Pages
▼
Monday, June 18, 2018
መቅረዝ ዘተዋሕዶ : ነገረ መላእክት (Angelology)
መቅረዝ ዘተዋሕዶ : ነገረ መላእክት (Angelology): (መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ቅዳሜ ታኅሳስ 18 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!! ትርጕም ጥሬ ቃሉን ስንመለከተው መልአክ የሚለው የግእዝ ቃል ኹለት ትርጉሞች ...
Thursday, June 14, 2018
ሙስሊሞች በክርስቲያኖች ጉባኤ
በአማን ነጸረ እንደ ጻፈው
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሰኔ 07 ቀን፣
2010 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን!
ጥሎብኝ፣ ክርስቲያን ወንድሞቼ ስለ ቁራን በተቃርኖ ሲተረጉሙ መስማት ይጨንቀኛል፡፡ በራሴ ደርሶ ስላየሁት ይሆናል፡፡ የቤ/ክ ገድላትና ድርሳናት በማያምኑባቸው ሰዎች ሲተረጎሙ በአማኝ ዕዝነ ልቡና እያዳመጥኩ ብዙ ጊዜ ቅር ይለኛል፡፡ የባለቤትነትና የማንነት ስሜት በሌለህ እምነት ውስጥ ገብተህ ስትተረጉም እንደ ምዕመን ሳይሆን እንደ ፈላስፋ ሁሉን ነገር በአመክንዮ እየፈታህ ትገጥምና ጭርሱን እምነት የሚለውን ከአመክንዮ (ሎጂክ) በላይ የሆነ አስተሳሰብ ትዘነጋለህ፡፡ ያን ጊዜ መዘንጠል ይመጣል፡፡ ያለ አነባበቡ፣ ተነሺና ወዳቂ ሳይለይ የሚያነብ ሰው በድፍረት ንባቡን ሲሾፍረው ‹‹ኧረረረረረ ዘነጥልከው!›› ይላሉ የቤ/ክ አስነባቢዎች፡፡ ሰው የማያምነበትን ሲተረጉም ደግሞ ዝንጠላ የማያመልጠው ግድግዳ ይሆንበታል፡፡ ጥሎብኝ፣ ከዚህ ግድግዳ መላተም አልወድም፡፡
Monday, June 11, 2018
ምሥጢራትን የመሳተፍ ሕይወት
በ ገብረ
እግዚአብሔር ኪደ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሰኔ 04 ቀን 2010 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን!
የኦርቶዶክሳዊ
ሕይወት ዋና ዓላማውና ግቡ ምእመናን እግዚአብሔርን እንዲመስሉ፣ በቅድስና ላይ ቅድስና፥ በክብር ላይ ክብር፥ በጸጋ ላይ ጸጋ እየጨመሩ
እየተመነደጉም እንዲኼዱ ነው፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ፡- “ለክብርህ ከፍተኛነት ፍጻሜ የለውም” እንዲል፥ ቅድስናው፣ ቸርነቱ፣ መልካምነቱ፣
ክብሩ ወሰን ድንበር ስለሌለው እርሱን መምሰልም ወሰን፣ ድንበር፣ ልክ የለውም፡፡ በዚህ ዓለም ብቻ ሳይኾን በወዲያኛውም ዓለም የማይቋረጥ
ምንድግና ነው፡፡ ስለዚህ የኦርቶዶክሳዊ ሕይወት ዋና ዓላማና ግብ እግዚአብሔርን መምሰሉ ብቻ ሳይኾን ይህ ራሱ የማይቋረጥ እድገትም
ነው፡፡ ከአንዱ ክብር ዓይን ወዳላየችው፣ ጆሮ ወዳልሰማችው፣ የሰውም ልብ ወዳላሰበው ወደ ሌላ ክብር መወለጥ ነው፡፡