Monday, April 18, 2016
መቅረዝ ዘተዋሕዶ : ሰማዕታት
መቅረዝ ዘተዋሕዶ : ሰማዕታት: (መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሚያዝያ 17 ቀን 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!! ሰማዕት የሚለው ቃል ስርወ ቃሉ “ሰምዐ” የሚል ሲኾን ይኸውም ሰማ፣ አደመጠ፣ አስተ...
Sunday, April 17, 2016
ኒቆዲሞስ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሚያዝያ 9 ቀን 2008 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ኒቆዲሞስ ማለት ድል አድራጊ፣ የሕዝብ አለቃ ማለት ነው፡፡ እውነትም ይህ ሰው አለቃ ነበር፡፡ አለቅነቱስ እንደ ምን ነው? ቢሉ በሦስተ ወገን ነው፡-
(ሀ) በሹመት፡-
የአይሁድ ሸንጎ - ማለትም የሳንሄድሪን - አባል ነበርና፡፡ ይህ እንግዲህ (ምንም እንኳን የሚያውክ ንጽጽር ቢኾንም) በእኛ ስናየው የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የኾነ አንድ ሊቀ ጳጳስ እንደ ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ዝቅ ብሎ ሊማር መጣ፡፡ ከማን? ብለን ስንጠይቅ ደግሞ ይበልጥ እንደነቃለን፡፡ ምክንያቱም ምንም እንኳን ጓደኞቹ ትምህርትን የማይወዱ፣ እውነትን የሚጠሉ፣ ጌታችንን ለመግደል ዕለት ዕለት የሚመክሩ ቀናተኞች ቢኾኑም ኒቆዲሞስ ግን ከእነርሱ ተለይቶና ሹመቱ ሳያስታብየው በሥጋ ዕድሜ ከእርሱ ከሚያንስ ከጌታችን ዘንድ ሊማር ነውና የሚመጣው፡፡ እስኪ ትልቅ ጥምጣሙን አድርጎ ከጌታችን እግር ሥር ቁጭ ብሎ ሲማር በዓይነ ሕሊናችሁ ሳሉት! እንደ ምን ያለ ትሕትና ነው? እንዴት እውነትን የተጠማ ሰው ነው? “ቀን አይመቸኝምና ማታ አልሔድም፤ እንደዉም ጥሩ ምክንያት አገኘሁ” አላለም፡፡ ከጓደኞቼ ጋር ተመሳስዬ ልኑር አላለም፡፡ ጌታችን የወደደውና ለትውልድ ኹሉ የተረፈ ምሥጢር - ስለ ጥምቀት - ያስተማረውም ስለዚሁ ግሩም ትሕትናውና ቅንዓቱ ነው፡፡ “ሥራህን ትተህ ለምን በቀን አትመጣም?” አላለውም፡፡ “አንተን ብቻ አላስተምርም” አላለውም፡፡ “ለምን ጓደኞቼ ያዩኛል ብለህ ፈራህ?” አላለውም፡፡ “ለምን እንደ ዕሩቅ ብእሲ ቈጥረህ መምህር ትለኛለህ?” አላለውም፤ በፍጹም፡፡ ሹመቱና እልቅናው ሳይታሰበው ዝቅ ብሎ ሊማር መጥቷልና፡፡ “አለቃ ስኾን እንዴት ለመማር - ያውም በጨለማ - እሔዳለሁ?” አላለምና፡፡ በመኾኑም ቸሩ ጌታችን እንደ ሳምራይቱ ሴት ለብቻውም ቢኾን የማታ ክፍለ ጊዜ አዘጋጀለት፡፡
Saturday, April 2, 2016
ዕለተ ምጽአት
ምንጭ፡- ቅዳሴ አትናቴዎስ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ መጋቢት 24 ቀን፣ 2008 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ይህቺ
ዕለት (ቅድስት ሰንበተ ክርስቲያን) በምትሠለጥንበት ጊዜ አዲስ ሥራ አዲስ ነገርም ይኾናል፡፡ ያን ጊዜ የፀሐይና የጨረቃ የከዋክብትም
ብርሃን ወይም ፀዳል ወይም በጋ የለም፡፡
በውስጥዋ
በነፍስ ሕያው ኾኖ የሚንቀሳቀስ ፍጥረት ሳይኖርባት ምድር ሰባት ቀን ታርፋለች፡፡ እንደ ረቂቅ ፉጨት ያለ ቃል ይላካል፡፡ በዚያችም
ቃል የሰማያት ጽንዕ ይወገዳል፤ የምድር ግዘፍ ይነዋወጻል፡፡
ያን ጊዜ
መቃብራት ይከፈታሉ፡፡ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የፈረሱ ሙታን ፈጥነው እንደ ዓይን ቅጽበት ይነሣሉ፡፡ አብ መንግሥቱንና ፍርዱን ለልጁ
ይሰጣል፡፡ ግሩም የኾነ የነጐድጓድም ቃል ይሰማል፡፡ ከመጀመሪያው (ከጥንት) ጀምሮ ጆሮ ያልሰማው ዓይንም ያላየው!
