Tuesday, February 9, 2016
መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የሃይማኖታችን ሊቀ ካህናት- ክፍል አንድ!!
መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የሃይማኖታችን ሊቀ ካህናት- ክፍል አንድ!!: በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ከ ሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ስለ ሊቀ ካህናችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ በስፋትና በጥልቀት የምናገኘው በዕብራውያን መልእክት ነው፡፡ ሐዋርያው መልእ...
Friday, February 5, 2016
የክርስቲያን መከራው
በቅዱስ
ዮሐንስ አፈወርቅ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ጥር 27 ቀን 2008 ዓ.ም.)፡- በስመ
አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ለአንድ
ክርስቲያን መከራው ለጥቅሙ የሚሰጠው ነው፡፡ ለአንድ ክርስቲያን መከራን
መቀበል ማለት ከሰማያዊ ክብር መሳተፍ ነው፡፡ ይህስ እንደ ምን ነው ያልከኝ እንደ ኾነም እንዲህ ብዬ እመልስልኻለሁ፡- ስንፍናንና
ክፉ ፈቃድን የሚያርቅ፣ ዓለማዊ ግብርን መውደድን፣ ውዳሴ ከንቱ መውደድን የሚያርቅ ነውና የክርስቲያን መከራው ክብርን ያስገኛል፡፡
ነፍስን የሚረዳ፣ በክብር ላይ ክብርን የሚያገኝ ነውና የክርስቲያን መከራው የሚያሳዝን መከራ አይደለም ብዬ እነግርኻለሁ፡፡
Friday, January 29, 2016
ዕረፍተ ድንግል
በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ
(ከመጽሐፈ ገጹ የተወሰደ)
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ጥር 20 ቀን
2008 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ
ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
አሐዱ አምላክ፤ አሜን፡፡
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ብሥራት ይዞ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ እመቤታችን ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ የሔደው የዕረፍቷ ጊዜ መድረሱን ለማብሠር ነበር፡፡ የድል ምልክት የሆነውን ፍሬው የተንዠረገገ የቴምር ፍሬ የሚያፈራውን ዘንባባ ይዞ ለሁለተኛ ጊዜ እርሷ ወዳለችበት ይዞ ገብቶ ደስ ይበልሽ ሲላት አሁንም እየሰገዳና እጅ እየነሣ ነበር፡፡ ጌታችን እንዳዘዘውም
"ልጅሽና ጌታሽ እናቴ ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ ጊዜው ደርሷል ብሏል፡፡ ከሴቶች ተለይተሸ የተባረክሽ ቅድስት ሆይ ስለዚህም ለሁለተኛ ጊዜ ይህን መልካም የምሥራች እነግረሽ ዘንድ ላከኝ፡፡ ብፅዕት ሆይ በምድር የሚኖሩትን ሁሉ በደስታ እንደሞላሻቸው አሁን ደግሞ በዕረፍትሽና በዕርገትሽ ምክንያት የሰማይ ኃይላት በደስታ ይሞሉ ዘንድ በሰማይ ያሉ ነፍሳትም ሁሉ ከመቼውም ጊዜ በላይ በክብር ያበሩ ዘንድ ምክንያት ትሆኛለሽ፡፡ ደስተኛይቱ ፍስሕት የሚል ማዕረግ ለዘላለም ተስጥቶሻልና ስታዝኝና ስታለቅሽ በኖርሽው መጠን ደስ ይበልሽ፡፡ ጸሎቶችሽና አስተብቁዖቶችሽ በሙሉ በልጅሽ ፊት ወደ ሰማይ ዐርገዋል፤ ስለዚህም ይህን ዓለም ትተሽው ወደ ሰማይ ትሔጅና ፍጻሜ በሌለው የዘላለም ሕይወት ከልጅሽ ጋር ትኖሪ ዘንድ አዝዟል" ብሎ ዘንባባውንም በእጇ ሰጣት፡፡
Friday, January 22, 2016
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የተረጐመው የኦሪት ዘፍጥረት መጽሐፍ በገበያ ላይ ዋለ!
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ጥር 13 ቀን 2008 ዓ.ም.)፡- በስመ
አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
በ388 ዓ.ም. ዐቢይ ጾም መግቢያ ላይ ተጀምሮ፥ በቀጣዩ ዓመት ጥቅምት መጨረሻ ላይ የተጠናቀቀው የቅዱስ
ዮሐንስ አፈወርቅ የኦሪት ዘፍጥረት የትርጓሜ መጽሐፍ የመጀመሪያ ቅጹ በገበያ ላይ ዋለ፡፡ ይህ ከሐዋርያት ዘመን አንሥቶ በተመሠረተውና
በንጉሥ ቆስጠንጢኖስ እንደ ታነፀ በሚነገረው ፓላዪያ (The Palaia) በተባለ በታላቁ ቤተ ክርስቲያን የተሰጠው ትምህርት ጠቅለል
ባለ መልኩ ሲታይ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያለውን እጅግ የጠለቀ ፍቅርና የሰው ልጅም ምን ያህል ክቡር ፍጥረት እንደ ኾነ የሚያስረዳ
መጽሐፍ ነው፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)