላል ተብሎም አይገመትም፡፡ ሐኪሞች የሚሰጡን መድኃኒት እንዲህ ዓይነት ችግር ሊያጋጥመው ይችላል፡፡ ሐኪሞች የሚሰጡን መድኃኒተ ሥጋ ለጊዜው ብርቱ ነው፤ ሰውነታችን እያረጀ እንደሚሔደው ኹሉ መድኃኒቱም በጊዜ ሒደት ብርታቱን እያጣ ይሔዳል፡፡ ሌላ ደዌ ዘሥጋ ሲገጥመንም መቋቋም የሚችል አይደለም፡፡ ምክንያቱም መድኃኒቱን የቀመሙት ሰዎች ስለኾኑ፡፡ ከእግዚአብሔር የሚሰጠን መድኃኒት ግን እንደዚህ አይደለም፡፡ ምንም ያህል ጊዜ ቢቆይም አይበላሽም፤ ጊዜው አያልፍበትም፤ ኃይሉም ብርታቱም ያው ነው አይቀንስም፡፡