የእሳት
ክንፎች ያሏቸው ግሩማን መላእክት በፊቱ ይቆማሉ፡፡ ስም የሌላቸው፣ እገሌና እገሌ የማይሏቸው በአብ መጋረጃ ውስጥ የሚኖሩ ባለሟሎች
መላእክት ናቸው፡፡ የሊህም ክንፍ ከክንፍ ጋር ይሳበቃል፤ ይሰማሉ፤ ያንጐደጕዳሉ፤ ሰይፋቸውንም ይመዛሉ፤ ጽናታቸውንም ያሳዩ ዘንድ
ይበራሉ፡፡
Thursday, March 31, 2016
መጻጉዕ - ለምን እስከ ሠለሳ ስምንት ዓመት ሳይድን ቆየ?
በቅዱስ ዮሐንስ
አፈወርቅ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ መጋቢት 22 ቀን 2008 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ተወዳጆች
ሆይ! እነሆ እግዚአብሔር ፈቃዱ ኾኖ በዚህ ሳምንትም “ወደ ኦሎምፒያስ የተላኩ
መልእክታት እና ሌሎች” በተሰኘ አዲስ የሊቁ መጽሐፍ ተገናኝተናል፡፡ እርሱ እስከ ወደደ ድረስም እስከ አሁን በተተረጎሙት
ሳንረካ ብዙ ለመተርጎም ወደ ፊት እንሔዳለን፡፡ የሊቁ ሥራዎች ለዚህ ትውልድ ዓይነተኛ መድኃኒቶች ናቸውና፤ እንዲሁ ለማወቅ ያኽል
ብቻ ተነብበው በመጻሕፍት መደርደሪያ ላይ የሚቀመጡ ሳይኾኑ መንፈሳዊ ሕይወታችን እንዲጎለምስ ዕለት ዕለት ልናነባቸው የሚገቡ ናቸውና፤
በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ላይ እስከ ምን ድረስ ጠንካራ ክርስቲያኖች ልንኾን እንደሚገባን የሚያሳዩ ናቸውና፡፡
ሊቁ፥
በዚህ መጽሐፍ ላይ ሦስት ዋና ዋና ርእሶችን ይዞልን ቀርቧል፡፡ በመጀመሪያው ርእስ ላይ የእግዚአብሔር ከአእምሮ የሚያልፍ አሠራርና
ፍቅር፥ ጓደኞቹ የቤቱን ጣራ ነድለው ባወረዱት ሽባ አንጻር እናያለን፡፡ እንዲሁ የበይ ተመልካቾች ግን አንኾንም፤ የድርሻችንን ዘግነን
እንወስዳለን እንጂ፡፡ በኹለተኛው ዐቢይ ርእስ “ሰው ራሱን ካልጎዳ በስተቀር ማንም እርሱን ሊጎዳው እንደማይችል” በማለት የሰው
ብቸኛና እውነተኛ ጠላቱ እርሱ ራሱ እንደ ኾነ ያስረዳናል፤ ማስረዳት ብቻም ሳይኾን መፍትሔዉንም ያመላክተናል፡፡ በሦስተኛው ዋናው
ርእስ ላይ ወደ አምስት የሚኾኑ ንኡሳን አርእስት አሉ፡፡ እጅግ በጣም አስደናቂ ወደኾነችው ወደ ዲያቆናዊት ኦሎምፒያስ የላካቸው
መልእክታት ናቸው፡፡ በእነዚህ መልእክታት ውስጥ እጅግ በጣም ብዙ አሳቦች ተነሥተዋል፡፡ በዚህ ዘመን ያሉ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ካህናትና
አገልጋዮች ከእነዚህ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ደብዳቤዎች እጅግ በጣም ብዙ ቁም ነገሮችን ያገኛሉ፡፡ ራሳቸውንና አገልግሎታቸውን
ይመዝናሉ፡፡ ምእመናንም በአስደናቂዋ ሴት አንጻር ራሳችንን እንመለከታለን፡፡ አሻቅበን ማየት ከተቻለንም ከዲያቆናዊቷ ከኦሎምፒያስ
ምን ያኽል ርቀት ላይ እንዳለን እናያለን፡፡ የዘመኑ ባለጸጎችም ከዚህች ባለጸጋ ሴት የድርሻችሁን ትወስዳላችሁ፡፡
አሁን
እዚህ የማቀርብላችሁ ትምህርትም በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት ይህ ሳምንት “መጻጉዕ” እንደ መባሉ ሊቁ በዚህ መጽሐፍ ስለ
መጻጉዕ ካስተላለፈልን ትምህርት የተቀነጨበ ነው፡፡ መልካም የምክርና የተግሣጽ ጊዜ ይኹንልዎት!
Subscribe to:
Posts (Atom)