Pages

Monday, April 7, 2014

ኒቆዲሞስ ዘሠሉስ



በዲ/ን ስመኘው ጌትዬ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ መጋቢት 29 ቀን 2006 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

 የኦሪት ሰንኮፍን ከእኛ ያራቅህልን፣ በሚደነቅ አጠራር ከጨለማ ጠርተህ የዳግም ልደትን የሠጠኸን፣ ሰውነታችን ሳይሆን ነፍሳችን የምትጠራበትን ሕጽበት ምሥጢር የገለጥክልን፣ በሌሊት ጨለማ ሕይወታችን ወደ አንተ እንገሰግሳለን፤ አንተም የጽድቅን የእውነትን ነገር ትገልጥልናለህ:: ከዚያም እውነትህን መመስከር እንጀምራለን:: በመጨረሻም ማንም በሌለበት ወቅት እንኳን ከመስቀልህ ስር ቅዱስ ሥጋህን እንገንዝ ዘንድ እንደ ኒቆዲሞስ ያለፍርሃት በጽድቅና በእውነት እንኖራለን:: ምክንያቱም በአንተ መኖር ያለውን ሰላም ከአይሁድ ተለይተን አይተናልና:: ይህ ሰላምህ ሁልጊዜ አብሮን ይኖር ዘንድ ፈቃድህ ይሁን::


 አብርሃምን በተቀበለበት፣ ይስሃቅን በመረጠበት፣ በሙሴ የዋህነት፣ በሐዋርያት ፍቅር ወደ ቤተክርስቲያን ጠራን፡፡ በረከትን፣ ጸጋን፣ ምሕረትን፣ ተስፋን ሁሉ አደለን” በማለት የዕለቱን ድርሰቱን ይጀምራል:: የተጠራንበት ምሥጢር በሰው ልቡና ታስቦ አይደረስበትም፤ ተመርምሮም አይታወቅም፤ ነገር ግን እንዲሁ የቤተክርስቲያን ልጆች የእርሱም ወዳጆች እንድንሆን ጠራን:: ከዚህ በኋላ እንደ ሁልጊዜው ቤተክርስቲያንን ሰላም ብሎ ያወድሳታል::

  ሥርጉት በስብሐት ቅድስት ቤተክርስቲያንበምሥጋና ያጌጥሽ ቅድስት ቤተክርስቲያን፣ በሰንፔር ዕንቊ በከርከዴን በጳዝዮን ዕንቊዎች ግድግዳዎችሽ ያጌጡ በወርቅ የተለበጡ ናቸው:: አንተ በምሥጋና ዙራት ቤተክርስቲያን ከፍ ከፍ ታደርግሃለች::” “አንቺ ጽዮን ቤተክርስቲያን ሆይ ተነሺ፤ ኃይልሽን ልበሺ፤ ጠላቶችሽን አሸንፊ፤ ንጉሥሽ ያስደስትሻል” እያለ ቤተክርስቲያንን ያወድሳታል:: ጌታሽ አሸናፊ ነው::

 አብርህ ለነ እግዚኦአቤቱ ብርሃንን አብራልን፤ በሰማያት ምሥጋና ይሁን፤ በምድር ላይ ብርሃንህን ታበራለህና::” አምላኬ አምላኬ የአንተን ብርሃን በሕይወታችን እንፈልጋለን፤ ብርሃንህን አይተው ካመሰገኑህ ጋር ገብቶን እናመሰግን ዘንድ ስለዚህም በችግራችን ጊዜ ወደ አንተ እንጮሃለን:: በጠዋትም ጸሎታችንን ስማ:: ነፍሳችንን ለአንተ ብቻ ሰጥተናል::

 ታቦተ ሕጉ ለእግዚአብሔር በካሕናት ሕፅርትየእግዚአብሔር የሕጉ ማደሪያ በካሕናት የታጠረች (የተከበበች) በመንፈስቅዱስ የተጋረደች ጽዮን ሆይ ንጉሥሽ ለጠላት አይሸነፍም፤ ሃገሩንም አይተዋትም::” እርሱን ተስፋ ታደርጋለችና ቤተክርስቲያን ንጉሧ ይሞትላታል እንጂ አይተዋትም፤ ሞቶ ያሸንፍላታል፤ ልጆቿን ከጠላት ምርኮ ከኃጢአት ግዛት ይጠብቃቸዋል::

 አንሰ እትአመን ወአሰምክ ላዕለ እግዚአብሔርእኔ በእግዚአብሔር እታመናለሁ፤ ወደ እርሱ እጠጋለሁ፤ በክርስቶስ ዕፀ መስቀልም እመረኮዛለሁ፤ እርሱ ማዳንም መርዳትም የሚችል ነው፤ እርሱ ምሕረት ማድረግ ይችላል::” ወንድሞቼ ማዳን የሚችለውን እንደገፍ እንጂ በሃብትና በውበት በሚጠፋውም የምድር ነገር አንመካ::

 ንሕነ አግብርቲከ ወአእማቲከ ተማኅፀነ ኀቤከእኛ አገልጋዮችህና ባሮችህ ወደ አንተ ተማጽነናል፡፡ ከፊትህ አትተወን (አትጣለን) ነፍሳችንን እንደ ጥላ ከሚሄደው ከሞት ወጥመድ አድን::” ሰውን የምትወድ ሁልጊዜ ስምህን እንጠራ ዘንድ በመድኃኒትህ ጎበኘን:: ጾሙን በሰላም አስፈጽመን::

 በጾም ወበጸሎት በስዒል ወበሰጊድበጾምና ጸሎት፣ በልመናና በስግደት አባቶቻችን ከጥፋት ዳኑ፤ ከሞት ወደ ሕይወት ተሻገሩ:: የሰላም አምላክ መድኃኔዓለም ጻድቃንን ይወዳል፤ መገባቸው፤ መራቸው እንደ ዐይኑ ብሌን ጠበቃቸውበሰላም ንጹም ጾመበሰላም ጾምን እንጹም፤ ወንድሞቼ በመፋቀር እንኑር፤ ከጠላቶቻችን ያድነን ዘንድ ሕማማችንን ከእኛ አርቆልን እናደንቅ ዘንድ::” ሰላሙን ይስጠን::

No comments:

Post a Comment