በዲ/ን ሕሊና በለጠ ዘኆኅተ
ብርሃን
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሚያዝያ 16 ቀን፣ 2008
ዓ.ም.)፡-
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
በክፍል አንድ
ጽሑፍ ስለ ስግደት ምንነት ፣
በወዲቅ ፣ በአስተብርኮ
፣ በአድንኖ የሚሰገዱ የስግደት
አይነቶችን ፣ ለእግዚአብሔር
ብቻ የሚሰገድ የባሕሪይ ስግደትን
፣ ለቅዱሳን የሚሰገድ የጸጋ
ስግደትን መጽሐፍ ቅዱስን
መሠረት አድርገን አይተናል፡፡
ለቅዱሳን እንድንሰግድ ያስተማረን
እግዚአብሔር መሆኑንም በመጽሐፍ
ቅዱስ ማስረጃነት ተመልክተናል፡፡
በዚህ በሁለተኛው
ክፍል ትምህርታችን ደግሞ የሚሰገድባቸውና
የማይሰገድባቸው ጊዜያት ፤
ለመላእክት፣ ለቅዱሳንና ለቅዱሳን
ንዋያት የሚሰገድ ስግደትን
፤ የእግዚአብሔር መልአክ ባለራእዩ
ዮሐንስን አትስገድልኝ የማለቱን
ምሥጢር እናያለን፡፡