(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሐምሌ 28 ቀን 2009 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
አንድ
እኁ (ወንድም) ወደ አባ ሄላርዮን መጣና፡- “አንድ ሰው ሌሎች እርሱን የሚመስሉ አኀው ወደ ዓለም ተመልሰው ሲወድቁ አይቶ እንደ
እነርሱ ላለመውደቅ ምን ማድረግ አለበት?” ሲል ጠየቃቸው፡፡ እርሳቸውም እንዲህ አሉት፡- “አንድ ታሪክ ልንገርህ፡፡ ጥንቸሎችን
ለማደ’ን የሚሮጡ ውሾችን አስብ፡፡ ከእነዚህ ውሾች መካከል አንዱ በሩቅ ያለችን ጥንቸል ተመለከታት፡፡ ወዲያውም እርሷን ለመያዝ
ሩጫውን ጀመረ፡፡ አብረዉት የነበሩ ውሾችም አንዱ ሲሮጥ አይተው ጥንቸሊቱን ሳያዩዋት ተከትለውት ሮጡ፡፡ ለጊዜው አብረዉት ሮጡ፡፡
ሲደክማቸው ግን ሩጫውን አቆሙ፡፡ ማቆም ብቻ ሳይኾን እያዘገሙ ቅድም ወደ ነበሩበት ስፍራ ተመለሱ፡፡ ያ አንዱ ውሻ ግን ሩጫውን
ቀጠለ፡፡